Get Mystery Box with random crypto!

#Update የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፥ ዛሬ በባሕር ዳር ስታዲየም በነበረ የዒድ ሶላት ስነ | TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፥ ዛሬ በባሕር ዳር ስታዲየም በነበረ የዒድ ሶላት ስነስርዓት ወቅት ፥ ከቀናት በፊት በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የተፈፀመውን ግድያ በጽኑ እንደሚያወግዝ ገልጿል።

ህዝበ ሙስሊሙ ጉዳዩን እጅግ በሰከነ መንገድ ፣ በአስተውሎት ተመልክቶ ችግሩ እንዳይባባስ ላደረገው ጥረት ምስጋና አቅርቧል።

ግድያው የዒድ አልፈጥር በዓል በሀዘን ስሜት እንዲከበር እንዳደረገውም ገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ  ፤ በአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ የተፈፀመውን ግድያ " አረመኔያዊ ነው " ያለ ሲሆን " ግድያው በዓሉን #በሀዘን ውስጥ ሆነን እንድናከብረው አስገድዶናል " ብሏል።

ግድያውን " የሽብር ድርጊት ነው " ሲልም ጠርቶ " ሁሉም ሰው በአንድ ቃል ማወገዝ አለበት " ሲል ገልጿል።

ህዝበ ሙስሊሙ ከሌላው ወገኖቹ ጋር ግጭት ውስጥ እንዲገባ ፣ አካባቢውን ፣ ከተማውን እንዲሁም ክልሉን የእልቂትና ውድመት ማዕከል ለማድረግ የታሰበ ግድያ ነው ሲልም አስረድቷል።

የሙስሊም ማህበረሰብ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ በመመልከት የግድያው ፈጻሚዎች በህግ አግባብ ብቻ እንዲዳኙ እንጂ " እሾህን በእሾህ መንቀል " ተገቢ አይደለም በማለት ላደረገው አስተዋጽኦ ፣ መረጋጋትና ስክነት የከተማው አስተዳደር ምስጋና አቅርቧል።

ከቀናት በፊት በባህር ዳር ቀበሌ 14 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቹ እንዲሁም 1 ጎረቤታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ሰዎች በጥይት ተመተው መገደላቸው ይታወሳል።

እስካሁን ከግድያው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋለ አካል ስለመኖሩ በይፋ የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia