Get Mystery Box with random crypto!

“ በፀጥታ ጉዳይ ምንም አይነት ድርድር የለም ” - አዲስ አበባ ፓሊስ በአዲስ አበባ ከተማ በፋ | TIKVAH-ETHIOPIA

“ በፀጥታ ጉዳይ ምንም አይነት ድርድር የለም ” - አዲስ አበባ ፓሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ በፋኖና በፓሊስ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ አንድ ሲቪልና ሁለት ታጣቂዎች ሲገደሉ፣ በሁለት የፓሊስ አባላት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

የ“ፋኖ” አመራርና አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሚሊኒየም አዳራሽ አጠገብ ከፀጥታ አካላት ተኩስ እንደከፈቱ፣ በ “ፋኖ” በኩል ሁለት ታጣቂዎች ሲገደሉ አንድ በቁጥጥር ስር እንደዋለ፣ በመንግሥት በኩል ሁለት የፓሊስ አባላት ላይ ጉዳት እንደደረሰ፣ በንጹሐን በኩል ደግሞ አንድ አሽከርካራ እንደተገደለ፣ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በሰጡት ቃል፣ “ የተገደሉት የ “ፋኖ” ቡድን አመራርና አባላት ናቸው። አመራሩ ናሁሰናይ አንዳርጌ ነው። ሌላው አቤኔዘር ጋሻው የተባለው ነው፣ እዛው ቦታው ላይ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሂወቱ አልፏል። ሀብታሙ አንዳርጌ ግን ምንም አልሆነም በቁጥጥር ስር ውሏል ” ብለዋል።

የ “ፋኖ” አመራርና አባላት የነበራቸውን እንቅስቃሴ ሲያስረዱም ኮማንደሩ፣ “ በከተማው ውስጥ ነው የሚንቀሳቀሱት የነበረው። በከተማው ውስጥ ደግሞ የተለያዩ ጥፋቶች ለማጥፋት ነው እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበረው ” ነው ያሉት።

አክለውም፣ “ እነርሱን ለመያዝ በተደረገው ሂደት ቦሌ ወረዳ 3 ሳጅን አራርሳ ተሾመና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ የሚባሉ ሁለት የፓሊስ አባላት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ከእነርሱ (“ፋኖ”) በተተኮሰ ጥይት ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ እሱም ብቻ አይደለም አንድ አሽከርካሪ እንዲጭናቸው ሲያስገድዱት ‘አልተባበርም’ ስላለ መኪና ውስጥ በጥይት መትተውት ሞቷል። የአንድ ግለሰብ ተሽከርካሪ መስታውት በጥይት መትተውታል። ሙሉ ለሙሉ ጉዳት ደርሶበታል። ሰውየው ግን ምንም የሆነው ነገር የለም ” ነው ያሉት።

“ ማኀበረሰቡ ከፓሊስና ከፀጥታ አካላት የሚተላለፉ መረጃዎችን በቁም ነገር ማዳመጥ፣ አካባቢውን ማዬት መቻል አለበት። በሰላምና በፀጥታ ጉዳይ ምንም አይነት ድርድር የለም። እነዚህ ሰዎች መካከላችን አሉ። ይሄ አንዱ ማሳያ ነው። ቦሌ መሀል ከተማው ላይ እንግዲህ እየኖሩ ነው የነበረው ” ብለዋል ኮማንደር ማርቆስ።

“ እነዚህ ሰዎች መንፈስ አይደሉም። በተሽከርካሪያቸው ሲወጡ ሲገቡ ይታያሉ። ግን ፓሊስ በራሱ ነው ሲከታተተል የነበረው ” ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፤ አሁንም ማህበረሰቡ አካባቢውን መጠበቅ አለበት ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia