#Ethiopia " የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53% ድርሻ ይዟል " - የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ አምራቾች ማህበር በተጠናቀቀው ዓመት አደረኩት ባለዉ ጥናት " ለሁለተኛ ጊዜ በጥቅም ላይ የሚዉሉ ልብሶች በሀገሪቱ ለሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ገበያውን ይበልጥ ፈታኝ እንዲሆን እያደረገው " ነው ሲል ገለጸ። የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53% ድርሻ ይዘዋልም ብሏል። ማህበሩ ምን አለ ? - በተለምዶ ቦንዳ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አልባሳት የሃገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያን 53 በመቶ ድርሻ ይዘዋል። - እነዚህ ልብሶች ዋጋቸዉ ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ ዘንድ በጥራት የተሻለ ወይም ተቀባይነት ባላቸው አምራቾች የተመረቱ ናቸው በሚል አመለካከት ፍላጎቱ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል። - በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት አልባሳት ገበያ 71.22 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ አለው። እኤአ በ2030 ደግሞ ወደ 282.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። - የኢትዮጵያ የአልባሳት ገበያ በአሁኑ ወቅት ከአዉሮፓ እና አሜሪካ በመጡ የቦንዳ ልብሶች ተሞልተዋል። - የቦንዳ ልብሶች ወደ ሀገር በተለያዩ መንገዶች የሚገቡ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው በሞያሌ ፣ በድሬዳዋ እና በሌሎች የድንበር ከተሞች ከሚባሉት በተጨማሪ በ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩልም በተለያዩ ሁኔታዎች ይገባሉ። - ሀገሪቱ በአማካኝ 54 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የጨርቃጨርቅ አልባሳት ያለ ክፍያ (በዜሮ ወጪ) ድንበር አቋርጠው ይገባሉ። በዚህም ኢትዮጵያ በዓመት ከታክስ ገቢ 2.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ይደርስባታል። - በህገወጥ መንገድ የሚገቡ ልብሶች የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪውን መፈታተናቸውን ቀጥለዋል ፤ ለኪሳራ እንዲዳረጉም እያደረጉት በመሆኑ በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ቅሬታዎችን ያቀረብን ቢሆንም ምላሽ አላገኘንም። ምንጭ ፦ የካፒታል ጋዜጣ @tikvahethiopia 225.8K viewsedited 15:55