Get Mystery Box with random crypto!

' ኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም ' - ሞህሰን አል-ማንዳላዊ የኢራቅ ፓርላማ የግብረ | TIKVAH-ETHIOPIA

" ኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " - ሞህሰን አል-ማንዳላዊ

የኢራቅ ፓርላማ የግብረ ሰዶናዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ተግባርን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል።

በአዲሱ ሕግ ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት እርስ ቤት ይወረወራሉ።

እንዲሁም፦

- ግብረ ሰዶማዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤

- ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ

- ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና ሚያደርጉ ዶክተሮች

- ሆን ብለው ልክ #እንደ_ሴት_የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ።

የኢራቅ ፓርላማ ተጠባባቂ አፈጉባኤ ሞህሰን አል-ማንዳላዊ ፥ " ይህ አዲስ ሕግ የህብረተሰቡን የሞራል / የግብረገብ / የስነምግባር መዋቅር ለመጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል።

" በኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " ያሉት አል-ማንዳላዊ ፥ " ይህ የኢራቅ ምድር የነቢያት፣ የንፁህ ኢማሞች ፣ የጻድቃን እንዲሁም ቅዱሳን ምድር ነው " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ፎቶ፦ ፋይል

#Iraq

@tikvahethiopia