Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-ETHIOPIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopia — TIKVAH-ETHIOPIA
ርዕሶች ከሰርጥ:
Gbe
Questionandanswer
Globalbankethiopia
Bankinethiopia
Oursharedsuccess
Furtheraheadtogether
Mpesasafaricom
Addisababa
Update
Genocide
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethiopia
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.34M
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2024-04-22 17:05:51
#RoseWood

የቤትዎን ካቢኔት ሲያዙን ፦
በ አርኪቴክት ባለሞያ ለክተን እና ዲዛይን አደርገን
ካሉበት አድራሻ ዴሊቨር አድረገን
ካቢኔት ከነግራናይት እና ሲንክ በጥንቃቄ ገጥመን ለመገልገል ዝግጁ የሆነ ካቢኔት በአጭር ጊዜ እናስረክባለን ።

ሮዝዉድ ፈርኒቸር ፦ 0905848586

ኣድራሻ ፦ 4ኪሎ ኣምባሳደር ሞል 2ኛ ፎቅ 
                 እንቁላል ፋብሪካ ሩፋኤል

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/R0seWood
42.0K views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 21:36:31
" የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል "

ሰሞኑን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተማሪ የምግብ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ፤ " የምግብ በጀት እጥረት ገጥሞናል ያለውን ብሉ " አይነት ማስታዎቂያዎች መለጠፋቸውን ተከትሎ በበርካቶችን አነጋግሯል።

ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተለጠፉ ማስታወቂያዎች ምንድነው የሚሉት ?

- " እንደ ሀገር የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል። የምግብ ጥሬ ዕቃ ዋጋም በየቀኑ #ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት ተቆጥሯል። "

- " ተቋማችን የሚያደርገው ድጎማ ተማሪዎቻችን ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ ባሉን የምግብ ጥሬ እቃዎች አገልግሎት እየሰጠን ቢሆንም በአሁን ሰዓት እጅግ በጣም #እየከበደ ስለሆነ የሜኑ ማሻሻያ ለማድረግ ተገደናል። "

- " ከአሁን በኃላ የተሻሻለው ሜኑ ተግባራዊ ይሆናል። "

- " በተወሰኑ በስቶራችን ውስጥ ባሉ የምግብ ጥሬ ዕቃዎች እና በአትክልት የምግብ አገልግሎት እየሰጠን ነው። በአስቸኳይ የምግብ ጥሬ ዕቃ ግዥ አቅርቦት እንዲሟላ ጠይቀናል እስከዛ ታገሱ። "

... ይላሉ ማስታወቂያዎቹ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፥ በዲላ እንዲሁም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ካሉ የቤተሰቡ አባላት ማህተም ያረፈባቸውን ማስታወቂያዎች ተልኮለት ተመልክቷል።

ይህ ነገር የቤተሰብ የጭንቀት ምንጭ ከመሆኑ በላይ ፦

° ዩኒቨርሲቲን የሚያክል እጅግ ትልቅ ተቋም እንዴት መጭውን የዋጋ ንረት እንዲሁም የዓመቱ የምግብ ወጪ ያላገናዘበ በጀት ይይዛል ?

° ለረጅም ዓመታት ለተማሪ በቀን የሚመደበው ገንዘብ አነስተኛ ሆኖ ሳለ እንዴት ይህ ሊፈጠር ቻለ ? የሚሉና ሌሎች ነቀፌታዎች ተሰምተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ " የምግብ በጀት እጥረት ገጥሞናል " የሚል ማስታወቂያ ከተለጠፈባቸው ተቋማት አንዱ ወደሆነው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ደውሏል።

የተከሰተው ችግር ምንድነው

በዚህ አይነት ሁኔታ ተማሪዎች ከመጎዳታቸው በላይ ወላጆችንስ አያስጨንቅም ወይ ... ሲል ለዩኒቨርስቲው የምርምር እና ቴክኖሎጂ ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ሀብታሙ ተመስገን ጥያቄ አቅርቧል።

ዶ/ር ሀብታሙ ፤ ማስታወቂያውንም ሆነ ሀሳቡን እንደማያዉቁት በመግለጽ " ማን ይህን ሀሳብ እንዳመጣ እንዲሁም ማስታወቂያ እስከ መለጠፍ ድረስ እንደደረሰ እናጣራለን " ብለዋል።

" ተማሪዎች ሆኑ ወላጆች ምንም የሚያሳስባቸዉ ነገር ሊኖር አይገባም " ያሉ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዉም ሆነ እርሳቸዉ የሚመሩት የተማሪዎችን ጉዳይ የሚመለከት ቢሮ ችግሩ እንደሌለበት ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ማስታወቂያ ወደ ተለጠፈበት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ደውሏል።

የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር አክብር ጩፋ ፥ " ሶሻል ሚዲያ ላይ መረጃው ሲንሸራሸር እያየን ነው " ብለዋል።

" ሁኔታዉን ለማጣራት #ማኔጅመንቱ ስብሰባ ይቀመጣል። የስብሰባዉን ወጤት የተመለከተ መረጃ በፍጥነት አደርሳችኋለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

NB. ከላይ ተየያያዙት ማስታወቂያዎች ማህተም ያረፈባቸው ናቸው።

መረጃው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ ነው የተላከው።

@tikvahethiopia
236.1K views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 21:21:50
#Update

' ቲክቶክ ' አሜሪካ ውስጥ ከታገድኩኝ " የ170 ሚሊዮን አሜሪካውያን የመናገርና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ይረገጣል " አለ።

ይህን ያለው የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት መተግበሪያው ከቻይና ካልተፋታ እንዲታገድ ረቂቅ ህግ ካጸደቁ በኃላ ነው።

የ 'ቲክቶክ' ቃል አቀባይ መተገበሪያው እንዲታገድ የሚለውን ረቂቅ ህግ አውግዘዋል።

" ከታገደ ፦
- የ170 ሚሊዮን አሜሪካውያንን የመናገር መብት ይረግጣል፣
- 7 ሚሊዮን ንግዶች እንዲጠፉ ይሆናል፣
- ለአሜሪካ ኢኮኖሚ በዓመት የሚገባውን 24 ቢሊዮን ዶላር ያሳጣል " ብለዋል።

አክለው ፤ " ባይትዳንስ የቻይና ወይም የሌላ አገር ወኪል አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።  " የቻይና ኩባንያ እንዳልሆነም በተደጋጋሚ ተናግረናል " ሲሉ አክለዋል።

ጉዳዩን የሚከታተሉ አካላት ግን ' ቲክቶክ ' ከቻይና ተፋቶ ድርሻው ለአሜሪካ ሰዎች ካልተሸጠ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ #የመታገዱ ነገር አይቀሬ ነው ብለዋል።

ትላንት የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ' ቲክቶክ ' በመላው ሀገሪቱ እንዲታገድ የሚያደርግ ረቂቅ ህግ አጽድቋል።

@tikvahethiopia
226.7K views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 23:37:53
#Update

የ " ቲክቶክ " እገዳ በኪርጊስታን ተግባራዊ ሆነ።

ኪርጊስታን " ቲክቶክ " በመላ ሀገሪቱ  እንዲታገድ ውሳኔ ማስለፏ ይታወሳል በዚሁ ውሳኔ መሰረት የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ትዕዛዙን ወደ መፈጸም #እርምጃ ገብተዋል።

በሀገሪቱ " ቲክቶክ " መስራት እንዳቆመም ተነግሯል።

ሰዎች መተግበሪያውን ሲከፍቱን የሚያገኙት መልዕክት " Unable to load, please try again." የሚል ነው።

ውሳኔው በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት መ/ቤት የተላለፈ ነው።

የኪርጊስታን ዲጂታል ሚኒስቴር ቲክቶክን የሚያስተዳድረው ' ባይት ዳንስ ' ኩባንያ ፥ " #የልጆችን ፦
- አእምሯዊ፣
- አካላዊ፣
- መንፈሳዊ እና #ሥነምግባራዊ እድገትን ለመጠበቅ በህግ የተዘረዘሩ ህጋዊ መስፈርቶችን ማክበር አልቻለም " ብሏል።

በዚህም ምክንያት " ቲክቶክ " በሀገሪቱ እንዳይሰራ ተደርጓል።

ውሳኔው የተቃወሙ አካላት ይህ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ገደቡ እንዲነሳ ጠይቀዋል። ከገደብ ይልቅ ቁጥጥር ይደረግበት ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የኪርጊስታን የባህል፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ፥ " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው " ማለቱ ይታወሳል።

መተግበሪያው #ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ #መቆጣጠሪያ እንደሌለው ነበር የገለጸው።

በተጨማሪም ለተጠቃሚዎቹ ትክክለኛ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎች እንደለለው እና ተጠቃሚዎችን በአጫጭር የቪዲዮ ክሊፖች ወደ ምናባዊ ግዛት በመሳብ #ሱስ የሚያስይዝ ይዘት እንዳለው አስረድቶ ነበር።

ሚኒስቴሩ " ቲክቶክ " በወጣቱ ትውልድ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው በአጠቃላይም ለትውልዱ ጠንቅ እየሆነ እንደመጣ አሳውቆ ነበር።

በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ውስጥ ከመረጃ ደህንነት ጋር በተያያዘ መተግበሪያው እንዲታገድ ከፍተኛ ግፊት እየተደረገ ሲሆን  " ቲክቶክ " ከቻይናው ኩባንያ ካልተፋታ / አሜሪካ የምትቆጣጠረው አይነት ካልሆነ በመላ ሀገሪቱ መታገድ ዕጣ ፋንታ ሊገጥመው ይችላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
170.8K views20:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 23:27:58
የከባድ መኪና ሆነ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሹፌሮች በተለያዩ ወቅቶችና ቦታዎች በታጣቂዎች የሚደርስባቸውን ፦
- ግድያ ፣
- እገታ ፣
እምዲሁም የተሽከርካሪዎች ቃጠሎ በተመለከተ በተደጋጋሚ መረጃዎችን መለዋወጣችን ይታወሳል።

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን መቂ አካባቢ “ የታጠቁ ኃይሎች ” በአሽከርካሪና ረዳት ላይ ጉዳት እንዳደደረሱ ፣ ከወራት በፊትም በርካታ ተሽከርከርካሪዎች ታቃጥለው እንደነበር ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ቃላቸውን የሰጡ የመቂ ነዋሪ ፥ አንድ የአይሱዚ ሹፌር ሲገደል ፣ ረዳቱ አካላዊ ጉደት እንደረሰበትና ሌሎች ተሽከርካሪዎች በጥይት እንደተበሳሱ አስረድተዋል።

" የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው ሹፌሩ ተገደለ። ሚያዚያ 9 ቀን 2016 ዓ/ም ነው የተቀበረው ፤ ረዳቱም ቆሰለ " ሲሉ ነው የተናገሩት።

የተኩስ እሩምታ የተከፈተባቸው ከ7 በላይ ተሽከርካሪዎች መሆናቸውን ጠቁመው " ተዘግቦ እንኳን አየዋለሁ ብዬ ነበር የዘገበው ሚዲያ የለም " ብለዋል።

ሟቹ ሹፌር መነሻውን አዲስ አበባ በማድረግ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት መቂ አካባቢ ማታ ላይ በታጣቂዎች ተኩስ እንደተከፈተበት አስረድተዋል።

" ሌሎቹ ሹፌሮች ፈጣሪ አትርፏቸው አልተጎዱም። ተሽከርካሪዎቻቸው ግን በጥይት ተበሳስተዋል። ጎማው እስከ 15 ጥይት  ያረፈበት አለ " ብለዋል።
 
እኚሁ ነዋሪ ታጣቂዎች " ወደ ኦሮሚያ ተሽከርካሪ እንዳይሄድ ሰሞኑን እቀባ ጥለዋል " ያሉ ሲሆን ጥቃቱን በከፈቱ በማግስቱ  " ከመከላከያ ጋ ተታኩሰዋል "  ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላኛው ነዋሪ ፤ የዛሬ ወር ገደማ በተመሳሳይ እዛው ቦታ/መቂ ብዙ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል ሲሉ አስታውሰዋል።

" ጥቃቱ አለ አሁንም አልቆመም። የተወሰነ ጊዜ መከላከያ ሲመጣ ጋብ ይላል እንጂ። ሹፌሮች ስቃይ ላይ ናቸው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ እጅግ ትኩረት ይሻል የተባለውን የሹፌሮችን ጥቃት በተመለከተ ከክልሉም ሆነ ከዞኑ ኃላፊዎች ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፣ ምላሽ የሚሰጡ ከሆነ የሚያስተናግዳቸው መሆኑን ያሳውቃል።

NB. መቂ ከሰሞኑን ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር ግድያን ያስተናገደች ከተማ ናት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
164.3K views20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 20:29:33
" የመምህራን የስነ-ልቦና ቁስል ሳይሽር ስለ የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ማሰብ ይከብዳል "  - ማህበሩ

የትግራይ መምህራን ማህበር በድጋሚ የመምህራን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛቸው እንዲከፈል ጠየቀ።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርንም ዳግም አስጠነቅቋል። 

ማህበሩ ሚያዚያ 8 በኣክሱም ከተማ 33ኛው ጉባኤውን አካሂዶ ነበር። በጉባኤው ማጠቃለያ ባወጣው የአቋም መግለጫ " የትግራይ መምህራን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛቸው እንዲከፈል " ሲል ጠይቋል።  

የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ እስከ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከሚመለከታቸው የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር በመገናኘት ስለ ውዙፍ ደመወዝ መከፈል የመጨረሻ አቋሙ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል።

ለጥያቄው በጊዜ ገድብ የተወሰነ አሳማኝ መልስ ካላገኘ ጠበቃ አቁሞ ክስ እንደሚመሰርት አሳውቋል።

" ተቃውሟችን እና ጥያቄያችን ትምህርት ቤቶች በመዝጋትና ተተኪ ዜጋ በመጉዳት የማሳካት ፍላጎት የለንም " ያለው ማህበሩ " ግዴታችን እየፈፀምን መብታችን እስከ ጫፍ እንጠይቃለን " ብሏል።

" የመምህራን የስነ-ልቦና ቁስል ሳይሽር በትምህርት ስለሚገነባው ትውልድና የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ማሰብ ይከብዳል "  ሲልም አክሏል።

ማህበሩ የመምህራን ጥያቄ እስኪመለስ ህጋዊ ተቋውሞ ማሰማቱን እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

መረጃውን የመቐለው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ፥ ድምጺ ወያነ ቴሌቪዥንን ዋቢ አድርጎ ነው የላከው።

ፎቶ ፦ ፋይል
      
@tikvahethiopia            
196.0K viewsedited  17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 20:11:38
" ልጄን አድኑልኝ " - መምህርቷ እናት

መምህርት አልሻምጌጥ ንጉስ ፤ ልጇ የአብቃል በተወለደ በሀያ አንድ ቀኑ ነው የልብ ህመም እንዳለበት ያወቀችው።

ላለፉት 5 አመታት የህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና መዕከል አስመዝባ ብጠብቅም ወረፋ ሊደርሳት አልቻለም።

" አሁን ልጄ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደረሰ " ስትል ገልጻለች።

ከሀያ አንድ ቀኑ ጀምሮ ከሀዋሳ አዲስ አበባ እየተመላለሰች ሰርጀሪውን ስትጠብቅና ማስታገሻ መድሀኒት ስትጠቀም ብትቆይም እንደልጅነቱ መቦረቅ ያልቻለው የአብቃል  " አሁን ላይ የልቡ ክፍተት አራት ሚሊ በመድረሱ እብጠት ፈጥሮበታል " ስትል አስረድታችለ።

ይህ እብጠት ምግብ እንዳይረጋለት ከማድረጉ በላይ በአፍና በአፍንጫዉ ደም መውጣት መጀመሩ እና ድንገት በየሰአቱ እራሱን ከመሳቱ በተጨማሪ ፍጹም የድካም ስሜት ውስጥ እንዲገባ በማድረጉ ለቤተሰቡ ታላቅ ድንጋጤ ፈጥሯል።

ይህን ተከትሎ ጤና ባለሙያዎች በቶሎ ሰርጀሪዉ መሰራት እንዳለበት ቢናገሩም የመምህር ደሞዙን ከእለት ጉርስ አበቃቅቶ ለመድሀኒት ሲጠቀም ለቆዉ የመምህር አልሻምጌጥ ቤተሰብ ዱብ እዳ ሆኖበታል።

ቤተሰብም አሁን ላይ የሚያደርገዉ ጠፍቶበታል።

በጉዳዩ ላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ በቲኪቫህ ኢትዮጵያ በኩል መልእክት አስተላልፉልኝ የምትለው እናት አሁን ላይ በግል ሆስፒታል ለሰርጀሪዉ ብቻ 650 ሽህ ብር እንደተጠየቀ በአጠቃላይ ከ800 እስከ 900  ሽህ ብር እንደሚያስፈልግ ገልጸለች።

ይህን ማድረግ ባለመቻሏ እና ገንዘብም ስለሌላት ልጇን አይኗ እያዬ ልታጣዉ መሆኑን በእንባ ተናግራለች።

በመሆኑም ፥ " ደጉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚቻለዉን አድርጎ ልጄን ያድንልኝ " በማለት ተማጸናለች።

መምህር አልሻምጌጥ ንጉስን በስልክ ማነጋገር የሚፈልግ የግል ስልክ ቁጥሯ 0916155490 ነው። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000243926053 የሂሳብ ቁጥሯ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
194.1K viewsedited  17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 20:11:23
የፋሲካ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የመግቢያ ትኬትዎን በቴሌብር *127# ወይም http://onelink.to/fpgu4m በመግዛት ጎራ ይበሉ፤ እስከ ብር 2500 ለሚደርሰው ግብይትዎ የአየር ሰዓት እና ጥቅል የሚገዙበት 10% ተመላሽ ያግኙ፡፡

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
171.1K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 20:11:18
#BankofAbyssinia

በተለያዩ ቦታዎች በአፖሎ ሲከፍሉ ቅናሽ ያገኛሉ!

አሁኑኑ መተግበሪያውን በማውረድ ይጠቀሙ።

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
190.0K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 10:53:12
#Update

" የሟች ቤተሰብ ተገኝቷል " - ፖሊስ

በሟች ኪስ ማንነቱ የሚጠቅስ መረጃ በማጣቱ  ምክንያት የሟችን ፎቶ በመለጠፍ  ቤተሰቦቹን አፋልጉኝ ያለው የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ የሟች ቤተሰብ መገኘቱ አስታውቋል።

የማህበራዊ የትስስር ገፆችና ሚድያዎች በሟች ቤተሰብ ፍለጋ ያደረጉት የነቃ ወገናዊ ተሳትፎና ጥረት አመስግኗል።

ለሟቹ ቤተሰብ ክብር ሲባል ፎቶውን ከገፃቸው በማጥፋት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል።

በዚህም መሰረት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለሟች ቤተሰብ ክብር የሟችን ፎቶ #ማጥፋቱን ለመላ አባላቱ መግለጽ ይወዳል።

ምናልባት በውስጥ የተቀባበላችሁም የሟችን ፎቶ ከስልካችሁ እንድታጠፉ እንጠይቃለን።

ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት በዓዲግራት ከተማ አንድ ወጣት ተገድሎ ተጥሎ መገኘቱንና በግድያው የተጠረጠሩ 3 ግለሰቦች ሟቹ ከወደቀበት አቅራቢያ በሚገኝ አንድ መጠጥ ቤት በቁጥጥር ስር መዋላቸው መረጃ እንደላክልንላችሁ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
261.4K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ