Get Mystery Box with random crypto!

#FakeNews አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምንም አይነት የተለየ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም። ከ | TIKVAH-ETHIOPIA

#FakeNews

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምንም አይነት የተለየ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም።

ከወራት በፊት መሰል የፈጠራና ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ የ #የሶማሊያ አክቲቪስቶችና የማህበራዊ ትስስር ገጾች ከሰሞኑን ዳግም የፈጠራ ወሬዎችን ፅፈው ማሰራጨትን ይዘዋል።

እያሰራጩ ካሉት ሀሰተኛ እና የፈጠራ ወሬ አንዱ " በአዲስ አበባ የተለየ ሁኔታ እንዳለ ፣ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደጨመረ፣ በየቦታው ወታደሮች እንደተበተኑ " የሚገልጽ ነው።

ይህ ሀሰተኛ እና የፈጠራ ወሬ ሲሆን በከተማዋ ውስጥ አንዳችም የተለየ የወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም።

ምንም እንኳን ጉዳዩ ውሸት ቢሆንም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህ ሀሰተኛ መረጃ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እየተመለከቱት ፣ እያጋሩት እንደሆነ መመልከት ተችሏል ስለሆነም ጥንቃቄ አድርጉ።

#AddisAbaba #Ethiopia

@tikvahethiopia