2021-10-03 23:25:30
#Ethiopia ነገ ምን ይጠበቃል ?
• ነገ ጥዋት ከ2:30 ጀምሮ 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ ይካሄዳል።
• በሁለቱም ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤ ይሰየማሉ።
• የምርጫ 2013 አሸናፊው የሆነው " ብልፅግና ፓርቲ " እጩ አድርጎ የሚያቀርባቸው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ይሾማሉ።
• የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአፈ ጉባኤ፣ ምክትል አፈ ጉባኤ እንዲሁም እጩ ሆነው የሚቀርቡትን ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
• ሹመቱ የሚፀድቅላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር በምክር ቤቱ ንግግር ያደርጋሉ።
• ምናልባትም ተደራራቢ ፕሮግራም ከሌለ የሚሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ካቢኔያቸውን ያዋቅራሉ ፤ ይፋ ያደርጋሉ [ ይህ ፕሮግራም ምናልባት በቀጣይ ቀናት ሊሆን ይችላል ተብሏል ]
• በመስቀል አደባባይ ልዩ የመንግስት ምስረታ እና የተሿሚው ጠቅላይ ሚኒስትር በዓለ ሲመት ስነስርዓት ይካሄዳል።
ነገ ኢትዮጵያ ለምትመሰርተው አዲስ መንግስት ስነስርዓት ላይ ለመታደም የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና ባለስልጣናት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን እስካሁን ባለው መረጃ ፦
- የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሀመድ ቡሃሪ
- የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል
- የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሌሴንጎ ኦቦሳንጆ
- የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራማታን ላማምራ አዲስ አበባ ገብተዋል።
@tikvahethiopia
48.3K viewsedited 20:25