Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-ETHIOPIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopia — TIKVAH-ETHIOPIA
ርዕሶች ከሰርጥ:
Gbe
Questionandanswer
Globalbankethiopia
Bankinethiopia
Oursharedsuccess
Furtheraheadtogether
Mpesasafaricom
Addisababa
Update
Genocide
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethiopia
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.34M
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 431

2021-09-29 16:21:09
159.9K viewsedited  13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 16:20:58
ከ 100% በላይ ቦነስ ለወዳጆችዎ!

ከ አሜሪካ ፣ ከአውሮፓ ፣ ከአረብ ሃገራት ፣ ከደቡብ አፍሪካ እና ከሌሎች ሃገራት የሞባይል ካርድ ለቤተሰብዎ በመላክ የመስቀል ደመራ በዓልን ደማቅ ያድርጉ።

አሁኑኑ ይላኩ ፣ እስከ መስከረም 19 ብቻ የሚቆየውን ከ 100% በላይ ቦነስ ያሸልሟቸው።

ህጋዊ የሞባይል ካርድ አስተላላፊ ድርጅቶችን መረጃ ለማግኘት ethioremit.com ይጎብኙ
ወይም እንዴት መላክ እንደሚችሉ ፈጣን መረጃ ለማግኘት @ethioremit ይቀላቀሉ::
159.3K views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 13:49:22
#Metekel በመተከል የፀጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸው ፤ ከ194ቱ ውስጥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ፤ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፍረሳቸው ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው ዛሬ በአሶሳ በጀመረው 23ኛው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቀፍ ትምህርት ጉባኤ ላይ ነው።፡

በዚሁ መድረክ ላይ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ቢንያም መንገሻ እንደተናገሩት ፤ በመተከል ግጭት ትምህርት ቤቶቹ የተጎዱት በ2013 ዓ.ም ሲሆን እነዚህም የመጀመሪያ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ናቸው ብለዋል።

በፀጥታ ችግር ከተጎዱ 194 ትምህርት ቤቶች ፥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን፤ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፈራረሳቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ትምህርት ቤቶቹ 69 ሺህ ተማሪዎች የሚማሩባቸው እንደነበሩ ገልፀዋል።

የትምህርት ቢሮ ኃላፊው ፥ የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እንዲሁም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ተዘጋጅቶ እየተሠራ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
182.9K viewsedited  10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 13:20:16
182.1K viewsedited  10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 12:57:41
175.6K viewsedited  09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-28 22:39:34
#GONDAR : በጎንደር ከህገወጥ ተኩስ ጋር በተያያዘ የከተማው ፖሊስ መሳሪያ የማስወረድ ስራ እና ሰዎችን የማሰር እርምጃ እየወሰደ ነው።

ከትንላት ጀምሮ እስከ አሁን ሰአት ድረስ የጎንደር ከተማ ፖሊስ ከ50 የሚበልጥ የጦር መሳሪያ ያስወረደ ሲሆን ከህገወጥ ተኩስ ጋር በተያያዘ ከ30 በላይ ሰዎችን ማሰሩንና ፍ/ቤት በማቅረብ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ለጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

ስራው እየተሰራ የሚገኘው ከፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ አድማ ብተና፣ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ሃይል እንዲሁም ከከተማው የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ አመራሮችን ባካተት ቡድን ነው ተብሏል።

የጎንደር ከተማ ፓሊስ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ማምሻውን ለጎንደር ኮሚኒኬሽን በሰጡት ቃል፤ " ያለአግባብ መሳሪያ ሲተኩሱ የነበሩና ከህግ ለማምለጥ የተደበቁ ግለሰቦችንም የገቡበት ገብተን በቁጥጥር ስር ለማዋል ስራ እየተሰራ ነው" ብለዋል።

ኮማንደሩ አክለው ፥ "ህብረተሰቡ የሚሰጠውን ማንኛውም ጥቆማ በመቀበል ቦታው ድረስ የፀጥታ አካላትን በመላክ ህግ የማስከበር ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" ያሉ ሲሆን "ህብረተሰቡ ይህን ተረድቶ ትብብሩን ሊቀጥል ይገባል" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የህገ ወጥ ተኩስ ጉዳይ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችን በእጅጉ ሰላም የነሳቸው እና ያማረራቸው ጉዳይ መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለፅ እንደነበር ይታወቃል ፤ ከጊዜ ወደጊዜ ይህ ድርጊት ይቆማል ተብሎ ቢታሰብም አሁንም ድረስ ቀጥሏል። ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት በተለያየ ጊዜ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
64.6K viewsedited  19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-28 21:57:57
#ALERT

በአንድ ቀን የ49 ዜጎች ህይወት አለፈ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት 49 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,366 የላብራቶሪ ምርመራ 799 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 780 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

በየዕለቱ በኮቪድ19 ምክንያት ህይወታቸው የሚያጡ ዜጎች ቁጥር በእጅጉ እያሻቀበ በመሆኑ መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጥንቃቄያችሁን እንድታጠናክሩ አደራ እንላለን።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
86.7K viewsedited  18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-28 17:58:04
171.4K viewsedited  14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-28 17:39:14
164.0K viewsedited  14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-28 17:21:02
160.0K viewsedited  14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ