Get Mystery Box with random crypto!

#GONDAR : በጎንደር ከህገወጥ ተኩስ ጋር በተያያዘ የከተማው ፖሊስ መሳሪያ የማስወረድ ስራ እና | TIKVAH-ETHIOPIA

#GONDAR : በጎንደር ከህገወጥ ተኩስ ጋር በተያያዘ የከተማው ፖሊስ መሳሪያ የማስወረድ ስራ እና ሰዎችን የማሰር እርምጃ እየወሰደ ነው።

ከትንላት ጀምሮ እስከ አሁን ሰአት ድረስ የጎንደር ከተማ ፖሊስ ከ50 የሚበልጥ የጦር መሳሪያ ያስወረደ ሲሆን ከህገወጥ ተኩስ ጋር በተያያዘ ከ30 በላይ ሰዎችን ማሰሩንና ፍ/ቤት በማቅረብ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ለጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

ስራው እየተሰራ የሚገኘው ከፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ አድማ ብተና፣ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ሃይል እንዲሁም ከከተማው የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ አመራሮችን ባካተት ቡድን ነው ተብሏል።

የጎንደር ከተማ ፓሊስ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ማምሻውን ለጎንደር ኮሚኒኬሽን በሰጡት ቃል፤ " ያለአግባብ መሳሪያ ሲተኩሱ የነበሩና ከህግ ለማምለጥ የተደበቁ ግለሰቦችንም የገቡበት ገብተን በቁጥጥር ስር ለማዋል ስራ እየተሰራ ነው" ብለዋል።

ኮማንደሩ አክለው ፥ "ህብረተሰቡ የሚሰጠውን ማንኛውም ጥቆማ በመቀበል ቦታው ድረስ የፀጥታ አካላትን በመላክ ህግ የማስከበር ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" ያሉ ሲሆን "ህብረተሰቡ ይህን ተረድቶ ትብብሩን ሊቀጥል ይገባል" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የህገ ወጥ ተኩስ ጉዳይ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችን በእጅጉ ሰላም የነሳቸው እና ያማረራቸው ጉዳይ መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለፅ እንደነበር ይታወቃል ፤ ከጊዜ ወደጊዜ ይህ ድርጊት ይቆማል ተብሎ ቢታሰብም አሁንም ድረስ ቀጥሏል። ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት በተለያየ ጊዜ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia