Get Mystery Box with random crypto!

#Metekel በመተከል የፀጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸው ፤ ከ194ቱ ውስጥ 56 ትም | TIKVAH-ETHIOPIA

#Metekel በመተከል የፀጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸው ፤ ከ194ቱ ውስጥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ፤ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፍረሳቸው ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው ዛሬ በአሶሳ በጀመረው 23ኛው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቀፍ ትምህርት ጉባኤ ላይ ነው።፡

በዚሁ መድረክ ላይ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ቢንያም መንገሻ እንደተናገሩት ፤ በመተከል ግጭት ትምህርት ቤቶቹ የተጎዱት በ2013 ዓ.ም ሲሆን እነዚህም የመጀመሪያ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ናቸው ብለዋል።

በፀጥታ ችግር ከተጎዱ 194 ትምህርት ቤቶች ፥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን፤ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፈራረሳቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ትምህርት ቤቶቹ 69 ሺህ ተማሪዎች የሚማሩባቸው እንደነበሩ ገልፀዋል።

የትምህርት ቢሮ ኃላፊው ፥ የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እንዲሁም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ተዘጋጅቶ እየተሠራ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia