Get Mystery Box with random crypto!

#Diredawa : ድሬዳዋ ከተማ ዛሬ አዲስ መንግስት መስርታለች። ዛሬ ከሰዓት በተካሃደው የድሬዳ | TIKVAH-ETHIOPIA

#Diredawa : ድሬዳዋ ከተማ ዛሬ አዲስ መንግስት መስርታለች።

ዛሬ ከሰዓት በተካሃደው የድሬዳዋ ከተማ አዲስ መንግስት መስረታ የከተማው ምክር ቤት አቶ ከድር ጁሃርን በሙሉ ድምፅ ከንቲባ አድርጎ ሲሾም በከንቲባው የቀረቡትን የካቤኔ አባላትንም ሹመት አፅድቋል።

ሹመታቸው በምክር ቤት የፀደቀላቸው የካቢኔ አባላት የሚከተሉት ናቸው ፦

1. ም/ከንቲባና ንግድ ቢሮ - ሀርቢ ቡህ ወርሰሜ
2. የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ/ የመንግስት ተጠሪ - ኢብራሂም ዩሱፍ
3. ፋይናንስ ቢሮ - ሱልጣን አሊይ
4. ቴክኒክና ሙያ ቢሮ - ሮቤል ጌታቸው
5. ግብርና ቢሮ - ኑረዲን አብደላ
6. ኮንስትራክሽን - ኢ/ር ጀማል ኢብራሂም
7. ጤና ጥበቃ ቢሮ - ለምለም በዛብህ
8. ፍትህ ቢሮ - አብዱሰላም አህመድ
9. መሬት ልማት ቢሮ - ሳጂድ አሊይ ሁሴን
10. ትምህርት ቢሮ - ሙሉካ መሀመድ ሁሴን
11. መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ - ኢስቂያስ ታፈሰ
12. ሴቶችና ህጻናት - ፈጡም ሙስጠፋ ሀቢብ
13. ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ - አቡበከር አዶሽ ኦልሀዬ
14. ዋናው ኦዲተር - ጫልቱ ሁሴን
15. ብዙሃን መገናኛ - አብዱሰላም መይደኔ

Credit : ድሬዳዋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia