Get Mystery Box with random crypto!

' ስራ ዝግ ሆኖ ይውላል ' ነገ መስከረም 20 የሚካሄደው ምርጫን እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮ | TIKVAH-ETHIOPIA

" ስራ ዝግ ሆኖ ይውላል "

ነገ መስከረም 20 የሚካሄደው ምርጫን እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ተከትሎ ስራ ዝግ ሆኖ እንደሚውል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።

ስራ ዝግ ሆኖ የሚውለው ፦
- በሐረሪ ክልል፣
- በሶማሌ ክልል፣
- በደ/ብ/ብ/ህ ክልል ፦
• በምእራብ ኦሞ ዞን፣
• በደቡብ ኦሞ ዞን፣
• በቤንች ሸኮ ዞን፣
• በሸካ ዞን፣
• በጌዲዮ ዞን፣
• በሃድያ ዞን፣
• በጉራጌ ዞን፣
• በጋሞ ዞን፣
• በካፋ ዞን፣
• በወላይታ ዞን ፣
• በዳውሮ ዞን፣
• በባስኬቶ ልዩ ወረዳ እና በኮንታ ልዩ ወረዳ ነው።

ምርጫ ቦርድ ዜጎች እለቱን ለድምጽ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ ከላይ በተጠቀሱት ክልሎች እና ዞኖች የሚገኙ የፌዴራል እና የክልል መንግስታዊ ተቋማት መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ስራ ዝግ እንዲያደርጉ አሳውቋል።

ቦርዱ ፥ የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የእለት ተእለት አገልግሎት ሰጪዎች (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት …ወዘተ) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ ማከናወን እንደሚችሉ ገልጾ እነዚህ ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አይጠበቅባቸውም ብሏል።

የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም በተጠቀሱት ክልሎች እና ዞኖች ዜጎች ድምጽ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና እቅዶችን እንዳይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምጽ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉም ቦርዱ አበረታቷል።

@tikvahethiopia