Get Mystery Box with random crypto!

#ማስጠንቀቂያ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ሲ | TIKVAH-ETHIOPIA

#ማስጠንቀቂያ

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ሲያበር የተገኘ በሕግ እንደሚጠየቅ አስጠንቅቋል።

ለዜጎች ሰላም መረጋገጥ እንዲሁም የቁልፍ መሰረት ልማቶችን ደህንነት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመጠበቅና ስጋቶችን ለመከላከል ሲባል ድሮኖችን ያለምንም ህጋዊ ፈቃድ ለቀረፃ መጠቀምም ሆነ ማብረር እንደማይቻል መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን በሀገሪቱ በሚካሄዱ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ህዝባዊ ሁነቶች ላይ ለቀረፃ ሲጠቀሙ እና ሲያበሩ እየተስተዋለ መሆኑን የገለፀው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እነዚህ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጉዳዩ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አውቀው ከህገ ወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ በጥብቅ አስጠንቅቋል።

ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ለቀረፃ ሲጠቀምና ሲያበር የተገኘ ማንኛውም አካል ወይም ግለሰብ በህግ ይጠየቃልም ብሏል።

Credit : የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት

@tikvahethiopia