2023-07-05 12:50:05
በአማራ ክልል ገበሬዎች የተጠየቀው የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ጥያቄ ዛሬም አልተፈታ
ንሥር ብሮድካስት
ሰኔ 28/2015
ከዚህ ጋር ተያይዞ በምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል ወረዳ አርሶ አደር የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ጥያቄ እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል። የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት አለመኖሩ በአማራ ክልል አርሶ አደሮች ዘንድ በዕየለቱ ቁጣ እየቀሰቀሰ ነው።
ማቻከል ወረዳ አርሶ አደሮችም የሚመለከተው አካል ለጥያቄያችን ምላሽ ይስጠን እያሉ ነው።
ማዳበሪያ ከነጋዴ በ300 መቶ ብር ጭማሪ እየገዛን ነው። ምርጥ ዘርም ከ1500 እስከ 2000 ብር በአየር ላይ እየገዛን እና ለከፍተኛ ኪሳራ እየተጋለጥን ነው ብለዋል።
በመሆኑም መንግሥት ለአርሶ አደሩ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል።
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube: https://www.youtube.com/@nisir/videos
FaceBook Page 1 : https://www.facebook.com/Nisirbroadcast
FaceBook Page 2: https://www.facebook.com/Nisirmereja
Telegram: https://t.me/nisirbroadcasting
Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter: https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram: https://www.instagram.com/nisirbroadcast/
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።
414 views09:50