Get Mystery Box with random crypto!

የጋምቤላ ክልል በተደጋጋሚ የሚከሰተው የጸጥታ ችግር አሳሳቢ መሆኑን ኢሰመኮ አስታወቀ | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

የጋምቤላ ክልል በተደጋጋሚ የሚከሰተው የጸጥታ ችግር አሳሳቢ መሆኑን ኢሰመኮ አስታወቀ

ንሥር ብሮድካስት
ሐምሌ 17/2015

በጋምቤላ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ በነዋሪዎች ላይ ያደረሰው ከፍተኛ ጉዳት እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፤ የመንግሥትን ተጨማሪ ትኩረት የሚሻ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳስቧል።

በጸጥታው ችግር ምክንያት ገና ወደ አካባቢዎቹ በአካል ደርሶ ምርመራ ለማድረግ አለመቻሉን የገለጸው ኮሚሽኑ፤ ነገር ግን ነዋሪዎች በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ መንደሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መውደማቸውን ነዋሪዎች ገልጸውልኛል ብሏል።

በክልሉ በተደጋጋሚ ከጎረቤት አገር ደቡብ ሱዳን በሚመጡ ታጣቂ ቡድኖች በሚደርሱ ጥቃቶች እንዲሁም፤ አልፎ አልፎ በክልሉ በሚኖሩ ብሔሮች መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ከፍተኛ ጉዳት የሚደርስ መሆኑም በመግለጽ፤ ክልሉ ወደ 350 ሺሕ የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን በስምንት የተለያዩ ካምፖች እንደሚያስተናግድም አስታውሷል።
-------------------------------------------------------------
ወቅታዊ፤ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

Youtube :-https://www.youtube.com/channel UC9yOQepDMiEq7xHUodXo0kQ

FaceBook Page 1 :    https://www.facebook.com/Nisirbroadcast

FaceBook Page 2:  https://www.facebook.com/Nisirmereja 
 
Telegram:    https://t.me/nisirbroadcasting

Website: https://nisirbroadcasting.com
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።