Get Mystery Box with random crypto!

እስራኤል የኢትዮጵያ መንግሥት የዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታን እንዲያስጠብቅ አሳሰበች | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

እስራኤል የኢትዮጵያ መንግሥት የዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታን እንዲያስጠብቅ አሳሰበች

ንሥር ብሮድካስት
ሰኔ 28/2015

በግብፅ ኮፕቲክና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መካከል አለመግባባት የሚፈጥረው የዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታ፤ የኢትዮጵያ ሆኖ እንዲዘልቅ እንደሚፈልግ የእስራኤል መንግሥት ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ኢየሩሳሌም የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ንብረት የሆነውን የዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታ ማስጠበቅ አለበት ሲሉ፤ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ተናግረዋል፡፡

የእስራኤል መንግሥት የዴር ሡልጣን ገዳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይዞታ ነው ብሎ እንደሚያምንም አምባሳደሩ ገልጸዋል ሲል አዲስ ማለዳ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube: https://www.youtube.com/@nisir/videos

FaceBook Page 1 :    https://www.facebook.com/Nisirbroadcast

FaceBook Page 2:  https://www.facebook.com/Nisirmereja      

Telegram:    https://t.me/nisirbroadcasting

Website: https://nisirbroadcasting.com

Twitter:   https://twitter.com/NISIRInternati1

Instagram:  https://www.instagram.com/nisirbroadcast/
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።