ክፍል አንድ
↝ የትንሹ ዚና አደገኝነት↜
↝ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
«አንድ ሰው ወደ ባዳ (እንግዳ) ሴት በሚመለከትበት ጊዜ በዓይኖቹ ዝሙትን
ይፈጽማል፡፡ የጆሮዎች ዝሙት ወሲባዊ ውይይቶችን ማዳመጥ ነው፡፡ የምላስ ዝሙት ስለወሲብ ማውራት ነው:: የእጅ ዝሙት ያን ያልተፈቀደን መንካት ነው፡፡ እንዲሁም የእግር ዝሙት ወደ አጅነቢ ሴት መጓዝ ነው:: ልብ ዝሙተኝነትን በኃይለኛው ይመኛል፤ እንዲሁም
የወሲብ አካላት ድርጊቱን ያጽድቃሉ ወይም ይቃረናሉ፡፡» (ቡኻሪና ሙስሊም)
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ሙእሚኖችን ከትንሹ የዓይን፣ የጆሮ፣ የምላስ፣ የእጅ፣ የእግርና የኸልዋ (ከሴት ጋር መገለል) ዚናዎች አስጠንቅቀዋል፡፡ ምክንያቱም ዚና በኢስላም ውስጥ ጸያፍ ድርጊትና መንገድነቱም የከፋ ነውና፡፡ ከዚህም የተነሳ ማንኛውም ወደዚና የሚመራ መንገድ ሁሉ ሐራም እንደሆነ በግልጽ ታውጇል፡፡ በሌላ አነጋገር ኢስላም ዚናን ከነመዳረሻ መንገዶቹ ሐራም አድርጓል። ምክንያቱም መለኮታዊው ትዕዛዝ «ዝሙትን አትቅረቡ ... መንገድነቱም የከፋ ነው!» ይላልና፡፡ ትንሹ ዚና ከትንንሽ ኃጢአቶች መካከል እጅግ አደገኛው ነው፡፡ ይህነኑ አስመልክቶ ታላቁ ዓሊም ዐብዱሏህ ቢን ዐብ-ባስ (ረድየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ ብለዋል፡-
«እኔ እቡ ሁረይራ (ረድየላሁ ዐንሁማ) ከነብዩ (ﷺ) ካውሩት ይበልጥ የከበዱ (ትንንሽ ኃጢአቶች) የሚመስሉ ነገሮችን አላየሁም አሉና (ከዚያም እንዲህ ሲሉ ነብያዊውን ንግግር አስከተሉት፡-)
አላህ አዳም ልጆች ላይ ያንን እነርሱ በርግጠኝነት የሚፈጽሙትን የዝሙት ድርሻቸውን ጽፎላቸዋል፡፡
የዓይን ዝሙት ዕይታ ነው (ሐራም ነገሮችን መመልከት)፣ የምላስ ዝሙት ንግግር ነው፤ የልብ ዝሙት (የውስጥ ሰውነት ዚናን) ይመኛል፤ ይፈልጋልም፤ እንዲሁም የግል አካላት ያጸድቃሉ፤ አልያም ውድቅ ያደርጋሉ፡፡»
(ሰሒሕ አል-ቡኻሪ)
①/ የዓይን ዚና አደገኛነት ⇩
«እርሱ ያ ዓይኖቹን ያልተጠቀመበት፣ ጆሮዎቹንም ሊጠቀምበት እይቻልም፡፡»
(ታላቁ ሊቅ ኢማም ኢብኑል ቀይም)
↝ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
«(በምኞት የተሞላ) ዕይታ የሸይጧን ቀስቶች (ፍላፃዎች) የተመረዘ ቀስት ነው፡፡ እርሱ ያ ለአላህ ሲል የሴትን ውበት ከመመልከት ዕይታውን ዝቅ የሚያደርግ ሰው አላህ በርሱ (በሰውየው) ልብ ውስጥ እርሱን እስከሚገናኘው ቀን ድረስ ጥፍጥናን (ለዛን) ያደርግለታል፡፡» (አል-ሓኪም)
⇨ ዕይታን በዕይታ ላይ እከታትለህ አትልቀቅ (ዓይኖትህን እከታትለህ አትወርውራቸው)፤ የመጀመሪያዋ ያንተ ናት፤ ሁለተኛዋ ግን ያንተ አይደለችም፡፡»
②/ የምላስ ዚና አደገኛነት ⇩
ሁሉም የሰውነት ክፍሎች እያንዳንዱ አዲስ ቀን በመጣ ቁጥር ምላስን ይገስፃሉ፤ ያስጠነቅቁታልም፤ አላህን እንዲፈራ፡፡ ዕጣ ፋንታቸው የሚወሰነው በምላስ ላይ ተመሥርቶ መሆኑን በመግለጽ ምላስ አላህን እንዲፈራ ይገስጹታል፡፡
↝ይህንኑ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ በማለት ገልጸዋል፡- «በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ሁሉም የአካል ክፍሎች አላህን ፍራ ዕጣ ፋንታችን የሚወሰነው ባንተ ሁኔታ ላይ ነውና እንተ ከተስተካከልክ እኛም እንስተካከላለን አንተ ከጠመምክ እኛም እንጠማለን በማለት ምላስን ይገስፃሉ፤ ያስጠነቅቃሉም፡፡» (ቲርሚዚ)
ለመንቀሳቀስ እጅግ ቀላሉ የሰው ልጅ አካል ምላስ ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ ልቅ ከሆነ ብዙ ወለምታ የሚያገጥመው የሰውነት አካልም ቢኖር ይኸው ቁራሽ ሥጋ (ምላስ) ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ለባለቤቱ እጅጉን ጎጂው ነገርም ምላስ ይሆናል፡፡ ወደ ዚናም ስንመጣ ብዙውን ጊዜ ዚና በአንዴ ስለማይከሰት በጅማሮውና በፍፃሜው መካከል የምላስ አስተዋጽኦ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ስለዚህ ከሞላ ጎደል የትልቁን ዚና መንገድ የሚያመቻቸው ምላስ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
የምላስ ወለምታና መዘዝ ዝሙት ላይ ይጥላል፡፡ ለዚህም ነው መልዕክተኛው (ﷺ) ምላሱንና ብልቱን ከሐራም ነገር ለሚቆጣጠር ሰው ጀነት ሊገባ ዘንዳ ዋስትናን የሰጡት፡፡
ይ ቀ ጥ ላ ል
ክፍል ሁለት⇨ ይቀጥላል
ያሲን ኑሩ ኦፊሺያል
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia