Get Mystery Box with random crypto!

የሀድያ ሙስሊሞችን የሚወክለው ተቋም ማነው? .. ከአመት በፊት በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ውስጥ ያ | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የሀድያ ሙስሊሞችን የሚወክለው ተቋም ማነው?
..
ከአመት በፊት በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ውስጥ ያለው ጥምቀተባህር በስማችን የይዞታ ማረጋገጫ ይሰጠን በሚል ከኦርቶዶክስ ምዕመናን ጋር ዞኑ እሰጣገባ ገብቶ ነበር። ቦታው የህዝብ መገልገያ ስለሆነ በአመት አንዴ ቦታው ላይ ስለሚከበርበት ብቻ ተብሎ ለአንድ እምነት ይዞታ አልሰጥም ብሎ ተሟገተ። በተቃራኒው ወገን በኩል ጉዳዩን በጥንካሬ ይዞ የታገለው የከተማው አልያም የዞን ወይንም የክልሉ የቤተ ክህነት አደረጃጀት ብቻ አልነበረም። በጉዳዩ ላይ ግንባር ቀደም ትግል ያደረገው ላዕላይ ስልጣን ያለው ሲኖዶሱ እራሱ ነበር። ዞኑ ቦታውን አልሰጥም ብሎ በግትርነት ሲቀጥልም ጥምቀት በዞኑ እንዳይከበር ከማዘዝ ጀምሮ ጠንካራ መልዕክቶችን የሚመለከታቸው አካላት ዘንድ በመቅረብ የታገሉት በሲኖዶሱ የተሾሙ የበላይ አባቶች ናቸው። ልብ በሉ ምዕመን እንዳያመልክ ተደብድቦ አልያም ታስሮ አይደለም፥ ቦታ ይሰጥ ለሚለው ጥያቄ ብቻ ነው።
...
የሀድያ ሙስሊሞች ላለፉት አመታት አይደለም የማምለኪያ ቦታ ሊያገኙ ይቅርና ወቅፍ ባደረጉት የግል ቤት እንኳን እንዳይሰግዱ ወቅፍ ያደረጉትን የ90 አመት ሽማግሌ ከማሰር ጀምሮ ምዕመኑን እስከመደብደብ ያልተሰራ ግፍ አልነበረም። ይህንን ግፍ ጉዳይ ብሎ የሚከታተል የሙስሊም ተቋም ባለመኖሩ ተራ የወረዳ አመራር "አልሐምዱሊላህ" ብላችኃል ብሎ ወጣቱን የሚደበድብበት ድፍረትና ንቀት ውስጥ ተገብቷል። ህገ-መንግስታዊ መብታቸው ለሆነው ዳዕዋ ሳይቀር ጉቦ ካልሰጡ ዳዒዎችን አምጥተው ማስተማር የማይችሉበት አፈና ውስጥ አሳልፈዋል። 50 ሺ እና 100 ሺ ካሬ መሬት እያነሳ ነብይ ነን ለሚሉ ሰዎች የሚሰጡ የዞን አመራሮች ለሙስሊሞች ግን ለምን በገዛ መሬታችሁ ሰገዳችሁ ብለው ዱላ የያዘ ፖሊስ ልከው ሴትና ህፃናትን ሳይቀር ያስደበድባሉ።
...
ይህ ጉዳይ ግድ የማይሰጠን ከሆነ ከቶ የትኛው ጉዳይ ነው እንደ ኡማ የሚያስጨንቀን? የእነዚህ ህዝቦች የዕለት ተዕለት ስቃይ ለውግዘት እንኳን መጅሊሱን ግድ ካልሰጠው ስለየቱ የገዘፈ ጉዳይ ሊታገልልን ነው? መንጋው ሲበላ ግድ የማይሰጠው እረኛ እንዴት ተብሎ መልካም እረኛ ይሆናል? በዚህ ዙሪያ ድምጽ የሚሆንልንና መንገዱን ቃኝቶ መፍትሄ የሚፈልግልን ተቋም እንዲመጣ ከታገልንም በኃላ ጩኸታችን እንደድሮው ከፌስቡክ አለመዝለሉ ልብ ይሰብራል።
...
የሀድያ ወገኖቻችን፥ አሏህ ከናንተ ጋር ይሁን..!

Abdurehim ahmed



https://t.me/fethmedi
https://t.me/fethmedi
https://t.me/fethmedi