Get Mystery Box with random crypto!

የዓለም  አቀፉ ሙስሊሞች ሊግና የአወልያ እርዳታና ልማት ድርጅት ጋር አብረዉ ለመስራት ተስማሙ። | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የዓለም  አቀፉ ሙስሊሞች ሊግና የአወልያ እርዳታና ልማት ድርጅት ጋር አብረዉ ለመስራት ተስማሙ።


ጥር 2/2015 ማክሰ ኞ

የዓለም  አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ  رابطة العالم الاسلامي በአውሮፖ የአሜሪካ ዋና ዳይሬክተር  እና በሊጉ የዋና ፀሐፊው  የዶክተር ሙሐመድ  አብዱል ከሪም አል ጊሳ  አማካሪ በሆኑት በዶክተር  አብዱል አዚዝ ሰርሃን የተመራውን  ልዑክ በዛሬው እለት የአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅትን ጎበኙ።

የሙስሊም ወርልድ ሊግ ልዑክ አወሊያ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። በዉይይቱ ፕሮግራም ላይ
አወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ጀማል ሙሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እንዲሁም በድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰይድ አስማረ ራቢጣ ለአወሊያ የነበረውን ታሪካዊ አበርክቶ ከምስጋና ጋር አቅርበዋል። አወሊያ ከመቸውም በላይ ራቢጣን እንደሚፈልግ በአጽንኦት ገልጸዋል።

የዓለም  አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ  رابطة العالم الاسلامي ቀድሞ ያስተዳድረዉ ወደ ነበረው አወሊያ ተቋም በግፍ ከተባረረ ከ12 አመት በኋላ ዛሬ ተመልሶ ጉበኝት አድርጓል።

የቀድሞ መጅሊሶች የድጋፍ ደብዳቤ ለመጻፍና ሊጉ ድጋፍ እንዲያደርግ ፍቃደኛ ባለመሆናቸዉ በርካታ ነገሮች ተሰናክለው ቆይተዋል።

በእነ ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የሚመራዉ የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም አመራሮች በአካል ሄደዉ በተደረገላቸዉ ግብዣ መሠረት የልዑካን ቡድኑ ወደ ሚወዷት አወሊያ ለመምጣት ችለዋል። ለዚህም ድጋፍ ጠቅላይ ምክር ቤቱን እጅግ እናመሰግናለን።

Mujib amino



https://t.me/fethmedi
https://t.me/fethmedi
https://t.me/fethmedi