Get Mystery Box with random crypto!

ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fethmedia — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fethmedia — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የሰርጥ አድራሻ: @fethmedia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-01-06 19:38:08 #ኪታቡ አቂደቱ አህሊ ሱነቲ ወልጀመዓቲ
#በፈትህ አባቦራ መስጂድ
#ዘወትር ረቡዕ እና ጁመዓ ከመግሪብ- ዒሻ #በኡስታዝ ካሚል ጣሃ   ደርስ በድምፅ ክፍል #9 መከታተልና መቅራት ትችላላችሁ። #እንዳያመልጥዎ

https://t.me/fethmedia
137 viewsedited  16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 19:36:03
ዛሬም ፂዎናዊያን ከማይበገሩት የካፈር ቃዱም ነዋሪዋች ጋር የተፋጠጡ ቢሆኑም ነገር ነገር ግን አይናቸዉን ቢያወጡት የማይመለሱት የዌስት ባንክ መንደር ነዋሪዋች መክተዉ መልሰዎቸዋል ከዚህ ቀደም ስለ ካፈር ቃደም ጀግንነት በዚሁ ቻናል ተጠቅሷል።
ፓለስታይን ዛሬ

Palestine qudes


https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
126 viewsedited  16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 21:34:42 በጉራጌ ዞን በተለይም እኖረ ወረዳና ጉንችሬ ከተማ ላይ ግልፅ የሆነ ሙስሊም የማጽፋት ዘመቻ በዞኑና በወረዳው መዋቅር እየተፈጸመ ይገኛል። ኒቃብ የለበሱ ሙስሊም ተማሪዎች ትምህርት መማር የለባቸው በሚል ሴራ የተነሳው ይህ የጽንፈኝነት ጥግ፤ ከፊሉን ሙስሊም ተማሪና ወላጅ በማሰር፣ ከፊሉን በማሳደድ ሙስሊም ያልሆኑ ነዋሪዎች ብቻ እንዲማሩ ተደርጓል። የ16 አመት ኒቃብ ለባሽ እህታችን በጸጥታ ኃይሎች እየተረገጠች ለእስር መዳረጓን ሰምተናል።


በአጭሩ ሰሞኑን በጉራጌ እየተደረገ ካለው ጭቆና የታዘብኩት፤ ጉራጌ ማለት ከጎጃምና ጎንደር ሙስሊም ጠልና አሸባሪ ኃይል የባሰ የአጼው ርዝራዥ ያለበት መሆኑን ነው። ይህ ጽንፈኛ ሙስሊም ጠል ቡድን ለዘመናት ሙስሊሙን የስልጤ ማኅበረሰብ ሲጨቁን የነበረ ነው መባሉ፣ ቀቤናን፣ ማረቆን፣ ወለኔንና ሌሎችንም ሙስሊሞች እየጨቆኑ ያሉ መሆናቸውን በተግባር አሳይተዋል። ሙስሊም የሆናችሁ የጉራጌ ተወላጆች ካላችሁ ከነዚህ የአጼው ርዝራዦች ራሳችሁን አግልሉ። ከሌሎች ሙስሊም ጎረቤቶቻችሁ ጋር አሊያንስ ፍጠሩ። ጉራጌ ክልል ይሁን እያላችሁ ከነርሱ ጋር አትጃጃሉ። እንኳን ክልል ሆነው ዞንም ሆነው ጭቆናቸውን በተጨባጭ እንደምትመለከቱት ነው። ጽንፈኛው ጉራጌ እንኳን ክልል መሆን ቀበሌ መሆንም አይገባው።

አንዳንድ የዋሆች «ይሄ እየሆነ ያለው የክልልነት ጥያቄውን ለማኮላሸት ነው!» እያላችሁ አትጃጃሉ።
እያጠቃችሁ ያለው ጽንፈኛው ነዋሪው ነው። ወቅቱን ጠብቆ እየወጋችሁና እያስወጋችሁ ነው። አብረዋችሁ ቢሆኑማ አይማሩም ከማለት ይልቅ መንግስት ሙስሊሞቹ አይማሩም ቢል እንኳ እነርሱ ሳይማሩ አንማርም ብለው ከጎናችሁ ይሆኑ ነበር። እነርሱ ግን መንግስት ኒቃብ ለብሶ መማር ሲፈቅድ የሞኣ አንበሳ መስቀል ያለበትን ቲበርትና ነጠላ ለብሰን ካልገባን አሉና ያም ተፈቀደላቸው። በዚያ አላማቸው ስላልተሳካ ወደ መተታቸውና ተደራጅተው ሙስሊሞችን ወደ መደብደብ፣ ት/ቤት ወደማቃጠልና መሰል የለየለት ውንብድና አመሩ። ታዲያ እንደት ነው ከነዚህ የሰው እንስሶች ጋር አብራችሁ ስለ ክልልነት የምትታገሉት?


ከዛሬ ጀምሮ ብሄሩን ከእምነቱ አስበልጦ ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች ይልቅ ስለ ክልልነቱ የሚያወራ ሙስሊም ተብዬ የጉራጌ ተወላጅ ካገኘሁ በብሎክ ወገብ ዛላውን ብዬ ነው የምገላግለው። ስትፈልግ ሂደደ አሽቃብጥላቸው፣ እግራቸውን እጠብላቸው፣ አሽከር ሆናቸው፣ እንደፈለጉ ይጋልቡህ፣ ግን መቼም አይወዱህም። የትግሉ ጊዜ ከፊት ያሰልፉህና የጥቅሙ ጊዜ እንኳን ሊያጋሩህ ጭራሽ መብትህንም ይረግጡሃል። ከነዚህ ጋር ምንም ግንኙነት አይኖርህም። እነዚህን ታግለህ ራቁታቸውን አስቀርና እንደ ጎረቤትህ ስልጤዎች ነፃነትህን እወጅ። መንት ያለ ትግል አልተገኘም። በፈሊጥ ካልገባቸው በፍልጥ እንዲገባቸው ማድረግ ነው። በነርሱ ተርመጥምጬ ልሙት እንደ በአላህ! አላህ ወገባቸውን ይስበረውና! እንደት ሙስሊሙን አስረውና አሰድደው ክርስቲያኑ ብቻ ይማራል? የጉራጌ ዞን ኃይማኖታዊ መንግስት ነው እንበል? በዞኑ የመንግስት መዋቅር ፈርሷል እንደ? ህግ የለም እንደ? በህግ ሽፋን የሚፈጸመው ጸረ ሙስሊም ዘመቻ እስከ መቼ ነው የሚቀጥለው? ኧረ! የፍትሕ ያለህ!

ሙራድ ታደሰ



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
57 views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 20:21:33 #ኪታቡ አቂደቱ አህሊ ሱነቲ ወልጀመዓቲ
#በፈትህ አባቦራ መስጂድ
#ዘወትር ረቡዕ እና ጁመዓ ከመግሪብ- ዒሻ #በኡስታዝ ካሚል ጣሃ   ደርስ በድምፅ ክፍል #8 መከታተልና መቅራት ትችላላችሁ። #እንዳያመልጥዎ

https://t.me/fethmedia
71 viewsedited  17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 19:19:53 ኑር መስጂድን የፊታችን እሁድ እንረከባለን!

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኑር መስጂድን የፊታችን እሁድ ይረከባል።


ታህሳስ 26/1015 ረቡዕ

በዛሬዉ እለት የሁከትና የብጥብጥ ጠንሳሹ አቶ መንሱር ዘይኑ አብዱልቃድር በመስጂዱ ቅጥር ግቢ ባደራጃቸዉ አካላት በስለት የታገዘ እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን በሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል።

በትላንትናው እለትም በተመሳሳይ መልኩ ባደራጃቸው ወጣቶች ሁኩትና ብጥብጥብ ለማስነሳት መጣሩ ይታወሳል::

እንደሁልጊዜዉም ምዕመናን ተ ስፋ ለቆረጡ ዱርዬዎች መልስ ከመስጠት ይልቅ በሆደ ሰፊነት አሳልፏል።

ይህን ጉዳይ አልባት ለመስጠትም አቶ መንሱር
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ፀጥታ ዘርፍ ቢሮ እንዲገኙ የተደረገ ሲሆን፤ የአዲስ አበባ ከተማ ጠቅላይ ም/ቤ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ከተደረገ ቡኃላ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከዚህ ቀደም በፃፈዉ ደብዳቤ መሰረት አቶ መንሱር ከኑር መስጂድ አስተዳደርነት መሰናበቱ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት የፊታችን እሁድ ታህሳስ 30/2015 እሁድ ከጠዋቱ 3:00 ላይ አቶ መንሱር ዘይኑ በተገኘበት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኑር መስጂዱን ይረከባል።

አቶ መንሱርን ጨምሮ ጭፋራዎቹ የርክክቡ  ቃል ጉባዔው በተያዘዉ ሰነድ ላይ ተስማምተዉ ፈርመዋል። የፀጥታ ዘርፍ በተገኘበትም እለተ እሁድ ርክክቡ ይፈጸማል።

Mujib amino



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
85 viewsedited  16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 19:02:29
ታህሳስ 30/2015 የኑር መስጂድ አስተዳደር ርክክብ ይካሄዳል!!!

በደብዳቤ ቁጥር 0044/15 በቀን 20/3/2015 የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ሐጂ መንሱር ዘይኑን ከኑር መስጂድ አስተዳደርነት ያሰናበተ መሆኑ ይታወቃል።

ሆኖም በአስተዳደሩ በኩል ለማስረከብ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ርክክቡ ሳይፈፀም ቆይቷል።በዚህም የተነሳ ጉዳዩ የሁከትና ብጥብጥ ምክንያት ሆኗል።

በመሆን በዛሬው እለት የከተማዋ የሰላምና ፀጥታ አካላት ባሉበት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች አመራሮች ከሐጂ መንሱር ዘይኑ ጋር ባደረግነው ህግ የማስከበር ውይይት ርክክቡ ታህሳስ 30/2015 ቀን የከተማውና የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ፣የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት እንዲሁም ሐጂ መንሱር በተገኙበት እንዲከናወን በተፈረመ ቃለ ጉባኤ ስምምነት ላይ ተደርሶል!!!



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
79 viewsedited  16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 17:21:25
76 views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 17:21:18 "ፈገግ እያሉ በናፍቆት እይታ ውስጥ ሆነው ውስጤን ብርሃን ይሰማኛል! ነፃነት ይሰማኛል! የበራሪ ወፍ ያህል ነፃነት ይሰማኛል…በህይወት ዘመኔ ሁለት ጊዜ ምንም ገንዘብ የሌለው ሰው ሆኜ አውቃለው:: በፊት ላይ የድህነትን ስሜት እና ሁኔታ በደንብ በህይወቴ አውቀዋለው:: ያሁኑ ግን በፍላጎቴ እና በምርጫዬ ነው:: ምንም ለራሴ ባይኖረኝም እጅግ መረጋጋት፣ የዐዕምሮ ሰላም እና ደስታ ይሰማኛል::ሀብት ሁሉ የአላህ ነው:: የእሱን ሀብት እንድንጠብቅ ነው የተሰጠን:: አሁን ላይ ጌታዬ አላህ ሲጠራኝ ያለ ምንም እክል ጥሪውን መመለስ እችላለሁ! ይህ ታዲያ እንዴት ያለ እፎይታ እና እረፍት የሚሰጥ ነው!!በማለት አስደናቂ ምላሻቸውን ሰጥተዋል::

በእርግጥም ለጋሽ መሆን ይከፍላል!!

አላህ ከችሮታው አሁንም ይጨምርላቸው

ለኛም የመለገስን ልብ ይወፍቀን

(ኡስታዝ አቡበከር አህመድ)



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
68 views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 17:21:18 በእርግጥም ለጋሽ መሆን ይከፍላል!!

~ ደስታን በልግስና ውስጥ ያገኙት የአለማችን ቁጥር አንድ በጎ አድራጊ፣

#Ethiopia | ሼይኽ ሱለይማን አልራጅሂ ይባላሉ:: ሳዑዲ አረቢያ ካፈራቻቸው ቢኒየነሮች መካከል አንዱ ናቸው:: ከንጉሳውያን ቤተሰብ ሳይሆኑ ቢሊየነር መሆን የቻሉ ሰው ናቸው:: በአለም ግዙፉን አልራጅሂ ኢስላማዊ ባንክ መመስረት ችለዋል::

በህይወታቸው ያጋጠማቸውን አንድ አስተማሪ ክስትተት እንዲህ ሲሉ ያካፍሉናል -

"በልጅነቴ እጅግ በድህነት ውስጥ ነው ያደኩት:: ቤተሰቦቼ ድሆች ነበሩ:: በአንድ ወቅት ትምህርት ቤት ተማሪ እያለው ትምህርት ቤቱ የመዝናኛ ጉዞ ስላዘጋጀ በዚህ የሽርሽር ጉዞ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ 1ሪያል ማዋጣት እንደሚጠበቅበት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አስታወቀ:: እኔም በዚህ ጉዞ ላይ ለመሳተፍ እጅግ ስለጓጓው ለወላጆቼ አንድ ሪያል እንዲሰጡኝ እያለቀስኩኝ ጠየኳቸው:: ነገር ግን ወላጆቼ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ህይወት የሚኖሩ ሚስኪኖች ስለነበሩ ይህን አንድ ሪያል ስለሌላቸው ሊሰጡኝ አልቻሉም:: የጉዞ ቀናት መቃረቡን ተከትሎ አንድ ሪያሉን የሚሰጠኝ በማጣቴ እጅግ በጣም አለቀስኩኝ ፤አዘንኩኝ::

ለጉዞ አንድ ቀን ሲቀረው በትምህርት ቤቱ የወሰድነው ፈተና ውጤት ደርሶ ስለነበር የፈተና ውጤታችንን ስንቀበል ከሌሎች ተማሪዎች የላቀ ውጤት በማምጣቴ ፍልስጤማዊ የሆነው መምህራችን ተደስቶብኝ በተማሪዎች ፊት አስጨብጭቦ ውጤቴን ሰጠኝ:: ለማበረታታም አንድ ሪያል በሽልማት መልኩ አበረከተልኝ::

ለጉዞ መዋጮ የሚያስፈልገኝን አንድ ሪያል በሽልማት መልኩ በማግኘቴ እጅግ በጣም ተደሰትኩኝ:: ያንን የተሸለምኩትን ኣንድ ሪያልም ለትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በፍጥነት ሄጄ በመስጠት ብዙ በጓጓሁለት ጉዞ ላይ መሳተፍ ቻልኩኝ::

ለቀናት ሳነባ የነበረው እንባ በደስታ ተቀየረልኝ:: የቀናት ለቅሶዬ በዛች አንድ ሪያል ሽልማት የተነሳ ለረጅም ጊዜያት ውስጤ በቀረ ደስታ ተለወጠልኝ::

ጊዜያት ነጎዱ:: እኔም ትምህርቴን አጠናቀኩኝ:: ጠንካራ እና ታታሪ ሆኜም በስራ ዘርፍ ላይ ተሰማራው:: የአላህ ፀጋ ብዙ ነውና ስራዬን በረካ አደረገልኝ:: ፀጋውንም በኔ ላይ አንቧቧልኝ:: ከትንሽ ስራ ተነስቼ በሳኡዲ አረቢያ የመጀመሪያው የሸሪዓ መር ባንክ በመመስረት በመላው ሳኡዲ አረቢያ ቅርንጫፎች በዙልኝ::

በአንድ ወቅት በልጅነቴ ተማሪ እያለው አንድ ሪያል የሰጠኝ መምህሬን በማስታወስ በወቅቱ የሰጠኝ አንድ ሪያል ሽልማት ነው ወይስ እርዳታ ? በሚል ከእራሴ ጋር ሙግት ውስጥ ገባው:: እራሴን ደጋግሜ ጠየኩኝ:: ግን ፈፅሞ መልስ ላገኝለት አልቻልኩም::

መምህሩ ያንን አንድ ሪያል የሰጠኝ ምንም አስቦ ቢሆን ለእኔ ግን በወቅቱ የነበረብኝን ትልቅ ችግሬን ቀርፎ አስደስቶኛል ፤ ያንን የደስታ ስሜት ደግሞ ከእኔ ውጪ ማንም ሊረዳው አይችልም ስል ለራሴ ነገርኩት::

ውስጤ ለሚመላለሰው ትዝታ እና ጥያቄ ምላሽ ሊሆነኝ የሚችለው ይህን መምህር ካለበት አፈላልጌ አግኝቼው ስጠይቀው ነው በሚል ወደ ቀድሞ ትምህርት ቤቴ በመሄድ ፍልስጤማዊ መምህሬን ማፈላለግ ጀመርኩኝ::
በአላህ እገዛ መምህሬ ያለበትን ቦታ አፈላልጌ ማግኘት ቻልኩኝ:: እሱን ለማግኘትም ቀድሜ ተዘጋጀሁና ወዳለበት ስፍራ አቀናው::

ፍልስጤማዊው መምህሬ በጡረታ ላይ ሆኖ፣ እጅግ በድህነት እና በችግር ላይ ሆኖ አገኘውት::

የእርሱ ተማሪ እንደነበርኩኝ በማብራራት እንዲያስታውሰኝ አደረኩት ::

የተከበርከው ውዱ መምህሬ ሆይ ፣እኔ እኮ ለረጅም አመታት የቆየ ያንተ ባለእዳ ነኝ አልኩት::

አንድ ደሃ ሰው ምን የሚያበድረው ነገር ኖሮት ነው የማበድርህ ሲል ተገርሞ ጠየቀኝ::

እኔም ተማሪ እያለው በውጤቴ ምክንያት የሰጠኝን አንድ ሪያል አስታወስኩት::

መምህሬም :- ክስተቱን በማስታወስ እየሳቀ ባለእዳ ነኝ ያልከኝ ታዲያ አሁን ያቺን አንድ ሪያል ልትከፍለኝ ነው ? በማለት ተገርሞ እየሳቀ ጠየቀኝ::

እኔም አዎ ውዱ መምህሬ በማለት መለስኩለት::

ወደ መኪናዬ እንዲገባ በማድረግ እጅግ ዘመናዊ መኪና በግቢው ውስጥ የቆመበት ግዙፍ ዘመናዊ ቪላ ቤት ውስጥ ይዜው ገባው::

መምህሬ ሆይ ተማሪ እያለው ለሰጠኸኝ አንድ ሪያል ምላሽ ባይመጥንም፤ ይሄ ግዙፍ ቪላ እና መኪና ላንተ ይሆን ዘንድ ያዘጋጀሁት ነው፤ በህይወት ዘመንህም የሚበቃህን ያህል ገንዘብ እኔ ዘንድ ተዘጋጅቶልሀል ብዬ ነገርኩት::

መምህሬ እጅግ በመደንገጥ ይሄ ፈፅሞ ለእኔ አይገባም፣ ይህ በጣም ከልክ ያለፈ ብዙ ነው በማለት አይኑ በእንባ ተሞልቶ መቀበል እንደሚከብደው ነገረኝ:::

መምህሬ ሆይ በወቅቱ አንድ ሪያል ስትሰጠኝ የነበረኝ ደስታ ዛሬ አንተ ይህን ቪላ እና መኪና ስታገኝ ከተሰማህ ደስታ በላይ ነው:: የዛኔ የነበረኝ የልጅነት ደስታ እና ሀሴት ዛሬም ድረስ አይረሳኝም በማለት ለመምህሬ ስጦታዬን አበረከትኩለት::ይላሉ

በመጨረሻም ሼይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ ምክር ሲመክሩ

"ምን ጊዜም ለሌሎች ደስታን ፍጠር፣ የሌሎችን ጭንቀት አሶግድ ፣ ምንዳህን እጅግ ከሰጪው ፣ከለጋሹ እና ከደጉ ጌታ ጠብቅ ይላሉ'

ለመረጃ ያህል

ሼይኽ ሱለይማን አልራጅሂ ያላቸውን ሀብት ግማሹን ለልጆቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ግማሹን ደግሞ ለበጎ አድራጎት አበርክተዋል::

በአለማችን ታሪክ ግዙፉ የተባለለትን እና በአለም ድንቃ ድንቅ መዘገብ ላይ ሊሰፍር የቻለ ለበጎ አድራጎት አገልግሎት የሚውል በሳኡዲ አረቢያ በቀሲም ግዛት የሚገኘውን 5466 ሄክታር ስፋት ያለው የእርሻ ማሳቸውን፤ ይህም የእርሻ ማሳ በአመት 10ሺህ ቶን የቴምር ፍሬ የሚሰጥ እና በውስጡም 45 አይነት የተለያዩ የተምር ፍሬዎችን የያዘ፣ 200,000 የሚሆን የተምር ዛፍ ለበጎ አድራጎት ይውል ዘንድ ወቅፍ ማድረግ የቻሉ ሰው ናቸው::

ሸይኽ ሱለይማን አራጅሂ ለዳእዋና ለበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ቋሚ ድጋፍ እንዲሆን ወቅፍ ያደረጉት ካፒታል አሁን ላይ 60 ቢሊዮን ሪያል ደርሷል። ይህ በአለማችን እስካሁን ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ወቅፍ ነው::

ሼይኹ ወቅፍ ካደረጉት የተምር እርሻ የሚገኘው የቴምር ምርት ተሽጦም ገቢው ለበጎ አድራጎት ማህበራት የሚከፋፈል ሲሆን ቀሪው ተምርም ለሁለቱ ቅዱሳን መስጂዶች መካ እና መዲና ለሚገኙት ሀረሞች የረመዳን ኢፍጣር ፕሮግራም አገልግሎት ይውል ዘንድ ለምዕመናን በነፃ ይከፋፈላል::

በሳዑዲ አረቢያ ባሉ ከተሞች ላይ በሼይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ እና ቤተሰባቸው አማካኝነት መስጂድ እና መድረሳ ያልተገነባበት ከተማ ማግኘት ያዳግታል:: በሁሉም ቦታዎች ላይ መስጂዶችን አስገንብተዋል::

በስራቸው ላለው ሰራተኞቻቸውም ደሞዛቸውን ወሩ ከመጠናቀቁ በፊት በመክፈል ይታወቃሉ::

ሽይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ በአንድ ወቅት ቃለመጠይቅ ሲደረግላቸው

ግማሹን ሀብታችሁን ለቤተሰባችሁ፤ ግማሹን ደግሞ ለወቅፍ ለግሰውታል:: ለራስዎት የግል ወጪ የሚሆንስ ምን አስቀምጠዋል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ

ውብ በሆነ ፈገግታ ተሞልተው "ባጭሩ ምላሼ ምንም ነው!" የምለብሳቸው ልብሶች ብቻ እኔ ጋር አሉኝ:: እድሜዬ በሰማኒያዎቹ ውስጥ ነኝ! ከዚህ ቡኃላ ምን ልፈልግ እችላለሁ? የወቅፍ ፕሮጀክቴ ወጪዬን ይሸፍናል፣ መጠለያ፣ ምግብ፣ ህክምና እና መጓጓዣ አገኛለው::በትንሹ ለመኖር በደንብ የተብቃቃው ነኝ:: ሲሉ መልሰዋል::

” ቢሊየነር ሆነው ግን ምንም ገንዘብ የሌለው ሰው በመሆኖት! "ምን ይሰማዎታል?" ሲባሉም
81 views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 11:34:57 #የእሳት ቢሆን እንጂ…

ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿وَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ، لَا يَسْمَعُ بِي أَحَدٌ مِنْ هَذِهِ الْأُمَّةِ يَهُودِيٌّ وَلَا نَصْرَانِيٌّ، ثُمَّ يَمُوتُ، وَلَمْ يُؤْمِنْ بِالَّذِي أُرْسِلْتُ بِهِ إِلَّا كَانَ مِنْ أَصْحَابِ النَّارِ﴾

“የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው እምላለሁ! አንድም ከዚህ ኡመት አይሁድም ይሁን ክርስቲያን ስለእኔ መላክ አይሰማም። ከዚያም በእርሱ በተላኩበት ሳያምን የሚሞት አይኖርም። እርሱ የእሳት ባለቤት የሚሆን ቢሆን እንጅ፡፡”

ሙስሊም ዘግበውታል: 153



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
99 views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ