Get Mystery Box with random crypto!

ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fethmedia — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fethmedia — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የሰርጥ አድራሻ: @fethmedia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-01-01 13:50:02
105 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 13:49:58 ኢስላሚክ ባንክ እና ከወለድ ነፃ መስኮት አሰራራቸው አንድ ነው በሚል በወለድ ባንክ ገንዘብ ማስቀመጥ አልተፈቀደም።

ምክንያቱም የሪባ ባንኮች ገንዘቡን አላህን ለማመፅ ይጠቀሙበታል። በእነዚህ ባንኮች ገንዘቡን የሚያስቀምጥ ደግሞ የሪባ ሰዎችን ጉልበት እያፈረጠመ ነው።

አላህ ደግሞ «በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ።» በማለት ከወንጀለኞች ጋር መተባበርን ከልክሏል።

በአንፃሩ አንድ ሰው ኢስላሚክ ባንክ ከተጠቀመ የሪባ ሰዎችን እየተዋጋ ነውና የአላህን ሃይማኖት እየረዳ ነው።

አንዳንድ ሰዎች ኢስላሚክ ባንክም ሆኑ የሪባዎቹ ለግላቸው ጥቅም የሚነገዱ ከሆነ ምን ልዩነት አለው? ይላሉ።

ልዩነት አለው፦

አንደኛ አላህ ንግድን አልከለከለም። ሪባን ግን ከልክሏል። ስለዚህ ሪባን እንደ ዋና የገቢ ምንጩ ከያዘ አካል ጋር ካለሪባም ቢሆን መገበያየት አልተፈቀደም።

ሁለተኛ ኢስላሚክ ባንክ ሰዎችን ከሪባ የሚጠብቅ በመሆኑ ጥቅሙ ለባንኩ ባለቤቶች ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ሙስሊም ጭምር ነው።

አንድ ሰው ከወንጀል የጠበቀውን ጉዳይ አልጠቀመኝም ብሎ የሚያስብ ከሆነ ደግሞ የኢማን ትርጉሙ አልገባውም። ወይም ሰው ለምን አገኘ የሚል ቅናተኛ ነው።

በአገራችን ወለድ አልባ መስኮት ይፈቀዳል እያሉ የሪባ ባንኮችን ገንዘብ እንዲያካብቱ ምክንያት የሆኑ ዳዒዎችና ዑለማዎች አሉ። ይህ ጉዳይ ኢስላሚክ ባንክ ከመምጣቱ በፊት ከሆነ ችግር የለውም። ባንኮቹ ከተመሰረቱ በኋላ ከሆነ ግን ወለድ አልባ መስኮትን ማበረታታት ኢስላማዊ ባንኮችን ማዳከም ነውና ከዚህ ስህተታቸው መታረም አለባቸው። ኢስላሚክ ባንክ እያለ ወለድ አልባ መስኮትን የሚፈቅድ አንዳችም ማስረጃ የለም። ካልሆነ አላህ ይጠይቃቸዋል።

ሰል ማን




https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
100 views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 13:22:33
በጎንደር ከተማ ሐጅ አሊ ጎንደር መካነ  መቃብር ዙርያ  የነበረው የይዞታ ይገባኛል ክርክር በሽምግልና ይፈታ ዘንድ መጅሊሱ ያዘጋጀው የሽምግልና ፕሮግራም አሁን ጀምሯል።

አዲሱ መጅሊስ ገና ከመምጣቱ ለአመታት ያልተፈታን ችግር መፍታት መጀመሩ ትልቅ ተስፋ ነው ።



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
81 viewsedited  10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 10:05:58 የተረሱ ሱናዎች

~ የ40 ዓመት ሴት  ማግባትም ሱና ነው።
~ የፈታች ሴት ማግባትም ሱና ነው።
~ ልጅ ያላት ሴት ማግባትም ሱና ነው።
~ ባሏ የሞተባት ሴት ማግባትም ሱና ነው።
~ ቤት ዉስጥ ሥራ ማገዝም ሱና ነው።
~ ለሚስት ምርጥ ባል መሆንም ሱና ነው።
~ ሚስት ማጉረስም ሱና ነው።
~ ከሚስት መጨዋወትም ሱና ነው።
~ ለሚስት ፍቅር መግለፅም ሱና ነው።
~ ሚስትን ማቆላመጥም ሱና ነው።
~ ለሚስት ማዘንና መለሳለስም ሱና ነው።
~ የሚስትን ስህተት ማለፍም ሱና ነው።
~ ሚስትን ማክበርም ሱና ነው።
~ ለሚስት መዋብም ሱና ነው።
~ የሚስትን ቤተሰብ ማክበርም ሱና ነው።
~ የሚስትን ዉለታ ማውሳትም ሱና ነው።
~ ሚስትን ማማከርም ሱና ነው።

Muhammedseid ABX

https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
84 views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 08:53:02
አልሐምዱሊላህ ስርጭታችን ተመልሷል። ስላደረጋችሁት ድጋፍ ሁሉ በአላህ ስም እናመሰግናለን። ጀዛኩሙላሁ ኸይረን
nesihatv
88 views05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 06:25:19
#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 08 #ጀማዱል አኽር 1444 ሂ
102 views03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 06:23:34 "ኢብኑ ወሊድ ዑባደት ኢብኑ ሷሚት (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦

"በማንኛውም ወቅትና ሁኔታ በታዛዥነታችን ልንፀና የመልዕክተኛውን ፍላጎት ከፍላጎታችን ልናስቀድም ከአላህ ዘንድ ለመረጃ የሚሆንን ግልፅ ኩፍር እስካላየን ድረስ ሙስሊም መሪያችንን ላንቀናቀን፥ የትም ብንሆን ከሀቅ ውጭ ላንናገር፥ የአላህን እርካታ በመሻት በምንፈፅመው ተግባር የሰዎችን ትችት ላንፈራ ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ቃል ተጋባን።"
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
- ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል"
==========================================
ይህን ሐዲስ ያገኙውት ከ ኢትዮ ቢላል ሃዲስ አፕ ነዉ



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
103 views03:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 22:53:21
104 views19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 22:52:29 ሰሞኑን ደግሞ «የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት ከኦሮሚያ ባንክ ጋር አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ» የሚል ዜና ያዩ ወንድሞች ጉዳዩን ከብሄር ፖለቲካው ጋር ለማገናኘት የሄዱበትን ርቀት አይቼ ሳቅቼ ነው የሞትኩት ። ምንም እንኳ አጭር ግዜ ቢሆንም መጅሊሱን ለመውቀስ ወይም ለመተቸት እኮ ሌሎች ክፍተቶች ነበሩ። በእርግጥ «የመግባቢያ ሰነድ» ምን እንደሆነ ያወቁ አልመሰለኝም።

በነገራችን ባንኩን ያከበሩና አብረው መስራት የፈለጉ ሰርክ ደጅ እንደሚጠኑ እሙን ነው። ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀምሮ በርካታ ባንኮች ሂጅራና ዘምዘምን ጨምሮ አብረው ለመስራት ውይይቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። የሀጅ ስራ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንደመጠየቁ መጠን ከወዲሁ ለሁሉም በራቸው ክፍት ማድረጋቸው የሚያስመሰግናቸው ሲሆን አንዳንድ ባንኮች ደግሞ ከዚያ አልፈው ወደተግባር መግባታቸው የሚያስመሰግናቸው እንጅ የሚያስወቅሳቸው አይደለም።

በነገራችን ለይ ሀጅን ከዘምዘምና ከሂጅራ ባንክ ጋር ብቻ እንስራ ቢሉ የአንድ ሺ ሰው ምንዛሬ እንኳ በአግባቡ የማግኘት እድል አይኖራቸውም። ስለሆነም እንኳን ደጅ ጠንቶ የመግባቢያ ሰነድ ያዘጋጀ ባንክ ይቅርና የመጅሊሱ በር የት እንደሆነ ማወቅ የማይፈልጉ አማራ ባንክ እና አሀዱ ባንክ የመጅሊሱን መስፈርት አሟልተው አብረው ለመስራት ከመጡ ወይም ኩራቱ ለቋቸው እንደባንክ ከመጡ የሚከለከሉበት ምንም ምክንያት የለም።

የቁርዓን ውድድሩ ወቅት 10,000 ዶላር ለአሸናፊው ሽልማት የሰጠው ኦሮሚያ ህብረት ሰራ ባንክ አጅር ለማግኘት ሳይሆን ደንበኛ ለማግኘት እንደሆነ ባንኩን የሚመሩት ጠንቅቀው ያውቃሉ።

እናም «አማራ ባንክ ለመጅሊስ ጋር ለመስራት ለምን ኮራ» ከማለት ይልቅ አብሮ ለመስራት መጅሊሱን አክብሮ የመጣን ባንክ ከራሳችን የፖለቲካ እሳቤ ተነስተን መውቀስ የውስጥ ቂም ወይም ስለባንክ ቢዝነስ ያለማወቅ እንጅ ሌላ አይመስልም።

ይልቅስ ከወለድ አልባ ስርዓት ያላችው ባንኮች ሁሉ ሳይኮሩና ሳይግደረደሩ በሀጅና መሰል ጉዳዩች አብሮ ለመስራት ቢፈራረሙ ያተርፋሉ እንጅ አይከስሩም። ደንበኛ ንጉስ ነው እንደሚባለው ደንበኛን ያከበረ ይከበራል።
Adugnaw Muche




https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
101 views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 21:41:38
ነገ እሁድ ታህሳስ 23 የወልዲያ የመድረሰተል ኢስላሚያ የሰላም ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች በኃይካን ሆቴል የሚገናኙበት ልዩ የውይይት መድረክ ተዘጋጅቷል:: በአዲስአበባ እና በአቅራቢያዋ ያላችሁ በዚህ የውይይት ፕሮግራም ላይ እንድትሳተፉ ጥሪ ቀርቧል!
Abdurehim ahmed



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
111 viewsedited  18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ