2023-01-02 21:23:44
ኢንዶኔዥያ ከጋብቻ በፊት የሚደረግን ግንኙነት የሚከለክል ጥብቅ ህግ አወጣች ።
ከአለም ትልቋ ሙስሊም ሀገር ኢንዶኔዥያ በሀገሪቱ ውስጥ ከጋብቻ በፊት ፆታዊ ግንኙነት መፈፀም ከፍተኛ ቅጣት የሚጠብቀው ወንጀል መሆኑን በህጓ ደንግጋለች ። በመሆኑም ከዚህ በሗላ ኒካህ የሌላቸው ጥንዶች አንድ ቤት መሆንም ሆነ አብረው መኖር እንደማይችሉ ህጉ ይደነግጋል ።
ይህ እንደ ሀገሪቱ አጠቃላይ ህግ ሲሆን በተለያዩ የኢንዶኔዥያ ግዛቶች ደግሞ ከዚህም ጠበቅ ያለ ህግ ተደንግጓል ። በዚህም መሰረት ሁሉም ወንጀሎች የሚዳኙት በሼሪአ ህግ ብቻ ይሆናል ።
ኢንዶኔዥያ ይህንን ህግ ማውጣቷን ተከትሎ ከምእራቡ አለም መገናኛ ብዙሀንና ከተቋማት ከፍተኛ ተቃውሞና ውግዘትን እያስተናገደች ትገኛለች ። የሰብአዊ መብት ተቋማት የሚሰኙት እነ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና Human rights watch የኢንዶኔዥያን ድርጊት የመብት ጥሰት እና የድሞክራሲ ጭፍለቃ ሲሉ አውግዘውታል ።
ኢንዶኔዥያ በርካታ ሚሊዮን ቱሪስቶች በየአመቱ የሚጎበኟት ሀገር ናት ። እናም ምእራባውያን የሆኑ አስጎብኚ ድርጅቶች በኢንዶኔዥያ ላይ አድማ እንደሚያደርጉ ቢያስፈራሩም ኢንዶኔዥያ ግን የሚፈጠር ነገር የለም በማለት ህጉን አፅድቃለች ።
ኢንዶኔዥያ ከ 231 ሚሊዮን በላይ ሙስሊሞች ያሏት አጠቃላይ ህዝቧም 275 ሚሊዮን ይደርሳል ። ይህም ከአለም አራተኛዋ ባለግዙፍ ህዝብ ያደርጋታል ።
ኢንዶኔዥያ በጥቅል ኢኮኖሚዋ ከአለም 7 ኛ ደረጃ ላይ የምትቀመጥ ሲሆን በሚቀጥሉት አመታት ከአለም ባለ 3 ግዙፍ ኢኮኖሚ ሀገራት አንዷ እንደምትሆን ተተንብዮላታል ።
Seidmohammed alhabeshi
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
77 views18:23