2023-01-03 21:09:00
ለብልጽግና መጅሊስ አልታዘዘም፣ ከአስተዳደርነት አልነሳም ሲል አቶ መንሱር ዘይኑ በኑር መስጂድ ቅጥር ጊቢ ህገ ወጥ የሆኑ የመስጂዱ ሰጋጅ ያልሆኑ አካላትን በማሰባሰብ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት መሞከሩ ታውቋል።
ታህሳስ 25/2015 ማክሰኞ
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከ/ም/ቤ ባለፉት ወራት በአዲስ መልኩ ሕዝባዊና ሕጋዊ አደረጃጀት በመፍጠር በመላው ከተማ ያሉ የመጅሊስ የወረዳና የክ/ከ አመራሮችን ስራ ማስጀመሩ ይታወቃል።
በዚህ ሕጋዊና ሕዝባዊ ውክልና መሰረት መላዉ ሕዝባችን በሚፈልገዉና በመረጠዉ መልኩ መዋቅሩ በመውረዱ እጅግ ደስተኛ መሆኑን ከፍተኛ ድጋፍ አሳይቷል።
ይሁንና በርካታ የከተማዉ ምዕመን በሚሰግድበት በአራዳ ክ/ከ የሚገኘዉ ኑር/በኒ መስጂድን አስተዳድራለዉ የሚለዉ በአቶ መንሱር ዘይኑ የሚመራዉ የቀድሞ ሕገ ወጥ መጅሊስ በሠላም ከመልቀቅና ከማስረከብ ይልቅ ረብሻ ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
በዛሬው እለትም የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሰጠዉ አቅጣጫ መሰረት የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሊድ መሀመድ ፣የአራዳ ክ/ከ ና የወረዳ አመራሮች የኑር መስጂድ አስተዳድር በአዲስ መልኩ እንዲያዋቅሩ በቅጥር ጊቢ ቢገኙም አቶ መንሱር ዘይኑ ባደራጃቸዉ ህገ ወጦች ምክንያት ሁከትና ብጥብጥ ለማሳነሳት ጥረት አድርጓል።
አቶ መንሱር "እናንተ የብልጽግና መጅሊስ ናችሁ፣ ደም ይፈሳል እንጂ ከቦታዬ አልነሳም፣ መስጂዳችንን ልትነጥቁን ነው፣..." እንዲሁም እድሜዉን የማይመጥኑ ስድቦች ሲሳደብ የመጅሊስ አመራሮቹ ሁኔታዉን በትዕግስት አሳልፈዋል።
አቶ መንሱር ያሰባሰባቸዉ ወጣቶች ከጠሮ፣ ከ01፣ እና ከኑር መስጂድ አከባቢ ተሰባስበዉ የመጡ መሆናቸዉን ለማወቅ ተችሏል። እነኚህ ወጣቶች በቀደመዉ ጊዜ በተለያዩ መስጂዶች ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸዉ ልብ ይሏል።
የአ/አ ከተማ መጅሊስ ለአቶ መንሱር የስንብት ደብዳቤ መጻፉ ይታወቃል።
ሙጂብ አሚኖ
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
117 views18:09