2023-01-08 09:16:27
በጭንጎ ቀዴ የአክፍሮት ሀይላት በሙስሊሞች ላይ ትንኮሳ እና ጥ*ቃት መፈጸማቸው ተገለጸ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ታሕሳስ 29/2015
...
በደቡብ ክልል በሀድያ እና በስልጤ ዞን ድንበር በሚገኘው በሊሙ ወረዳ በጭንጎ ቀበሌ የአክፍሮት ሀይላት በአልን ሽፋን በማድረግ በቀበሌው ባሉ ሙስሊሞች ላይ ትንኮሳ እና ጥቃት አድርሰዋል::
..
የዚህ መሰሉ ትንኮሳ በሀድያ ባሉ የዞን እና የወረዳ አመራሮች ጭምር ድጋፍ እና ሽፋን ሲፈፀም የቆየ መሆኑን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች በዛሬው እለት ግን ትንኮሳው ወደ ጥቃት ከፍ ብሎ በጭንጎ ባለው መስጂድ ውስጥ ባሉ ደረሶች እና በዙሪያው በነበሩ ሙስሊሞች ላይ ድብደባ መፈፀማቸው ታውቋል:።
..
የአክፍሮት ሀይላቱ በአካባቢው የእምነቱ ተከታዮች ባይኖሩም ከመስጂዱ አጠገብ ቤተ አምልኮ እንገነባለን በሚል ከአባባቢው ባሉ የስልጤ ሙስሊሞች ጋር ሁሌም ትንኮሳ እና ግጭት ለመፍጠር ሲታገሉ የቆዩ ሲሆን በዛሬው እለትም በዓላቸውን ሽፋን በማድረግ ወደ መስጂዱ እየጨፈሩ በመምጣት በሙስሊሞች ላይ ጥ**ቃ*ት ማድረሳቸው ታውቋል።
..
በ*ጥ**ቃቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሙስሊሞችም ወደ ሆሳና ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ሴቶችን ጨምሮ በርካቶች ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ታውቋል። ጥቃት አድራሾቹ በስልጤ ድንበር በሀድያ ዞን በጭንጎ ቀዴ ወረዳ የሚገኙ አመራሮች ጭምር ድጋፍ እንደሚደረግላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የስልጤ እና የሀድያ ዞን አስተዳደር በነዚህ አጥፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ የሀይማኖት ግጭት ለመቀስቀስ የሚጥሩ ሃይላትን ሊያስቆም ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
...
ሀሩን ሚዲያ
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
92 views06:16