2022-12-31 17:52:02
በሼህ አደም ቱላ ፋውንዴሽ ከስድስት ቢሊየን ብር በላይ የእስልምና ሀይማኖት መንፈሳዊ ዩንቨርስቲ ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ፡፡
**የሼህ አደም ቱላ ፋውንዴሽን ከሀረሪ ክልል ፣ከምስራቅ እና ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ከድሬደዋ ኢላሞች እና ሀጢቦች ጋር የጋራ የውይይት መድረክ አካሂደዋል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሀረሪ ክልል እስልምና ጉዳዮች መጅሊስ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ሼክ አብዱሰላም ጅብሪል እንደተናገሩት በሼክ አደም ቱላ የተጀመረው ፋውንዴሽን መንገድ ላይ እንዳይቀር እንደ ሀረሪ ክልል አባላቶችን በማደራጀት ከእስልምና ሐይማኖት አባቶች ጋር ሰፊ ስራዎች እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡
በድሬደዋ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተወክለው በመድረኩ የተገኙት ሼኽ አሊዪ አህመድ በበኩላቸው የድሬደዋ መጅሊስ በሼክ አደም ቱላ የተጀመረውን ፋውንዴሽን በበጀት እና በሰው ሀይል የመደገፍን ስራ እንደሚሰሩም ገልፀዋል፡፡
በምስራቅ ሀረርጌ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምክትል ሀላፊ የሆኑት ሼክ ኡመር እስማኤል በመድረኩ ላይ በሰጡት አስተያየት የሼኽ አደም ቱላ ፋውንዴሽን ጉዳይ የክልል ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ ስለሆነ በእርሳቸው ስም የተጀመረው የእስልምና ዲን ከግብ ለማድረስ የድርሻውን እንደሚወጡም ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ በሼኽ አደም ቱላ ፋውንዴሽን ላይ ያጠነጠነ የጥናታዊ ፁሁፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የፋውንዴሽኑ ዋና አላማ ላይም የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡
የሼኽ አደም ቱላ ፋውንዴሽን ከግብ ለማድረስ የእስልምና ዩንቨርስቲ በስድስት ቢሊየን ብር ለመስራት እቅድ ተይዞ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል ተብሏል፡፡
በመድረኩ ላይ የተሳተፉ ሼኾችና ኡላማዎች ወደ መጡበት ሲመለሱም የሼኽ አደም ቱላን ፋውንዴሽ ለማሳካት የድርሻቸውን ጥረት እንደሚያደርጉም ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ ከምስራቅ ሀረርጌ ከድሬደዋ አስተዳደር ምእራብ ሀረርጌ እና ከሀረሪ ክልል የተወጣጡ እስልምና ሀይማኖት መሪዎች እና ሼኾች ተገኝተዋል፡፡
ዘጋቢ አብዲ ኡስማን
22 / 04 / 2015
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
113 views14:52