Get Mystery Box with random crypto!

ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fethmedia — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fethmedia — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የሰርጥ አድራሻ: @fethmedia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 77

2022-07-04 17:45:32 በድጋሚ ሙስሊም ወሎዬዎች ተጨፈጨፉ
===========================

Majlisa Oromiyaa - የኦሮሚያ መጅሊስ - Oromia Mejlis

በቄለም ወለጋ ዞን በመቻራ ወረዳ መንደር 20 ቀበሌ ውስጥ በወሎ ሙስሊሞች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል። ኢናሊላሂ ወእና ኢሌይሂ ራጂኡን። ቁስለኞች ሆስፒታል አጨናንቀዋል። የሟቾች ቁጥር ብዙ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመልክታል። ከማህበረሰቡ የደረሰን መረጃ በኦነግ የታጣቂዎች እንደተፈፀመ አሳውቀውናል። ታጣቂዎቹ በቅርብ ግዜ በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ወረዳ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተጨፍጭፈዋል። ተፈናቅለው ያሉትም አስፈላጊ እርዳታ አልደረሳቸውም። የወሎዬዎች ሞት መች ያበቃ ይሆን ሃላፊነቱስ ማን ይወስዳል
ለፖለቲካ ፍጆታ ለምን የሙስሊሞች ደም ይፈሳል እስከመቼ
የኦሮሚያ መጅሊስ ድርጊቱን አጥብቆ ያወግዛል። ሀገርን እያስተዳደረ ያለው መንግስት ነው። ስለዚህ ይህንን ጉዳይ በአስቸኳይ አጣርቶ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ አጥብቀን እንጠይቃለን። የቶሌ ጉዳይ ፈር ሳያገኝ በድጋሚ መከሰቱ አሳፋሪ ነው።
የአላህ ወንድሞቻችን የሸሂድነት ደራጃ የቆሰለቱን ፈውስን ለቤተሰባቸው ሰብርን ወፍቃቸው። አሚን


https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
171 views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 17:25:26 በሳኡዲ የመጅሊሱ አካውንት ተቀምጦ የነበረው የሶማሌ ክልል ሁጃጆጅ ገንዘብ

አቡ ዳውድ ኡስማን

ከ 3 አመት በፊት ሀጅ ሳይሄዱ የቀሩት 423የሶማሌ ክልል ሁጃጆች ገንዘብ በወቅቱ በባንክ በኩል ተልኮ 3.4 ሚሊዮን ሪያል በሳኡዲ የመጅሊሱ አካውንት ገቢ ተደርጎ ነበር!

ሁጃጆቹ መሄድ ሳይችሉ ሲቀር ገንዘባቸው ከሳኡዲ የሐጅ ሚኒስተር የመጅሊሱ አካውንት ወጪ ሆኖ እንዲመለስ ደብዳቤ እንዲፅፉ የተጠየቁት ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ዘለቀ ተመላሽ እንዲሆን ደብዳቤ አልፅፍም አሻፈረኝ በማለታቸው ላለፉት ሶስት አመታት ገንዘባቸው በሳዑዲ የሐጅ ሚኒስተር የመጅሊሱ አካውንት ውስጥ በዝግ ሂሳብ ተቀምጦ ቆይቷል::

አሁን የሀጅ ዉቅት በመድረሱ አካውንቱ ወደ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ በመዞሩ ገንዘባቸው ተበልቷል እያሉ ሲቀጥፉ የነበሩት ቀጣፊዎች አይናቸውን በጨው አጥበው ብራችሁ ቢበላም አሁን ከራሳችን አውጥተን የሱማሌ ክልል ሀጃጆች ሀጅ እንዲያደርጉ ወስነናል ብለው በራሳቸው ምላስ ያጡትን ገፅታ ህፃን ልጆችን እንኳን ማሳመን የማይችል አመክንዬ በማቅረብ ገፅታቸውን ለመገንባት ውድቅ ሙከራ ለማድረግ ሞክረዋል!
አስቡት የሰራተኛ ደሞዝ እንኳን መክፈል አቅቶት የነበረ ተቋም፣ ላስገነባው ህንፃ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ እዳ ያለበት ተቋም፣ ከሚስኪኑ ህዝብ የአገልግሎት እያለ ከ8እስከ 12ሽህ ብር እየያስከፈለ ያለ ተቋም፣ በዘንድሮ አመት እንኳን ሀጅ መሄድ ሳይችሉ ቀርተው ገንዘባችንን መልሱልን እያሉ ቀን እና ማታ አፈር ላይ እየተኙ ሲንገላቱ ለከረሙ ሚስኪን አዛውንት እናት እና አባቶች የተቋሙን መስታወት በድንጋይ እየመቱ ኑው በማለት ለፖሊስ በሀሰት በመወንጀል ከግቢው አስደብድበው ለማባረር የሚጥሩ ክብር የማያውቁ ክብር ቢስ ሰዎች፣ ሶስት አመታት ሲያንገላታቸው ለነበሩ ሁጃጆች አዝኖ ከኪሱ አውጥቶ ሐጅ ሲያስደርግ አስቡት ?

የሱማሌ ክልል ሁጃጆች ገንዘባቸውበወቅቱ ከሳኡዲ እንዳይመለስ ማን እንዳደረገው ጠንቅቀው ያውቃሉ::/በክልሉ መንግስት በኩል ሳይቀር በኡለሞች እና በሽማግሌዎች በኩል ገንዘቡ ከሳኡዲ እንዲመለስ መጅሊሱ እንዲያደርግ ተጠይቋል:: አሻፈረኝ ተብሎ እስካሁን ቢቆይም::ይህን እውነታ የሶማሌ ክልል ኡለሞች በይፋ ለህዝባቸው አሳውቀዋል::

የሶማሌ ክልል ሁጃጆች የሰጡትን ምስክርነት በሀሩን ሚዲያ መመልከት ትችላላችሁ





አሁን ላይ የሶማሌ ክልል ሁጃጆች ሀጅ ከሄዱም ለሶስት አመታት ገንዘባቹ ተበልቷል እየተባሉ ሲዋሹት በነበረው በራሳቸው ገንዘብ ነው:: በዘንድሮ አመት ሐጅ መሄድ ያልቻሉ ካሉም ገንዘባቸውን የሚቀበሉት የማንም ቀጣፊ በግል ችሮታው የሚመልስላቸው ሳይሆን ሶስት አመታት በሳኡዲ በመጅሊሱ አካውንት ተቀምጦ ከነበረው የራሳቸው ገንዘብ ነው::

ሶስት አመታት ሙሉ ኦዲት አንደርግም እየተባለ ሲሸሽ የነበረው የሱማሌ ክልል ሀጃጆች ገንዘብ በቦርዱ ተበልቷል እያሉ ሲሰብኩ የነበሩት ቅጥፈት ስለሚጋለጥባቸው ነበር::

ዞሮ ዞሮ ሶስት አመት ሲቀጥፉ ቢሰነብቱም የሱማሌ ክልል ሁጃጆች ገንዘብ ተበልቷል እያሉ መቆየት በኦዲት የሚረጋገጥ መሆኑ አይቀሬ በመሆኑ አሁን ላይ ገንዘባቸው ከተቀመጠበት ወጥቶ አገልግሎት ላይ ውሏል::

የሚገርመው ግን ከ 40ሚሊዬን ብር በላይ የሀጃጆቹ ገንዘብ ተበልቷል እያሉ ሶስት አመታት ሙሉ እየሰበኩ ሲቆዩ ይህን ሁላ ሶስት አመት በኦዲት ገንዘቡ መበላቱን አረጋግጦ ለህዝብ ማሳወቅ እና በህግ እንዲጠየቁ አለማድረጋቸው እራሳቸውን በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን አለማወቃቸው/ነው::የህዝብ ገንዘብ ተዘርፎ ዘራፊውን በህግ ሳይጠይቁ ሶስት አመት ዝም ማለት ዘርፈዋል ከተባሉት ጋር እኩል የወንጀሉ ተባባሪነት መሆኑን ዘንግተውታል:: ሌባ ሲዘርፍ እያዩ ዝም ማለት በህግ ያስጠይቃል:: እነሱስ ገንዘቡ ሲዘረፍ የማንን ጎፈሬ ሲያበጥሩ ነበር መባላቸው አይቀርም::

እውነታው ግን ገንዘቡ ተበልቶ ሳይሆን በሳኡዲ የመጅሊሱ አካውንት በዝግ አካውንት እስካሁን ተቀምጦ ስለነበር እና አሁን ሲከፈት ገንዘቡን አውጥተው ለሁጃጆቹ አገልግሎት ላይ እንዲውል ማድረጋቸው ነው::

መጅሊሱ በህጋዊ የውጪ ኦዲተር ይመርመር እና እውነታው ይውጣ በተባለ ቁጥር መጅሊሱ ለሁለት ይከፈል እያሉ ሲሸሹ የነበሩት እነማን እንደሆኑ ሁሉም ያውቀዋል!

የኦዲት ሽሽት በዱኒያ ቢያመልጡት በአኼራ ግን ማምለጫ የለውም!

ነገም አላህ ውሸታሞችን እና ቀጣፊዎችን እንዲህ ያዋርዳቸዋል!


https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
156 views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 16:59:21
//የሰዎች ነፃነት የሚያበቃው
የአላህን ወሰን ማለፍ ሲጀምሩ ነዉ//

« የአላህንም ሕግጋት የተላለፈ ሰው በእርግጥ ነፍሱን በደለ»
[ ሱረቱ-ጦላቅ - 1 ]
حريّة الإنسان تنتهي حيث تبدأ حدود الله (وَتِلكَ حُدُودُ اللَّهِ وَمَن یَتَعَدَّ حُدُودَ اللَّهِ فَقَد ظَلَمَ نَفسَه)

||ሸይኹል ሐዲስ ሐፊዘሁሏህ|

Amir mohammed


https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
150 views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 16:57:23
«ይሄ ኡማ የሚጨቆነው በጨቋኞች ፊት ቆሞ

እውነትን የሚናገር ደፋር ታጋይ ጀግና
«ሰው በውስጡ ከሌለ ነው»፡፡

[ ዶ/ር ሰልማን አል-ኦዳህ] [ሐፊዘሁሏህ]

Amir mohammed


https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
137 views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 13:47:20
152 views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ