Get Mystery Box with random crypto!

ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fethmedia — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fethmedia — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የሰርጥ አድራሻ: @fethmedia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 68

2022-07-18 17:48:20
16 views14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 17:47:57 " أقسم بالله العظيم أن أكون موثوقا لديني ووطني ، وأن أحافظ على وحدة المسلمين، وإنه لقسم لوتعلمون عظيم، والله العظيم، والله العظيم،والله العظيم،والله العظيم!!"
" የሃይማኖቴንና የሀገሬን አደራ በአግባቡ ለመወጣት እንዲሁም የሙስሊሙን አንድነት ለማስጠበቅ እንደምሰራ ዝግጁ መሆኔን በአላህ ስም ቃል እገባለሁ። "

በመጨረሻም መርሃ ግብሩ በሸ/ጣሀ የሚቀጠሉት አንቀፆች ተነበው በዱዐ ተቋጭቷል።
" وتلك الآيام نداولها بين الناس.."

والحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات!

#አዲስአመራር
#ሁሉንአቀፍመጅሊስ
#ለውጥ

Nesru Khedir/ነስሩ ኸድር


https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
17 views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 17:47:57 የዛሬው ሀምሌ11/2014 "የኢትዩጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥ እና አንድነት 2ኛ ጉባኤ" ውሎ አጭር ጥንቅር

ፕሮግራሙ በሽ/ዐብዱልሐሚድ አሕመድ (ከጅማ) መድረክ መሪነት ከረፋዱ 4:30 ላይ ጀምሯል።

የታላቁ አንዋር መስጅድ ሸ/ጧሀ ሀሩን የሚከተሉትን የቁርአን አንቀፆች አንብበዋል:-

" لا يكلف الله نفسا إلا وسعها لها ما كسبت وعليها ما اكتسبت ربنا لا تؤاخذنا إن نسينا أو أخطأنا ربنا ولا تحمل علينا إصرا كما حملته على الذين من قبلنا ربنا ولا تحملنا ما لا طاقة لنا به واعف عنا واغفر لنا وارحمنا أنت مولانا فانصرنا على القوم الكافرين "

" الله الذي خلق سبع سموات ومن الأرض مثلهن يتنزل الأمر بينهن لتعلموا أن الله على كل شيء قدير وأن الله قد أحاط بكل شيء علما "

በመቀጠል ዶ/ር ጀይላን ኸድር እና ሸ/ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እንዲሁም ሸ/ዐብድልከሪም ሸ/በድረዲን በየተራ የጉባኤውን መርሃ ግብር አንደሚከተለው አስረድተዋል:-

1ኛ/የዶ/ር ጀይላን ኸድር መልዕክት:-
የሚከተሉትን አንቀፆች አስታውሰዋል
" واعتصموا بحبل الله جميعا.."
" إن الذين فرقوا دينهم وكانوا شيعا لست منهم في
شيء إنما أمرهم إلى الله ثم ينبئهم بما كانوا يفعلون "
" ዛሬ እዚህ የታደማችሁ ሚያዚያ 23/2011 ያስረከባችሁንን ስልጣን መሠረት አድርገን መንግሥታችን ባደረግልን ድጋፍም ጭምር ኢስላማዊ ባንክን ማቋቋም ችለናል፣ ሕዝበ ሙስሊሙን የሚመጥን መሀል መዲናዋ ላይ ሰፊ መሬትም ተቀብለናል..
ሆኖም ከዚህ በላይ ብዙ ስራዎችን መስራት ሲገባን የተመረጥነው ለ6 ወራት ሳይሆን እስከመጨረሻው አንድንቀጥል ነው በሚል ንትርክ እየተስተጎጎልን ለዛሬዋ እለት በቅተናል።
ዛሬ የተገኘነው ጉዳዩን ወደናንተው ለመመለስ ነው። ምክንያቱም የኢትዩጵያን ሙስሊም የምትወክሉት እናንተ እንጂ መስማማት ያልቻልነው እኛ ጥቂት ዑለሞች ስላልሆንን።"

2ኛ/የሸ/ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መልዕክት:-
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አሕመድ በሰጡን ምክር መሠረት እሰከ ዛሬ ሀምሌ 11/2014 ድረስ ብቻ እኔና ሙፍቲ መጅሊሱን በጊዜያዉነት እየመራን ነበር ፣ የዛሬውም ፕሮግራም የዘገየው ሙፍቲን እየጠበቅን ስለነበር ነው።
እሳቸው ባለመገኘታቸው የእሳቸው ምክትል የነበሩት ዶ/ር ጀይላን ኸድር መድረክ ላይ እንዲመጡ ሆኗል።
የዛሬው አብይ አጀንዳችንም ለ3 ዓመታት መጅሊስን የሚመሩ አዲስ አባላትን መምረጥ ይሆናል።
ይህንን ለማድረግ በሚያስችል መጠን እስከ አሁኑ ሰዓት ከ 300 አባላት 250 በመገኛተችውና ምልአተ ጉባኤው በመሟላቱ ወደ ምርጫችን እናመራለን (እስከ ፕሮግራሙ ፍጻሜ ድረስ የጉባኤተኛው ቁጥር ወደ 261 ከፍ ማለቱን ልብ ይሏል) ።
ይሀንን የሚመሩ የአስመራጭ ኮሚቴ አባላትም ይኖሩናል።

3ኛ/የሸ/ዐብድልከሪም በድረዲን መልዕክት:-

ዛሬ እዚህ የተገኘነው አማናውን ለሚገባው አካል ለማስተላለፍና፣የሰላም አጋር መሆናችንን በተጨባጭ ለማስመስከር ነው።
ይህን የምናደርገው እንኳን ደም ይቅርና አንባም ሳይፈስ ነው።
የሰላም ጉዳይ የዑለሞች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነው።
በሰላም ጉዳይ ከማንም ጋር አንደራደርም።
በመቀጠል የሚከተሉት አስመራጭ ኮሚቴ አባላት መድረኩን ተረክበዋል:-
1_ ሐጂ/ሙሐመድኑር ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ (የሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ ልጅ)
2_ ሐጂ/ ዐብዱልቃድር
3_ ኡ/ዐብዱልዐዚዝ ኢብራሂም
4_ አቶ/ባሕረዲን አወል
5_ ሐጂ/ኻልድ ሙሐመድ

በመቀጠልም አስመራጭ ኮሚቴው የምርጫ ሂደቱን አፈጻጸም እንደሚከተለው አብራርቷል:-

የሁሉም ክልል ተወካዩች በተሰጣቸውና እንደሚከተለው በተዘረዘረው ኮታ መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት የሚሆኑ በድምሩ 30 የሚሆኑ ተወካዩቻቸውን ይመርጣሉ።
* ኦሮሚያ 5
* አማራ 3
* አ/አ 3
* ደቡብ 3
* ሶማሌ 3
* ዐፋር 3
* ድሬዳዋ 2
* ትግራይ 2
* ሀረሪ 1
* ቤኒሻንጉል 2
*ጋምቤላ 1
* ሲዳማ 1
* ደቡብ ምእራብ 1

የሚመረጡ አመራሮች መስፈርት:-
1_ ዕድሜው ከ30 በላይ የሆነ፤
2_ ኢትዩጵያዊ የሆነ፤
3_ በሚመረጥበት ክልል ነዋሪ የሆነ፤
4_ ሕዝበ ሙስሊሙን ለማገልገል ቅን ፍላጎት ያለው፤
5_ ለእምነቱ ተማኝ የሆነ ተቅዋ ያለው፤
6_ ለቦታው የሚመጥን ብቃትና ክህሎት ያለው፤
7_በመልካም ሥነ ምግባር የሚታወቅ፤
8_ የተላያዩ ማህበራዊ ተሳትፎዎችን ያደረገ፤
9_ መሠረታዊ የሃይማኖቱን መርሆች አክብሮ የሚተገብር፤
10_ የየትኛወም ፖለቲካ ፖርቲ አባል ያልሆነ።

በመቀጠል የእያንዳንዱ ክልል ተወካዩች የተለያዩ ቦታዎች ላይ በመሆን ከተጠቆሙት እጩዎች መካከል የሚከተሉትን የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በድምጽ ብልጫ መርጠዋል:-

ከኦሮሚያ
1_ሸ/ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ
2_ሸ/ዐብዱልሐሚድ አሕመድ
3_ ኡ/ጋሊ አባቦር
4_ ኡ/ዚያድ ዐሊ
5_ ሸ/ሙሐመድ ዐሊ ኸድር

ከአ/አበባ:-
1_ ሸ/ጧሀ ሀሩን
2_ ሸ/ኑረዲን ደሊል
3_ ሸ/ሐሚድ ሙሳ

ከአማራ:-
1_ ሸ/ኡድሪስ ደጋን
2_ ኡ/ዐብዱረሕማን ሱልጣን
3_ ሸ/ሙሐመድ ኢብራሂም

ከደቡብ:-
1_ ሸ/ዐብዱልከሪም ሸ/በድረዲን
2_ሸ/ሙሐመድ ሙስጠፋ
3_ ሸ/ዐብዱልሀዲ

ከሶማሌ:-
1_ሸ/ዐብዱልዐዚዝ ሸ/ዐብዱልወሌ
2_ሸ/አሕመድ ሙሐመድ
3_
ከድሬዳዋ:-
1_ሸ/አሚን ኢብሮ
2_ሸ/ሙሐመድ ዑመር

ከትግራይ:-
1_ ሸ/ዐብዱልመናን ማሕሙድ
2_ ኢንጂነር/አንዋር ሙስጠፋ

ከቤኒሻንጉል:-
1_ ሸ/ዐለሙዲን
2_ሸ/አልመርዲ

ከጋምቤላ:-
1_ ሸ/ዛኪር ኢብራሂም

ከዐፋር:-
1_ ዶ/ር ሙሐመድ ሑሴን
2_ ሸ/መሐመድ አሕመድ ያሲን
3_
ከሲዳማ:-
1_ሸ/ሙስጠፋ ናስር

ከደቡብ ምእራብ:-
1_ሸ/ሑሴን ሐሰን

ከሀረሪ:-
1/ሸ/ሙሐመድ አሚን ዐያሽ

በመቀጠል ከእነዚህ 30 የጠቅላላ ጉባኤ አዲስ አባላት 14 የስራ አስፈጻሚ አመራሮችን አንደሚከተለው መርጠዋል:-
1_ ሸ/ ሐጂ ኢብራሂም (ፕሬዚዳንት)
2_ ሸ/ ዐብዱልከሪም ሸ/በድረዲን (ተ/ም/ፕሬዚደንት )
3_ ሸ/ ዐብዱልዐዚዝ ዐብዱልወሌ (ም/ፕሬዚደንት)
4_ሸ/ ሐሚድ ሙሳ (ዋና ፀሃፊ)
5_ሸ/ ዐብዱልሐሚድ አሕመድ (አባል)
6_ሸ/ እድሪስ ዐሊ (አባል)
7_ ሸ/መሐመድ አሕመድ ያሲን (አባል)
8_ሐጂ/ሙስጠፋ ናስር (አባል)
9_ሸ/ አልመርዲ ዐብዱላሂ (አባል)
10_ ሸ/ ሑሴን ሐሰን (አባል)
11_ ሸ/ ዛኪር ኢብራሂም (አባል)
12_ ሸ/ ሙሐመድ አሚን ዐያሽ (አባል)
13_ ሸ/ አሚን ኢብሮ (አባል)
14_ኢንጂነር/ አንዋር ሙስጠፋ (አባል)

በመቀጠል አዲሱ አመራሮች በሸሪዐ ፍርድቤቱ ዋና ፕሬዝደንት አማካኝነትየሚከተለውን ቃለ መሀላ ፈፅመዋል:-
19 views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 17:20:38
" እኛ ድናችን አንድ ነው ስማችን ሙስሊም ነው ከዚህ ውጭ ሲለጠፍብን የነበረው ታርጋ ሱፊ ፣ ሰለፊ ፣ ውሀቢ የሚባል ታርጋ ዛሬ ሙቶ ቀብሩን ጨርሰነዋል ! ይህንን ከፋፋይ ታርጋ ማጥፋት ብቻ ሳይሆን ተመልሶም እንዳይመጣ አድርገን እናስወግደዋለን " !!

ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ዋና ፕሬዚዳንት ዛሬ ከተናገሩት የተወሰደ !
31 views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 16:48:07
አንዳንድ ያኮረፋችሁ ወንድሞች እኛ አናኮርፍም ሁሌም ለእርቅ በራችን ክፍት ነው ኑ ለዱኒያም ለዲናችንም በጋራ እንስራ

ሸህ አብዱልከሪም በድረዲን ከተናገሩት
55 views13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 16:09:59 Welcome !!

በዛሬው የሸራተኑ ጉባኤ አንገኝም ብለው ያለታሪካቸው ጀግንነት ተሰምቷቸው መንግስትን ና ውረድ እንውረድ ያሉት ሳይቀሩ ተገኝተዋል። ምረጫም ተደርጎ አዲሱ ኃይል መጥቷል። በሱፊያ ስም የተደበቀው ቡድን በግድም ይሁን በውድ ለባለፉት አራት አመታት መርቷል። በዚህ ጊዜው ለህዝበ ሙስሊሙ አንዳችም ፋይዳ ያለው ስራ መስራት ተስኖት አልፏል።

እንዲያውም በከፋ መልኩ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ለሁለት የመሰንጠቅ ትንቅንቅ ውስጥ ገብቷል። የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች historical enemies and nucleus of Islamophobic ከሚባሉት ጋር ያልተቀዳ ጋብቻ መፈፀሙ ታሪካዊ ስህተቱ ይመስለኛል። ከሰራቸው የትግል ስትራቴጂዎች የመጨረሻው የውድቀታቸው ምንጭ "ከየትኛውም የሙስሊም ጠል ኃይላት ጋር ስትራቴጂካል አሊያንስ" መፍጠራቸው ነው።

ሌላኛው አደገኛው የውድቀታቸው ምንጭ መንግሥትም ሰላም መንሳታቸው፣ መንግሥትን መገዳደራቸውና አገር አቀፍ አመፅ ለመፍጠር የሄዱበት እርቀት ነው።

እነሱ ፀረ ሰላም ፣ ፅንፈኛ፣ አክራሪ የሚሉትና በስሙ ጠላታችን ያሉትን ሁሉ ለማስጨፍጨፍ ብዙ የደከሙለት ቡድን በአንፃሩ ትእግስተኛና ለዘብተኛ ሆኖ ማለፉ መራራ ሀቅ ነበር።

አሁን በይፋ መጅሊሱን አዲስ ሓይል ተመርጦበታል። እኛ ልንል የምንችለው ይህን ብቻ ነው።

እንኳን በሠላም መጣችሁ! ለጠቅላላው ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እንጅ ለሆነ ፊርቃ አሊያም ብሄር አሊያም የፖለቲካ ስላልተመረጣችሁ የኢትዮጵያውያንንን ሙስሊሞች ወርድና ቁመት በሚመጥን መልኩ፣ እስልምና በሚያዘው መልኩ ህዝብ ለማገልገል እስከሞከራችሁ ድረስ ከጎናችሁ ነን።

ግና የባለፈውን ነውር ለመድገም ወይም አሻሽላችሁ ለመተግበር ትቂትም ከሞከራችሁ ፣ በተራችሁ ትግላችሁ የሚሆነው ከኛው ከድምፃችን ይሰማ ትውልዶች ጋር ነው። we are watching you and be ready for our serious struggle.

መልካም የሥራ ዘመን

ዐብድልጀሊል ሸኽ ዐሊ ካሰ


https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
71 views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 14:17:40
መልካም ዜና
===========
ሲጠበቅ በነበረው በዛሬው የመጅሊስ ጉባዔ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፕሬዝዳንት ተደርገው ተሹመዋል። ከስራቸውም ሁለት ምክትሎች ተመርጠዋል።


በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ እየተካሄደ በሚገኘው ሁለተኛ ዙር ጉባዔ ከቀድሞ 300 ተሳታፊዎች መካከል 261ዱ ተገኝተዋል። ቀሪዎቹ 39ኙ በሞት፣ በህመምና በሐጅ ጉዞ ምክንያት ሳይታደሙ ቀርተዋል።


በዚህ ጉባዔ ላይ በርካታ የመጅሊሱ አመራሮች እየተመረጡ ሲሆን ዋና ፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መደረጋቸው ታውቋል።


አላህ ለኡማው የሚበጁ ያድርጋቸው። መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልዎ ብያለሁ ሸይኽ ሐጂ!

መላው የኢትዮ ሙስሊምና ለዚህ ለውጥ ህይዎታችሁን፣ ንብረታችሁን፣ ክብራችሁንና ጊዚያችሁን ለሰዋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን።


አል-ሐምዱ ሊላህ አላህ ቀሪ ዘመናችንን ያሳምርልን።


ለታሪክ ቀኑን ልጻፈው፦
ሐምሌ 11, 2014 E.C.
ዙልሒጃህ 19, 1443 H.C.
July 18, 2022 G.C.
||
t.me/MuradTadesse
twitter.com/MuradTadesse
77 views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 13:42:42
104 views10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 13:42:29 የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአመራሮች ምርጫ እየተካሄደ ነው

ሐምሌ 11 ቀን 2014 (ኢዜአ)የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአመራሮች ምርጫ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥና አንድነት 2ኛ ዙር አገር አቀፍ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።

በጉባኤው ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን መጂሊሱን ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የሚመሩ አመራሮች ምርጫም በመካሄድ ላይ ነው።

በጉባኤው ላይ በድምፅ ይሳተፋሉ ተብለው ከሚጠበቁት 300 ተሳታፊዎች መካከል ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 261ዱ መገኘታቸው ታውቋል።

ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በተካሄደው ጉባኤ ከተሳተፉት መካከል 39ኙ በሞት፣ በህመም፣ ከሀጂ ጉዞ ባለመመለስና በልዩ ልዩ ምክንያቶች በዛሬው ጉባኤ አለመገኘታቸውም እንዲሁ።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥና አንድነት 1ኛ ዙር አገር አቀፍ ጉባኤ ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል።


https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
107 views10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 12:23:56 ዛሬ እየተካሄደ የሚገኘው የሸራተኑ ጉባኤን አስመልክቶ
------------
ስብሰባው የሚመለከታቸው ከሁለቱም በኩል ያሉ ዑለማኦችና አስተባባሪዎች እንዲሁም የመንግስት አካላት በሸራተኑ ስብሰባ ታድመዋል።

አካባቢው ልዩ የሆነ ጥበቃ እየተደረገለት በመሆኑ ከፍል ውሀ መስጂድ ጀምሮ በሸራተን ወደ አራት ኪሎ መዞሪያ የሚወስደው መንገድ ለተሽከርካሪም ሆነ ለእግረኛ ዝግ ተደርጓል። በፍል ውሀ ዙሪያም በርካታ የፌዴራል ፖሊሶች ይታያሉ።

ሚዲያን አስመልክቶ የትኛውም ሚዲያ መግባት የተከለከለ በመሆኑ ሁዳ መልቲሚዲያን ጨምሮ ሌሎች ሚዲያዎችም በአካባቢው በቅርብ ርቀት ላይ አዲስ ነገር ካለ በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን።

አላህ ለሁላችንም ኸይር ያሰማን! ለህዝበ ሙስሊሙ አንድነት የሚበጀው ይመረጥልን ዘንድ በዱዓ አንዘናጋ!

ሁዳ መልቲሚዲያ



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
111 views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ