2023-01-08 16:47:49
ተቋማዊ አሰራርን በማጎልበት ከግለኝነትና ከስሜታዊነት ከፍ እንበል!!!
የሐጂ መንሱርን ጉዳይ በተመለከተ:-
1)የወረዳው እስልምና ጉዳዮች ሐጂ መንሱርን በመስጂዱ አስተዳደራዊ ጉዳይ ሊያነጋግራቸው ቢሮአቸው ድረስ ቢሄድም ፍቃደኛ አልነበሩም።
2)የአራዳ ክፍለ ከተማ መጅሊስ በተመሳሳይ ጉዳይ ሊያወያያቸው ወደ ቢሮአቸው ቢያቀናም ኢ-ስነምግባራዊ በሆነ መልኩ እንዲመለሱ አድርገዋል።
3)የክፍለ ከተማው መጅሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ኃላፊና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ሐላፊ ወደ ቢሮአቸው ያቀኑ ቢሆንም በተመሳሳይ ከኢስላማዊ አደብ ውጪ እንዲመለሱ አድርገዋል።
4)የአዲስ አበባ መጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች በተደጋጋሚ:-በመስጂዱ ልማት ዙሪያ፣በፍርድ ቤት ክርክር፣እንዲሆም በካርታው ጉዳይ ቢያወያያቸውም በውይይቱ (በሹራው) መሰረት ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
5)አዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በሪፎርሙ መሰረት በስሩ የሚያስተዳድራቸውን ሰራተኞች ለመለየት እና ህጋዊነታቸውን ለማረጋገጥ ሰራተኞቹ የም/ቤቱ ሰራተኛ ለመሆናቸው የሚስረዱ ሰነዶቻቸውን እንዲያቀርቡ ያዘዘ ቢሆንም እሳቸው መረጃም ሆነ ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም።ወይም ፍቃደኛ አልሆኑም።
6)በመጨረሻ የም/ቤቱ ሰራተኛ ለመሆናቸው ያቀረቡት ብቸኛ መረጃ በራሳቸው የተፈረመ መሆኑ።
7)ከተራ ቁጥር 1-6 በተጠቀሰው መልኩ ህጋዊነትን እና ኃላፊነትን በአግባቡ ካለመወጣታቸው ባሻገር በምን አግባብ ወደ ስራ እንደገቡ ማረጋገጥ ባለመቻላቸው ወይም መረጃና ማስረጃ ለመስጠት ተባባሪ ባለመሆናቸው ምክንያት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አስተዳደር ለግለሰቡ የስንብት ደብዳቤ ለመፃፍ ተገዷል።
8)በኑር መስጂድ ያሉ ሌሎች ሰራተኞች ፎርማሊቲውን በሟሟላታቸው በስራቸው ላይ እንዲቀጥሉ ተደርጓል።
9)የስንብት ደብዳቤ አልቀበልም በማለታቸው ህጋዊ አካሄድን ተከትሎ በሚመለከተው አካል እንዲያደርሳቸው ተደርጓል።
10)የስንብት ደብዳቤው በእጃቸው መግባቱን ካረጋገጥን በኃላ የርክክብ ደብዳቤ የተፃፈላቸው ቢሆንም አልቀበልም በማለታቸው በአራዳ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገን በመጨረሻ ዛሬ ታህሳስ 30/2015 ጠዋት 3:00 እሳቸው ብቻ እንደ አስተዳደር ተገኝተው ለመጅሊሱ አመራር ሊያስረክቡ ተስማምተን በቃለ ጉባኤው ላይ ሁላችን እሳቸውም ጭምር ፈርመው ተለያይተናል።
11)በመጨረሻ ቃላቸውን አጥፈው ስልካቸውን አጥፍተው ተሰውረዋል።
12)የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤትም በቀጠሮው መሰረት በቦታው ዋና ፀሐፊው እና ከፍተኛ አመራሩ የተገኙ ቢሆንም ከስምምነቱ ውጭ የተደረጉ አላስፈላጊ መሰባሰቦች ህዝበ ሙስሊሙን የማይመጥኑ ከመሆናቸውም ባሻገር ለሁከትና ብጥብጥ ምክንያት እንዳይሆኑ በማድረግ ማንኛውም ግለሰብ ከህግ በላይ ሊሆን እንደማይችል አፅንኦት በመስጠት ነገሩ ለማረጋጋት ተችሏል።--- ወዘተ
----
በመጨረሻም ተቋማዊ አሰራርን ማጎልበት ለሁላችንም የሚጠቅም መሆኑን አውቀን ከግለኝነት ከፍ እንል ዘንድ እራሴንም ሁላችንንም በመምከር መልእክቴን እቋጫለሁ።
Ustaz Mohammed Abate
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
94 views13:47