Get Mystery Box with random crypto!

ተቋሙን ለማሳጣት እየተደረገ ያለው የግለሰቦች የጥፋት መንገድ ግለሰቦቹን ከባድ ዋጋ ያስከፍላል! | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

ተቋሙን ለማሳጣት እየተደረገ ያለው የግለሰቦች የጥፋት መንገድ ግለሰቦቹን ከባድ ዋጋ ያስከፍላል!

የአ/አበባ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት የተቋሙን ህልውና ለማስጠበቅ ለአንድም ሰኮንድ ወደ ኋላ አይልም

የአ/አበባ ከተማ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት የህግ ክፍል ሀላፊ ኡስታዝ ሱፊያን ኡስማን


የኑር መስጅድን ተገን በማድረግ የግል ፍላጎትን ማሳካት አይቻልም፡ህግና ስርዓት ይከበራል፡የጊዜና የጉልበት ዋጋ ካሳ በግለሰቡ ላይ በህግ ይዳኛል።

ተቋም ከግለሰብ በላይ ነው፡ግለሰብ ከማሕበረሰብ ጋር ራሱን አቆራኝቶ የግል ፍላጎትን ማስኬድ በፍፁም አይችልም፡ሀገራዊ ለውጥ የጋራ እንጂ የግለሰቦች ሊሆን አይቻለውም፡በተቋም ውስጥ ሌላ ተቋም፡በመንግስት ውስጥ ሌላ መንግስት፡በሀገር ውሰጥ ሌላ ደሴት መፍጠር ፈፅሞ አይታሰብም።

በበኒ ኑር መስጅድ ውሰጥ ተወሽቆ የሕዝበ ሙስሊሙ ተወካይ በመምሰል የተቀመጠው ግለሰብ፡ሕዝበ ሙስሊሙን ሲከፋፍል የነበረ፡አንድነት አይጠቅምም የሚል ከመሆኑ በዘለለ፡የልማት ስራውን በማደናቀፍ ለአመታት የመስጅዱን ሚናራ ሞሽሮ በማስቀመጥ በዋና ከተማ እንብርት ላይ ያለን ግዙፍ መስጅድ ያኮሰሰ ስው ከመሆኑ አንፃር፡በአስተዳደርነትም ደካማ የሆነና የኦዲት ሪፖርት የሌለው ሰው መሆኑ ይታወቃል፡የእምነት ተቋምን የኑሮ መግፍያ ማድረግ ደግሞ ነውርም ነው።

አስተዳደር ተብየው ከቦታው መነሳቱን በቃለ ጉባዔ አስይዞ በራሱ እጅ የፈረመበትን ሰነድ ያልተቀበለ ከሆነ፡የሚያሸሸው ገንዘብና ሌላ ተጨማሪ ሴራ መጎንጎን ላይ ስለመሆኑ የሚያመለክት ከመሆኑ አንፃር ተቋማዊ እርምጃ ወሳኝ ነው።

መስጅድ ተቀማ፡ኢማም ተባረረ፡ደምወዝ ተቆረጠ የሚል የውሸት ዘመቻ ጊዜና ቦታ የለውም፡አንድም ሰው በዝህ ጉዳይ ላይ የተነካ እንደሌለ እየታወቀ ብዙ ማስጮህ ተችሎ ነበር፡ነገር ግን የውሸት መንገድ ሁሌም አጭር ነውና ተጋለጠ።

መጅሊስ የቡድን ወይም የተወሰኑ ሰዎች ተቋም አይደለም፡ሁሉንም በእኩል የሚያገለግል ተቋም ነው፡የተቋም ክብርን ማስጠበቅ ደግሞ የተቋሙን ህልውና ማስቀጠል ነው፡ ስለዝህም ተቋሙን ለማሳጣት እየተደረገ ያለው የግለሰቦች የጥፋት መንገድ ግለሰቦቹን ከባድ ዋጋ የሚያስከፍላቸው መሆኑ መታወቅ አለበት፡ይህን ደግሞ አብረን የምናየው ጉዳይ ይሆናል፡በእስልምናና በቡድን ስም መነገድ አይቻልም፡አበቃ።

የአ.አበባ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት የተቋሙን ህልውና ለማስጠበቅ ለአንድም ሰኮንድ ወደ ኋላ የማይል ጠንካራ ተቋም መሆኑን ሁሉም ማወቅ ግድ ይለዋል ።



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia