Get Mystery Box with random crypto!

💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomerejaa
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

24 Hour News

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-02-02 08:33:24
996 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 08:33:18 #Ethiopia:

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ የእምነቱ ተከታዮች ዛሬ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ተገኝተው ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።

ክቡር አምባሳደር ስለሺ በቀለም የሰልፉ አስተባባሪዎችንና የእምነቱ ተወካይ አባቶችን አነጋግረዋል።

በተወካዮቹ በኩል የቀረቡ ጥያቄዎችን ተቀብለው ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እንደሚያደርሱም ቃል ገብተዋል።
986 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 21:45:23
1.3K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 21:45:18 መግለጫ

ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት የማያስከብር ከሆነ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ መላው ኦርቶዶክሳውያን የሚሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራት በደሉን ለዓለምዓቀፉ ማኅበረሰብ እንደሚገልጽ ዛሬ ማምሻውን በሰጠው አስታወቀ።

በመግለጫቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የተሰጠው መሬት ብዙ ነው ላሉት ሲኖዶሱ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል።

" በአዲስ አበባ ከ75% በላይ የሚኖረው የኦርቶዶከስ አማኝ ህዝብ ስለሆነ ተሰጠ የተባለው መሬት ከአገልግሎት ስፋቱ አንፃር የሚጋነን አይደለም ያሉ ሲሆን በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ጦርነት ምክንያት በማድረግ የትግራይ ቤተ ክህነት ተገንጥያለሁ ሲል ለምን ዝም አላችሁ በሚል ጠቅላይ ሚንስትሩ ላነሱት "የትግራይ ቤተክነት ቢያንስ የውሸት ጳጳስ አልሾመም፣ቤተክርስቲያንን አላዋረደም" የሚል ማብራሪያ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰጥቷል።

መንግሥት ህግን የማያስከብር ከሆነ ቅዱስ ሲኖዶሱ በመላው አለም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠራ በደሉን ለአለም እንደሚያሳውቅ አስታውቀዋል።
1.3K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 21:44:05
1.2K views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 21:43:59 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ

መሪዎቹ የተወያዩት በሶማሊያ ሞቃዲሾ ከተካሄደው ቀጠናዊ የጸረ ሽብር ውይይት መድረክ ጎን ለጎን ነው፡፡

በውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በተለይም የመሰረተ ልማት ትስስርን ማጠናከር፣ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ እና ንግድ ላይ በትኩረት መምከራቸው ተመላክቷል፡፡

መሪዎቹ ከሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፈ በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውም ተጠቁሟል፡፡
1.2K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 20:55:26
1.8K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 20:55:22 61 ቦንቦችን ጨምሮ የተለያዩ መሳሪያዎችን ለሽብር ቡድኑ ሸኔ ሊያደርሱ በድብቅ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

መነሻዉን አዋሽ አድርጎ አዳማ በአንድ ግለሰብ ቤት በመደበቅ ለሸኔ ታጣቂ ቡድን ሊሄድ የነበረ 61 ቦምብ፣ 53 ፊዉዝ፣ 1 ላዉንቸር ከ2 ተተኳሽ ቁንቡላ ጋር እንዲሁም 9 የብሬን ዝናር፣ 20 የክላሽ ካርታ፣ 11 የስናይፐር ካርታ፣ 1 የመኪና ፈንጂ ፊዉዝ፣ 1 የብሬን ጥይት፣ 5 የብሬን ማመላለሻ፣ 2 የስናይፐር መነፅር፣ 1 የብሬን አናት፣ ከሽብር ቡድኑ ጋር መረጃ የሚለዋወጡበት አንድ ላፕቶፕ መያዘቸዉን ለመረጃዉ ቅርበት ያላቸዉ ታማኝ ምንጮች በፎቶ የተደገፈ መረጃ በመላክ አረጋግጠዋል።

የብሕራዊ መረጃና ደኀንነት አገልግሎት የዚህ ህገወጥ ድርጊት ተሳታፊ ሁለት አዘዋዋሪዎች ላይ ጥብቅ ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ ለኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ጥቆማ በመስጠት አዳማ ላይ በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ ማድረጉን ምንጮች ተናግረዋል ፡፡
1.8K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 15:44:04 የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና አፈጻጸም አዝጋሚ መሆኑ ተገለጸ

ማክሰኞ ጥር 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአፍሪካ አገራት መካከል ነጻ የንግድ ቀጠና ለመመስረት ከኹለት ዓመት በፊት ስምምነት ላይ የተደረሰ ቢሆንም፣ አፈጻጸሙ እጅግ አዝጋሚ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ በቅርቡ የወጣ ሪፖርት እንደሚያሳየው በአፍሪካ አገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ በዓለም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በአህጉሪቱ ካሉ 55 አገራት በአምስት አገራት ብቻ ስምምነቱ በከፊል እየተተገበረ እንደሚገኝ ነው የተመላከተው፡፡

የአፍሪካ መንግስታት ለጉዳዩ የሰጡት ትኩረት አናሳ በመሆኑም፣ በቂ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማት አለመኖር፣ ግልጸኝነትና ቅልጥፍና የጎደላቸው አሰራሮች እንዲሁም የኮሮና ወረርሽኝ እና የፀጥታ ችግሮች ስምምነቱ እንዳይተገበር ትልቅ እንቅፋት መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

በአውሮፓ አገራት መካከል ያለው ነጻ የንግድ ልውውጥ ከ66 በመቶ በላይ፣ በእስያ ከ63 በመቶ በላይ እንዲሁም በአሜሪካ ከ44 በመቶ በላይ ሲሆን፣ በዓለም ዝቅተኛ የሆነውና በአፍሪካ አገራት መካከል ያለው ነጻ የንግድ ልውውጥ ግን ከ13 በመቶ በታች መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአህጉሪቱ ያለው ስር የሰደደ የፀጥታ ችግር እና ብልሹ የአስተዳደር ሁኔታ የነጻ ንግድ ልውውጡን የወደፊት ተስፋ የሚያጨልም ነው ተብሏል፡፡

የአፍሪካ መንግስታት የአፍሪካ ነጻ የንግድ ልውውጥ እንዲያድግ በሰዎች ነጻ ዝውውርና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ የመስራት አቅም በየዓመቱ እያሽቆለቆለ መምጣቱም ነው የተነገረው፡፡

በዚህም አህጉሪቱ የውስጥ አቅምን ከማሳደግ ይልቅ በውጭ ገበያ ላይ ጥገኛ በመሆኗ ውስጣዊ የኢኮኖሚ ቀውሱ ተባብሶ እንደሚቀጥል ተመላክቷል፡፡ በፈረንጆች 2021 ከኤርትራ በስተቀር ኹሉም አገራት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ልውውጥ እንዲኖር መስማማታቸው ይታወሳል፡፡

ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ቢደረግ አህጉራዊ የንግድ ልውውጡን በ40 በመቶ እንደሚያሳድገው ተጠቁሟል፡፡

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ልውውጥ ከቀናት በኋላ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 42ኛው የአፍሪካ ህብረት የሚኒስትሮች ጉባኤ፣ እዲሁም 36ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ዋነኛ አጀንዳ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
1.7K views12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 20:35:33 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለስሙም ሆነ ለክብሩ የማይመጥን እና ከእውነት የራቀ ለፖለቲካ ፍጆታ የሚውል ረብ-የለሽ መግለጫ ማውጣቱ በርካቶችን አስቆጥቷል

ንሥር ብሮድካስት
ህዳር 3/2015

አገልግሎት መስጠት ላይ የተሰማራ ማንኛውም ለትርፍ የተቋቋመ የንግድ ድርጅት በሚሰራበት አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰብን ስነ ልቦና እና እሴት ማክበር ግዴታው ነው።

በዋናነት ለንግድና ለማኀበረሰብ አገልግሎት የተቋቋመ በይበልጥ ደግሞ መንግሥታዊ የሆነ  ተቋም የሚሰራበትን አካባቢ ማህበረሰብ የወል ፍላጎቶች ማክበር፣ እሴትና ባህሉን መጠበቅ ትንሹ ተቋማዊ ኃላፊነት ነው።

ይህን አለማድረግ የንግድ ተቋሙ በአካባቢው ህዝብ ዘንድ በጥርጣሬ እንዲታይ ብሎም ከገበያ ውድድር መውጣትን ያስከትላል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአገሪቱ የፋይናንስ ተቋም ትልቁ ተቋም መሆኑ ይታወቃል።

ይህ አንጋፋ ባንክ ለስሙ ክብር የማይመጥን እና ከእውነት የራቀ ለፖለቲካ ፍጆታ የሚውል ረብ-የለሽ መግለጫ በዛሬው ዕለት አውጥቷል።

ባንኩ በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ላለፉት ሁለት ዓመት ከአከባቢው አስተዳደርና ህዝብ ተቀራርቦ ያለምንም የፀጥታ እንከን ሲሰጥ የነበረውን አገልገሎት በጎንደር ዲስትሪክት በኩል ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል።

ዛሬ፣ ባንኩ አሰራሩን ህቡዕ በሆነ አካሄድ በመቀየር ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት በ"ሽሬ ዲስትሪክት" በኩል በማድረግ እንደሚሰራ አስታውቋል።

በዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኛ ተኮር ( customer based) የንግድ አሰራርን ሳይሆን ፖለቲካዊ አቋምና ፍላጎት የሚያራምድ ከዝንባሌም ከፍ ያለ ሚና ለማሳየት ቃጥቷል። ይህ ኢትዮጵያችን ከምትኮራበት ግዙፍ የንግድ ተቋም የማይጠበቅ፣ ለተቋሙ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቱ ለሚኮራው ሕዝባችን ጭምር አሳፋሪ ክስተት ነው። ተቋሙ በዚህ ሁነቱ፣ ለወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብም ያለውን ንቀትም በጉልህ ገልጿል።

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ለዘመናት በዘረኛ የትግሬ ልሂቃን የደረሰበትን ዘግናኝ ግፍ የሚያስታውሰው አይፈልግም ብቻ ሳይሆን አምርሮ ይጠላል፤ ይታገላል። ከባርነት ወደ ነፃነት የተሸጋገረበትን ታሪካዊ ምዕራፍ ሊያደናቅፈበት የሚፈልግን የትኛውም ኃይል አይታገስም።

ለነፃነቱ ቀናኢ እና ሟች የሆነው የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ የባንኩን መግለጫ በፅኑ ያወግዛል።

ባንኩ የትልቋ ኢትዮጵያን መጠሪያ የያዘ እንደመሆኑ መጠን፣ ስሙን የሚመጥን ግብር (መገለጫ) ሊኖረው ይገባል ብለን እናምናለን። በእስካሁኑ ቆይታውም ከዘር፣ ኃይማኖትና ሌሎች ቡድናዊ ወገንተኝነቶች በራቀ መንገድ ኢትዮጵያዊ ቀለምና ገፅታ ተላብሶ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበረ እንረዳለን።

ከዚህ መልካም ገፅታውና ከፍታው ሊያወርደው በሚችል መልኩ በዛሬው ዕለት ያወጣውን መግለጫ እንደሚያስተካክለው እምነት አለን። ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ባንኩ እንደተቋም ፀረ-ወልቃይት ጠገዴ አማራቱን በግላጭ እንዳሳየ ይቆጠራል። እንደአስፈላጊነቱም መላው የአማራ ህዝብ እና ፍትህ ወዳድ የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች በባንኩ ያልተገባ ሁነት ላይ ቁጣቸውን እንዲያሰሙ ንቅናቄ ወደ መፍጠር ለመሻገር እንደምንገደድ እናስታውቃለን።

ወልቃይት ጠገዴ አማራ ነው !
ስንኖር በምክንያት ስንሞትም ለምክንያት!!
***
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን

ሕዳር 03/2015 ዓ.ም
ሁመራ-ኢትዮጵያ

=====================
692 views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ