Get Mystery Box with random crypto!

መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት የማያስከብር ከሆነ ከቅዱስ ፓትርያርኩ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

መግለጫ

ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት የማያስከብር ከሆነ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ መላው ኦርቶዶክሳውያን የሚሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራት በደሉን ለዓለምዓቀፉ ማኅበረሰብ እንደሚገልጽ ዛሬ ማምሻውን በሰጠው አስታወቀ።

በመግለጫቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የተሰጠው መሬት ብዙ ነው ላሉት ሲኖዶሱ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል።

" በአዲስ አበባ ከ75% በላይ የሚኖረው የኦርቶዶከስ አማኝ ህዝብ ስለሆነ ተሰጠ የተባለው መሬት ከአገልግሎት ስፋቱ አንፃር የሚጋነን አይደለም ያሉ ሲሆን በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ጦርነት ምክንያት በማድረግ የትግራይ ቤተ ክህነት ተገንጥያለሁ ሲል ለምን ዝም አላችሁ በሚል ጠቅላይ ሚንስትሩ ላነሱት "የትግራይ ቤተክነት ቢያንስ የውሸት ጳጳስ አልሾመም፣ቤተክርስቲያንን አላዋረደም" የሚል ማብራሪያ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰጥቷል።

መንግሥት ህግን የማያስከብር ከሆነ ቅዱስ ሲኖዶሱ በመላው አለም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠራ በደሉን ለአለም እንደሚያሳውቅ አስታውቀዋል።