Get Mystery Box with random crypto!

💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomerejaa
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

24 Hour News

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-12 16:28:21
2.8K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 16:28:19
2.8K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 16:28:12 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሶማሊያና ከኬንያ ፕሬዝዳንቶች ጋር ተወያዩ።

ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሶማሊያና ከኬንያ ፕሬዝዳንቶች ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል ።

ከኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ እና ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ነው ውይይት ያካሄዱት።

ብዙ የጋራ ጥቅሞቻችንን እና ሥጋቶቻችንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጋራ ተግዳሮቶቻችንን በድል ለመወጣት ኢትዮጵያ ከእያንዳንዱ ሀገር ጋር በመቀራረብ ለመሥራት ዝግጁ መኾንዋን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
2.8K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 16:27:16 " የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ከዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና እና ከ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር ሳይጋጭ እንደሚከናወን አሳውቋል።

በ208 የትምህርት ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና መዘጋጀቱንም ገልጿል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ ሚጀና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ቃል ፤ " የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ፣ ከመውጫና ከ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በማይጋጭ መልኩ እንዲከናወን የሚረዳ ዕቅድ ተዘጋጅቷል " ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት እንደሚሰጥ ዶ/ር ኤባ አስታውሰዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎቻቸውን የምረቃ መርሃግብር ከመውጫ ፈተና በኋላ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎቹ ምርጫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሲጠናቀቅ ማካሄድ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ዶ/ር ኤባ ፤ በዘንድሮው ዓመት 180 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸው ለ208 የመመረቂያ ፕሮግራሞች የሚውሉ የፈተና ዓይነቶች መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።

" የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል " ያሉት ዶክተር ኤባ፤ በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈትነው 50 በመቶና በላይ ያመጡ ተማሪዎች እንደሚያልፉ አስረድተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል መግባቱን አመላክተዋል።

ለተማሪዎች ለፈተና የሚሆን ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ይሰጣቸዋል ያሉት ዶክተር ኤባ፤ በተሰጣቸው ቁጥር መሠረት በኦንላይን መፈተን እንዲችሉ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በማዕከል ደረጃ የተዘጋጀውን የፈተና ሥርዓት ለመሞከር እንደ አገር ሞዴል ፈተና እንደሚሰጥ አስታውቀው፤ በዚህም ጉድለቶች ካሉ ለማስተካከልና ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።

ለፈተናው መሳካት ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የተደራጀ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ለመውጫ ፈተናው የሚውሉ ኮምፒዩተሮች፣ የኢንተርኔት አገልግሎትና ጄኔሬተሮች ዝግጅት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
2.1K views13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 16:26:44 ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸዉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን የቀድሞ የአየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄን በመተካት የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸው ነው የተሰማዉ፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን አሁን የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል።
1.8K views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 16:26:15 " በማህበራዊ ሚዲያ የተገለፀው ግነት የበዛበት ነው " የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ

ዩኒቨርሲቲው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ፤ ከዩኒቨሲቲው እውቅና ውጪ ባልተፈቀደ ሁኔታ በቀን 03/10/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠውን የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) " አንፈተንም  "በሚል  በዋናው ግቢ በዉስን ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ተሞክሮ ነበር ብሏል።

የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ በጥቂት የማህበራዊ ሚዲያዎች የፀጥታ ችግር እንዳለና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ መስተጓጎል እንዳለ በማስመሰል ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጨ  እንዳለ ለመገንዘብ ችለናል ብሏል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው ዜና ግነት የበዛበት " ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " የተፈጠረውን መጠነኛ ያለመግባባት ለመፍታት የዩኒቨርሲቲው ደህንነት ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከሀዲያ ዞን ፖሊስ፣ ከሌሞ ወረዳ ፖሊስ እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸው የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት በመስራት በአስተማማኝ ሁኔታ ሠላማዊ የሆነ የመማር ማስተማር ሥራ ማስቀጠል ተችሉዋል ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው ፤ ለተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ባስተላለፈው መልዕክት በነበረው መጠነኛ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በተማሪዎች ላይ " ምንም ዓይነት ጉዳት " ያለመድረሱንና ዩኒቨርሲቲው ወደተለመደው መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ መመለሱን አሳውቋል።

ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ላይ በቪድዮ እና በፎቶ ስለተያዙት ማስረጃዎች ምንም ያለው ነገር የለም።
1.9K views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 21:17:07 ሰበር ዜና

በሥላሴ ገዳም መንግስት በንፁሃን ላይ የፈፀመውን ጭፋጨፋ ያጋለጠውን ጋዜጠኛ ወግደረስን ለማፈን የገባው ቡድን በህዝቡ ተዋርዶ ወጣ

ከሰሞኑንን በደብረ ኤልያስ ሥላሴ  አንድነት ገዳም የተጨፈጨፉ ህፃናት፣ሴቶችን እና መነኳሳቱን ስፍራው ድረስ በመሄድ በድፍረት የመንግስትን ውሸት ያጋለጠውን ጋዜጠኛ ወግደረሰን ለማፈን ጎጃም የገባው የኦህዴድ ኃይል ዛሬ ከቀኑ 10 ገደማ በህዝቡ ተዋርደ ተባሯል።

ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው የሚገኝበትን ቦታ በጥቆማ ካረጋገጡ በኋላ በሁለት የኦህዴድ ደህንነቶች እየተመራ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ያለበትን ቤት በመክበብ ይዞ ለመሄድ ጥረት አድርጓል።ይሁን እንጂ በድፍረት ጥሶ የገባውን አፋኝ ኃይል ካዎቀ በኋላ፣ የአካባቢው ወጣት እና ህዝብ ግልብጥ ብሎ በመውጣት አፋኝ ቡድኑንን እያሳደደ መልሶታል።

በጋዜጠኛው ላይ ከበባ ከመፈፀማቸው አስቀድሞ የአካባቢውን ህዝብ ለማደናገር"በመኪና ሰው ገጭቶ ነፍስ አጥፍቶል"በሚል የበሬ ወለደ ጩኸት ሲያሰሙ እንደነበረ ታውቋል።

የአካባቢው ህዝብ ግን "ነፍስ አጥፊ ጨፍጫፊዎች እናንተ ናችሁ፤እናንተ ሌቦች ሳንጨርሳችሁ ከዚህ ሂዶ በማለት አስወጥቷቸዋል።

ይሁን እንጅ ኃይል አጠናክረን እንመጣለን በሚል ደንግጠው እንደወጡ ተሰምቷል።

በየትኛውም አካባቢ የምትገኙ የጎጃም ወጣቶች ጋዜጠኞቻቸሁን ጠብቁ።

ከምስራቅ ጎጃም ዞን ጋዜጠኛ ወግደረስ እንዲያዝ የምታስተባብሩ በሙሉ ለይተናችኋል ካላረፋችሁ በዝርዝር ስምና ፎቷችሁን እናወጣለን።
2.4K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 21:16:19 ደምበጫ!

ጦርነቱ ከደ/ኤልያስ ወደ ደምበጫ ተሸጋግሯል። ህዝቡ በመንግስት ጦር እየታመሰ ነው። መረጃዎችን አድርሱን!
2.2K views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 19:57:26
1.8K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 19:57:21 "ተቃውሞ አቀናጅታችኋል" የተባሉ ወጣቶች ከየቤቱ ታድነው እየታሰሩ መሆኑ ተገለጸ!

እስከአሁን የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል።

ባሳለፍነው አርብ በአዲስ አበባ ከተማ፣ መርካቶ በሚገኘው አንዋር መስጊድ አካባቢ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በአማኙ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት፤ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ስምንት ሰዎች ሲሞቱ፤ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁት ደግሞ ከፍተኛ እና መካከለኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዘመድኩን ብሩ፤ "በዕለቱ ከጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል" ሲሉ ለአዲስ ማለዳ የገለጹ ሲሆን፤ ከሟቾች መካከልም አንድ ግለሠብ መታወቂያ ባለመያዙ ምክንያት እስከአሁን ማንነቱ ሊታወቅ አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም፤ "ሰልፍ አቀናጅታችኋል" የተባሉ ወጣቶች ከየቤቱ ታድነው እየታሰሩ መሆኑን በመግለጽ፤ "ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል" ሲሉ ተናግረዋል።

ሟቾችን ለመቅበር የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ መዋቀሩን የተናገሩት ኃላፊው፣ ትናንት ቅዳሜ ግንቦት 26/2015 ኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መካነ መቃብር የአራት ምዕመናን ሥርዓተ ቀብር መፈጸሙን ገልጸዋል፡፡ የቀሩትንም ወደ ትውልድ ሥፍራቸው በአስቸኳይ ለመሸኘትና ማንነቱ ያልታወቀውን ምዕመን ማንነት ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

    
1.8K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ