Get Mystery Box with random crypto!

'ተቃውሞ አቀናጅታችኋል' የተባሉ ወጣቶች ከየቤቱ ታድነው እየታሰሩ መሆኑ ተገለጸ! እስከአሁን የ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

"ተቃውሞ አቀናጅታችኋል" የተባሉ ወጣቶች ከየቤቱ ታድነው እየታሰሩ መሆኑ ተገለጸ!

እስከአሁን የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል።

ባሳለፍነው አርብ በአዲስ አበባ ከተማ፣ መርካቶ በሚገኘው አንዋር መስጊድ አካባቢ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በአማኙ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት፤ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ስምንት ሰዎች ሲሞቱ፤ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁት ደግሞ ከፍተኛ እና መካከለኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዘመድኩን ብሩ፤ "በዕለቱ ከጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል" ሲሉ ለአዲስ ማለዳ የገለጹ ሲሆን፤ ከሟቾች መካከልም አንድ ግለሠብ መታወቂያ ባለመያዙ ምክንያት እስከአሁን ማንነቱ ሊታወቅ አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም፤ "ሰልፍ አቀናጅታችኋል" የተባሉ ወጣቶች ከየቤቱ ታድነው እየታሰሩ መሆኑን በመግለጽ፤ "ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል" ሲሉ ተናግረዋል።

ሟቾችን ለመቅበር የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ መዋቀሩን የተናገሩት ኃላፊው፣ ትናንት ቅዳሜ ግንቦት 26/2015 ኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መካነ መቃብር የአራት ምዕመናን ሥርዓተ ቀብር መፈጸሙን ገልጸዋል፡፡ የቀሩትንም ወደ ትውልድ ሥፍራቸው በአስቸኳይ ለመሸኘትና ማንነቱ ያልታወቀውን ምዕመን ማንነት ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡