Get Mystery Box with random crypto!

💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomerejaa
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

24 Hour News

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-02-06 19:16:08 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን “መንግስት ለህገ ወጥ ስብስቦች ላደረገው ድጋፍ” በይፋ ይቅርታ ይጠይቅ አለች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን “መንግስት ሕገ ወጥ ስብስቦች እየፈጸሙ ላሉት ድርጊት የሰጠውን ድጋፍ እና እገዛ በይፋ ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ በመጠየቅ እንዲያቆም” አሳሰበች።መንግስት መግለጫ ባወጣበት እለት በሻሸመኔ ከተማ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ድርጊት አለማውገዙ የመንግስትን ሚና ያሳያል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ገለፀች።

ቤተ ክርስትያኗ በመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ዛሬ ምላሽ የሰጠች ሲሆን “በሻሸመኔ ከተማ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የተፈፀመውን ሕገ ወጥ፤ አስነዋሪ እና ጭካኔ የተሞላበት የአደባባይ ግድያ እና የሕዝብ ፍጅት ያልጠቀሰና ሐዘኑን እንኳን መግለጽ ያልቻለበትና ያላወገዘ መሆኑ” የመንግሥትን ግልጽ ሚና በቀላሉ ለመረዳት እንድንችል ያደርገናል ብላለች።

ስልጣንን ተገን በማድረግ የቤተ ክርስቲያንችንን ሕጋዊ ጥያቄ በግድያ፤ በእስር፤ በማዋከብ እና በማስፈራራት ሊፈታ አይችልም የተባለ ሲሆን “ይልቁንም መንግሥት የተጣለበትን መንግሥታዊ ኃላፊነት ያለ አድሎ መፈጸም ሲችል ብቻ መሆኑን” ቤተ ክርስቲያኗ አሳስባለች።
921 views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 19:15:18 መረጃ

ጥቁር ልብስ ለብሰው አገልግሎት ለማግኘት ወደ መንግስት ተቋማት የሄዱ ዜጎች እንዲመለሱ እየተደረገ እንደሆነ ዛሬ ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

"ከበላይ በመጣ ትእዛዝ" በማለት እንደ ገቢዎች፣ መንገድ ትራንስፖርት፣ ፍርድ ቤት... ወዘተ ያሉ ተቋማት በዚህ መልኩ ሰዎችን እየመለሱ እንደሆነ ታውቋል።

በተጨማሪም፣ በዛሬው ሱባዔ ላይ ካራቆሬ ባለው የአቡነ ተክለሐይማኖት ቤተክርስቲያን ጥቁር ልብስ በመልበስ የሄዱ በሙሉ ለእስር እንደተዳረጉ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።#elias meseret
916 views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 20:59:34 የ ' ፌደራሉ መንግሥት ' በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች

ቤተክርስቲያኗ በሻሸመኔ ከተማ አንድ ሰው በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ገለፃለች።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጉዳዩን በተመለከተ ፤ " እየሞተ ያለው ሕዝብ ነው ቅጠል አይደለም እየተበጠሰ የሚወድቀው ፤ ይሄ ፖለቲካ ነው። የፌደራል መንግሥት በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል። " ብለዋል።

በሻሸመኔ ምንድነው የሆነ ?

ተ/ሚ/ማ የተባለው የቤተክርስቲያኗ ሚዲያ " በዛሬው ዕለት ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ሻሸመኔ ይመጣል መባሉን ተከትሎ ጠዋት ሁለት (2:00) ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተፈጸመ ሕዝቡን ለመጥራት በከተማዋ ያሉ አድባራት ደወል ደውለዋል " ሲል ገልጿል።

" ጥሪው ሰምቶ ሁሉም ምእመን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ ይጀምል ፤ በዚህ ጊዜ ወደ ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሔዱ ምእመናን የቤተክርስቲያኑ በር በመዘጋቱ ከውጪ ቆመው ነበር።

በእንዲህ ሁኔታ ውስጥ እያለ የከተማው ፖሊስ ሕዝቡን ለመበተን ተኩስ ከፍያል ፤ እስካሁን ድረስ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ሰማዕትነትን ተቀብሏል፤ በውል ያልታወቀ ሰውም በጥይት ተመቷል " ሲል የነበረውን ሁኔታ አስረድቷል።

በሌላ በኩል ቤተክርስቲያኗ ፤ " ትናንትና ሌሊት ሊቀ ጳጳሷን አስሮ ከከተማ ያባረረው ኃይል   በአርሲ ሀገረ ስብከት መናገሻ አሰላ ኦርቶዶክሳውያንን እያሠረ  ይገኛል " ብላለች።

በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ያሉትም እንዲወጡ እየተነገራቸውና ያ የማይሆን ከሆነ የኃይል እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተዝቶባቸዋል ብላለች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ያሉት ሁኔታዎች እየከረሩ መጥተው ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት እስከመሆን የደረሱ ቢሆንም መንግስት እስካሁን ስለጉዳዩ ምንም ያለው ነገር የለም።

ቤተክርስቲያን በበኩሏ ለዚህ ሁሉ መሆን ህገወጥ ሲመት አከናውነዋል ፤ ተቀብለዋል ባለቻቸው ግለሰቦች እና የመንግስት ተቋማት ላይ ክስ ለመመስረት በሂደት ላይ ነች
1.1K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 20:59:04 5. ማንኛውም የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ቤተ ክርስቲያን ያዘዘችውን ሰላማዊ ጥያቄ በሚከወንበት ማንኛውም የአገልግሎት ጊዜ ተግባራቱ ሰላማዊ መሆናቸውን በመገንዘብ ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት አውቆ እንዲያስፈጽም ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
953 views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 20:59:04 ኢትዮ መረጃ - NEWS:
መግለጫ

በየካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በመላው ሀገሪቱ ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ!

የቅዱስ ሲኖዶሱ ሙሉ መግለጫ!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ከኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ አዋጅ
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረው አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና የብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ በሚል በሕገ ወጥነት በቀድሞ ስማቸው አባ ሳዊሮስ የተባሉ ግለሰብ መሪነት ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ በተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግሥት በሚመራቸው ቦታዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ አህጉረ ስብከት የሆኑትን ሥርዓተ አምልኮዋን የምትፈጽምባቸው በየመዋቅሩ የሚገኙ አስተዳደር ቢሮዎችን  ከሕግ አግባብ ውጭ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ግለሰቦችን በማካተት በመንግሥት ልዩ ኃይል ድጋፍ በመውረር እና በመስበር የሕግ አግባብነት በሌላቸው  እንዲሁም መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው በማሸግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ እየተፈጸመባት የሚገኝ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመረዳት ችሏል፡፡

መንግሥትም ሰላም እና ደህንነትን ከማስጠበቅ ባለፈ የሕይወት እና የአካል ደህንነት መብትን እንዲሁም የመንቀሳቀስ መብትን በመገደብ ያለአግባብ ታግተው መቆየታቸውን ከሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ከዚህ ቀደም መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ድርጊታቸውም ሳይታቀቡ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብጹዕ አቡነ ያሬድን በሕገ ወጥ መልኩ የዜግነት መብታቸው ተጥሶ በደረቅ ሌሊት በማሰር እና በማዋከብ ከሀገረ ስብከታቸው ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን እንዲሁም የተለያዩ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትን ወደየ አህጉረ ስብከታቸው እንዳይሄዱ ማስፈራሪያ በመላክ የቤተ ክርስቲያችንን ክብር እና ልዕልና እጅጉን የሚጎዳ እና አሳዛኝ ድርጊት እየተፈጸመባት ይገኛል፡፡

በተጨማሪም የየሀገረ ስብከት ሥራ አኪያጆችንና ሠራተኞችን፤ አገልጋይ ካህናትንና ምእመናን በሕገ ወጥ መልኩ በማሰር እንደ መንግሥት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ባለመወጣቱ ቤተ ክርስቲያናችን እጅጉን አዝናለች፡፡ከዚህም አልፎ መንግሥትም በቤተ ክርስቲያችን በኩል በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማሳሰቢያ ችላ በማለቱ ምክንያት በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ ሕገ ወጦቹ መንግሥትን ተገን በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጥ መልኩ ወረራ ለመፈጸም ባደረጉት እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያንችንን ለመጠበቅ በወጡ ምእመናን ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የአደባባይ የግድያ ወንጀል ተፈጽሟል፡፡ ሌሎች በቁጥር ያልታወቁ ምእመናንም ላይ ከፍተኛ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 

ይህንንም ሕገ ወጥ ተግባር በተመለከተ ተገቢውን ሕጋዊ የሰላም እና የደህንነት ከለላ እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቤተ ክርስቲያናችን ብትሰጥም ይህንን ማሳሰቢያ ወደጎን በመተው መንግሥት ሕገ ወጡን ቡድን በመደገፍ እና በማስፈጸም ከላይ የተገለጹትን አሳዛኝ ድርጊቶች በይፋ በአደባባይ ፈጽሟል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጠራው አስቸኳይ ጉባዔ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

1. በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ የክፍል ኃላፊዎች፤ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ላይ የተፈጸመውንና እና እየተፈጸመ ያለውን ሕገ ወጥ እስር እና ወከባ ቅዱስ ሲኖዶስ በፅኑ አውግዟል፤

2. በጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፤ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የወጡት ምዕመናን ላይ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ የተፈጸመው ሕገ ወጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የተፈጸመው አሰቃቂ የሞት ድርጊትን ፍጹም ታወግዛለች፤ ተገቢውን ሲኖዶሳዊ እና ሃይማኖታዊ ጸሎት በማድረግ በሁሉም አጥቢያ ሥርዓተ ፍትሐት እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

3. ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ እና በሰጠው መግለጫ መላው የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ጾመ ነነዌን ሙሉ የሱባዔ ጊዜ በማድረግ ጥቁር ልብስ ያለውን ትርጓሜ በመግለጥ እንድንሰነብት መግለጫ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

3.1. ለዚህም ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 3 ቀናት በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የምትገኙ ማናቸውም ካህናት እና ምዕመናን ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ በየአብያተ ክርስቲያናት እና በገዳማት ያለውን ሥርዓተ ጸሎት እንድትመሩ እና እንድትከታተሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

3.2. በየትኛውም እንቅስቃሴ ይህንን ጥቁር ልብስ በመልበስ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ንቁ በመሆን እንድትፈጽሙ፤ ሆኖም ግን ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዓለም አቀፍ የጸሎትና የምህላ መርሐ ግብር ካወጀበት ቀን በኃላ በተለያዩ ከተሞች የጥቁር ልብስን ሆነ ተብሎ ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ መሆኑን በመረዳታችን ምዕመናን ያላችሁን ተመሳሳይ አልባሳት በመጠቀም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን በእንቅስቃሴያችሁ ሁሉ እንድትፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

3.3. በነዚህ ቀናት ውስጥ አገልግሎቱ በድምጽ ማጉያ እንዲከናወን እና የሙሉ ጊዜ ሆኖ በሰባቱ የጸሎት ሰዓታት እየተጠበቀ በተመሳሳይ ሰዓታት ለአምስት ደቂቃ ያህል በማያቋርጥ ደወል በመደወል የማስተጋባት ሥራ እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

3.4. ይህንንም የየአህጉረ ስብከት፤ የወረዳ ቤተ ክህነት እና የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤያት በመከታተል እንድታስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

3.5. የአኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የኦርቶዶክስ ዓለም፤ እውነቱን የምታውቁና የምትደግፉ ማናቸውም ኃይማኖታዊም ሆነ ማህበራዊ ተቋማት እና ግለሰቦች የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመደገፍ በአንድነት ትቆሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላፋለን፡፡

4. በነዚህ የጸሎትና የምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ እንደሆነ

4.1. በየካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ በየአጥብያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠዋቱ 1፡30 ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተፈጸመ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ሁሉም ገዳማት፣ አድባራት እና አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት ደወል በመደወል ምእመናን በሙሉ እስከ ጠዋቱ 2፡30 ድረስ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከየአጥቢያው በመነሳት የጥምቀተ ባህር ወይም የመስቀል አደባባይ ላይ ታቦተ ሕጉን በማክበር፤ በማጀብ በዝማሬ እና በምህላ በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡


4.2. የዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናሳውቃችሁ መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡ 
973 views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 14:45:34 ሱዳን በተቆጣጠረችው የኢትዮጵያ ግዛት ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ

አርብ ጥር ቀን 26 2015 (አዲስ ማለዳ) ሱዳን በተቆጣጠረችው የኢትዮጵያ ግዛት ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ግጭት መቀስቀሱ ከሱዳን በኩል ተስምቷ፡፡

ተቀስቅሷል በተባለው ግጭት የሰው ህይወት መጠፋቱ የተሰማ ሲሆን፣ ግጭቱን የቀሰቀሱት ኢትዮጵያ ታጠቂዎች መሆናቸውን የሚሳይ መረጃ ወጥቷል፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው ሱዳን በኃይል በተቆጣጠረችው አልፋሽጋ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሲሆን፣ በስፋራው በብዛት የሚገኙ ሱዳናውያን እረኞች የጥቃቱ ሰላባ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ባለፈው ማክሰኞ በወሰዱት እርምጃ አንድ እረኛ መግደላቸው ነው የተገለጸው፡፡

ጥቃት አድራሾች በእረኞችና በእንስሳት ላይ ማነጣጠራቸው የሱዳንን የእንስሳት ገበያ፣ አገራዊ ምጣኔ ሀብትን እና የእንስሳትን ምርት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ የሱዳን ፖሊስ አባላት ወደ ቦታው ደርሰው በአካባቢው ጥበቃ እያደረሱ መሆናቸው የተሰማ ሲሆን፤ የሱዳን እረኞችም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ከመጠጋት እንዲቆጠቡ የሱዳን ፖሊስ ማሳሰብ ተጠቁሟል፡፡

የሱዳንና ኢትዮጵያ መንግሥታት በመካከላቸው ያለውን የድንበር ውዝግብ በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸውን መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መቀራረብ የጀመሩት የኢትዮጵያ እና ሰዱን ባለሥልጣናት በኹለቱ አገሮች መካከል ያለውን የድንበርና ሌሎች የኹለትዮሽ ጉዳዮችን በጋራ ለመፍታት ተስማምተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሱዳን በተቆጣጠረቸው ኢትዮጵያ መሬት ላይ የራሷን ኃይል በማስፈሯ በተደጋጋሚ ግጭት መቀስቀሱ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ በድንበሩ አካባቢ አንድ ጊዜ በሱዳን በኩል አንድ ጊዜ ከኢትዮጵያ በኩል በሚተነኮሱ ጥቃቶች የሰው ሕወይወት ይጠፋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በድንበር አቅራቢያ ባሉ የጸጥታ ችግሮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ቢስማሙም፣ በታጣቂዎች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ጥቃቶችን ማስቆም አልቻሉም ነው የተባለው፡፡

በሱዳን በኩል ስለተሰማው ጥቃት መፈጸም ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተሰጠ መረጃ የለም፡፡ ሱዳን 70 ኪሎ ሜትር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በመዝለቅ በርካታ ቦታዎችን በኃይል ተቆጣጥራ እንደምትገኝ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
595 views11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 14:44:15 #ሩሲያ!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የሩስያን ፌዴሬሽን የፓርላማ አባል እና የሩስያ አምባሳደር በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የጉብኝታቸው ዋና ዓለማ በተፈጠረው የቤተክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ችግር መፍትሔ ለማግኘትና ሓሳብ ለመለዋወጥ የጠቀሱት ሲሆን እንዲሁም ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን አብሮነቻውና ድጋፋቸውን ለመግለጽ መሆኑን ገለፀዋል።

ምንጭ፡ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
537 views11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 22:48:35 ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በሙሉ!!

"የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት የሚያበቃ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲታቀርቡ እናሳውቃለን፡፡

ቀድማችሁ ቅሬታ ያቀረባችሁ ተፈታኞች የቅሬታችሁን መልስ www.neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራችሁን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ
• ቅሬታዎች ሁሉም ተጣርተው ሲጠናቀቁ በቀጣይ ቀናት የሚናሳውቅ በመሆኑ የቅሬታችሁ ምላሽ ያልደረሳችሁ ተፈታኞች በትዕግስት እንዲትጠብቁ እናሳስባለን፡፡
• ባልተሟላ ወይም በተሳሳተ ወይም በሌላ ሰው መለያ ቁጥር ያመለከታችሁ የስም ዝርዝራችሁን ዛሬ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገጽ አድራሻ ላይ የምናሳውቅ ሲሆን ቅሬታችሁን በድጋሚ በተስተካከለ መለያ ቁጥራችሁ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡"

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
1.2K views19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ