Get Mystery Box with random crypto!

የ ' ፌደራሉ መንግሥት ' በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የ ' ፌደራሉ መንግሥት ' በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች

ቤተክርስቲያኗ በሻሸመኔ ከተማ አንድ ሰው በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ገለፃለች።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጉዳዩን በተመለከተ ፤ " እየሞተ ያለው ሕዝብ ነው ቅጠል አይደለም እየተበጠሰ የሚወድቀው ፤ ይሄ ፖለቲካ ነው። የፌደራል መንግሥት በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል። " ብለዋል።

በሻሸመኔ ምንድነው የሆነ ?

ተ/ሚ/ማ የተባለው የቤተክርስቲያኗ ሚዲያ " በዛሬው ዕለት ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ሻሸመኔ ይመጣል መባሉን ተከትሎ ጠዋት ሁለት (2:00) ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተፈጸመ ሕዝቡን ለመጥራት በከተማዋ ያሉ አድባራት ደወል ደውለዋል " ሲል ገልጿል።

" ጥሪው ሰምቶ ሁሉም ምእመን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ ይጀምል ፤ በዚህ ጊዜ ወደ ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሔዱ ምእመናን የቤተክርስቲያኑ በር በመዘጋቱ ከውጪ ቆመው ነበር።

በእንዲህ ሁኔታ ውስጥ እያለ የከተማው ፖሊስ ሕዝቡን ለመበተን ተኩስ ከፍያል ፤ እስካሁን ድረስ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ሰማዕትነትን ተቀብሏል፤ በውል ያልታወቀ ሰውም በጥይት ተመቷል " ሲል የነበረውን ሁኔታ አስረድቷል።

በሌላ በኩል ቤተክርስቲያኗ ፤ " ትናንትና ሌሊት ሊቀ ጳጳሷን አስሮ ከከተማ ያባረረው ኃይል   በአርሲ ሀገረ ስብከት መናገሻ አሰላ ኦርቶዶክሳውያንን እያሠረ  ይገኛል " ብላለች።

በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ያሉትም እንዲወጡ እየተነገራቸውና ያ የማይሆን ከሆነ የኃይል እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተዝቶባቸዋል ብላለች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ያሉት ሁኔታዎች እየከረሩ መጥተው ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት እስከመሆን የደረሱ ቢሆንም መንግስት እስካሁን ስለጉዳዩ ምንም ያለው ነገር የለም።

ቤተክርስቲያን በበኩሏ ለዚህ ሁሉ መሆን ህገወጥ ሲመት አከናውነዋል ፤ ተቀብለዋል ባለቻቸው ግለሰቦች እና የመንግስት ተቋማት ላይ ክስ ለመመስረት በሂደት ላይ ነች