Get Mystery Box with random crypto!

ሱዳን በተቆጣጠረችው የኢትዮጵያ ግዛት ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ አርብ ጥር ቀን 26 2015 (አዲስ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

ሱዳን በተቆጣጠረችው የኢትዮጵያ ግዛት ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ

አርብ ጥር ቀን 26 2015 (አዲስ ማለዳ) ሱዳን በተቆጣጠረችው የኢትዮጵያ ግዛት ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ግጭት መቀስቀሱ ከሱዳን በኩል ተስምቷ፡፡

ተቀስቅሷል በተባለው ግጭት የሰው ህይወት መጠፋቱ የተሰማ ሲሆን፣ ግጭቱን የቀሰቀሱት ኢትዮጵያ ታጠቂዎች መሆናቸውን የሚሳይ መረጃ ወጥቷል፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው ሱዳን በኃይል በተቆጣጠረችው አልፋሽጋ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሲሆን፣ በስፋራው በብዛት የሚገኙ ሱዳናውያን እረኞች የጥቃቱ ሰላባ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ባለፈው ማክሰኞ በወሰዱት እርምጃ አንድ እረኛ መግደላቸው ነው የተገለጸው፡፡

ጥቃት አድራሾች በእረኞችና በእንስሳት ላይ ማነጣጠራቸው የሱዳንን የእንስሳት ገበያ፣ አገራዊ ምጣኔ ሀብትን እና የእንስሳትን ምርት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ የሱዳን ፖሊስ አባላት ወደ ቦታው ደርሰው በአካባቢው ጥበቃ እያደረሱ መሆናቸው የተሰማ ሲሆን፤ የሱዳን እረኞችም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ከመጠጋት እንዲቆጠቡ የሱዳን ፖሊስ ማሳሰብ ተጠቁሟል፡፡

የሱዳንና ኢትዮጵያ መንግሥታት በመካከላቸው ያለውን የድንበር ውዝግብ በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸውን መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መቀራረብ የጀመሩት የኢትዮጵያ እና ሰዱን ባለሥልጣናት በኹለቱ አገሮች መካከል ያለውን የድንበርና ሌሎች የኹለትዮሽ ጉዳዮችን በጋራ ለመፍታት ተስማምተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሱዳን በተቆጣጠረቸው ኢትዮጵያ መሬት ላይ የራሷን ኃይል በማስፈሯ በተደጋጋሚ ግጭት መቀስቀሱ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ በድንበሩ አካባቢ አንድ ጊዜ በሱዳን በኩል አንድ ጊዜ ከኢትዮጵያ በኩል በሚተነኮሱ ጥቃቶች የሰው ሕወይወት ይጠፋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በድንበር አቅራቢያ ባሉ የጸጥታ ችግሮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ቢስማሙም፣ በታጣቂዎች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ጥቃቶችን ማስቆም አልቻሉም ነው የተባለው፡፡

በሱዳን በኩል ስለተሰማው ጥቃት መፈጸም ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተሰጠ መረጃ የለም፡፡ ሱዳን 70 ኪሎ ሜትር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በመዝለቅ በርካታ ቦታዎችን በኃይል ተቆጣጥራ እንደምትገኝ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወቃል፡፡