Get Mystery Box with random crypto!

💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomerejaa
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

24 Hour News

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-11-09 21:56:10 ሁለት ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች ተብላ የተከሰሰችው የቤት ሰራተኛ ላይ ምስክር ተሰማ

ተከሳሽ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም  በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የህጻን ግዮናዊት መላኩ አፏን በማፈን  በቢላ በማረድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን እና ህጻን ክርስቲና መላኩን ደግሞ አፍፏን በማፈን በማነቅ  በአጠቃላይ ህፃናቶቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ  አድርጋለች ሲል በግድያ ወንጀል እና በወቅቱ የሟች ቤተሰቦችን የሰነድ ማስረጃዎች ቀዳዳ በመጣል በአጠቃላይ በተደራራቢ ክስ  ዓቃቢህግ በጥቅምት 15 ቀን ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

ተከሳሿ በጥቅምት 22 ቀን በነበረ ቀጠሮ የግድያ ወንጀሉን አልፈጸምኩም  ስትል የዕምነት  ክህደት ቃሏን መስጠቷን ተከትሎ  ወንጀል መፈጸሟን ያስረዱልኛል ያላቸውን 6 ምስክሮችን አቅርቦ ከሳሽ ዓቃቢህግ  ዛሬ አሰምቷል።አንድ ምስክር ተመሳሳይ ጭብጥ ያለው በመሆኑ እንዲታለው ተደርጓል።ችሎቱ የሟች ግዮናዊት እና ክርስቲና  መላኩ ወላጆችን ጨምሮ ስድስት ምስክሮች በእውነት ለመመስከር ቃለ መኃላ እንዲፈጽሙ አድርጓል።

በቀዳሚነት ዓቃቢህግ የሚሰሙለት ምስክሮቹን የምስክርነት ጭብጥ ለችሎቱ  አስመዝግቧል።በዚህም ባስመዘገበው የምስክር ጭብጥ መሰረት  የቤት ሰራተኛዋ መቼ እንደተቀጠረችና  ወላጆቻቸው ከቤት ሲወጡ የልጆቹ የነበሩበት የጤና ሁኔታ ÷ ተከሳሿ ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ እንዴት እጇን እደሰጠች እና ለሟች ህጻናቶች አባት መላኩ ታረቀኝ እንዴት ስልክ እንደደወለችና  በስልክ የተናገረኘ መልክት በሚመለከት እንዲሁም ፖሊስ ጣቢያ ከደረሰች በኋላ የሰጠችውን የዕምነት ቃል የሚመለከትና በቤት ውስጥ ተቀዳዶ ስለተገኘ የሰነድ ማስረጃን የሚመለከት ÷በቤት ሰራተኝነት ህጻናትን በመንከባከብ በምትሰራበት ቤት ውስጥ ሁለቱን የህጻናቶቹ ላይ እንዴት  ግድያን ወንጀል ፈጸመች በሚለው ነጥብ ÷ ወንጀሉ በተፈጸሙበት ወቅት ደግሞ የሟች ወላጆችን ማስረጃ   ተቀዳዶ  እንዲጠፋ የተደረገበትን ነጥብ አስመልክቶ ምስክሮቹ ምስክርነታቸው እንደሚሰማለት ጭብጥ አስመዝግቧል።

ጭብጥ ከተመዘገበ በኋላ በቀዳሚነት የሟች ህጻናቶች ወላጅ አባት መላኩ ታረቀኝ ልጆቹ እንዴት ተገለው እንደተገኙ እንደተመለከተ እና ትልቋ ህጻን ጊዮናዊች መስማት እና መናገር የማትችል እንደነበረች እና በወቅቱ የትምህርት ማስረጃው እንዴት ተቀዳዶ እንደተገኘ ገልጾ ምስክርነቱ አሰምቷል።በዚህ ምስክርነቱ ወቅት ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት እያለቀሰ ምስክርነቱን የሰጠ ሲሆን የችሎት ታዳሚውም በተመሳሳይ በለቅሶ ምስክርነቱን ሲሰሙ  ተስተውሏል።

የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ የሟች ህጻናቶች ወላጅ  አባት ተረጋግቶ ቃሉን መስጠት እንዲችል አረጋግተውታል።በማስከተል የሟች ህጻናቶች ወላጅ እናት መሰረት የሻነውም አጠቃላይ የህጻናቶቹን ሞት አስመልክቶ እንዲሁም በቤት ውስጥ ተቀዶ ስለተገኘ የስራ ልምድና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን በሚመለከት ምስክርነቷን ሰታለች።

እንዲሁም በፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ፈጽሜ ነው የመጣሁ በማለት ዕጇን መስጠቷን በሚመለከት በዕለቱ ፖሊስ ጣቢያ ተረኛ የነበሩ  አባላት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።ሌሎች ምስክሮችም የተመለከቱትን የህጻናት አሟሟትን በሚመለከት የምስክርነት ቃላቸውን አሰምተዋል።በተከሳሽ ተከላካይ ጠበቃ በኩል ለምስክሮቹ የመስቀለኛ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን በፍርድ ቤቱ የተለያዩ የማጣሪያ ጥያቄ ቀርቦ በምስክሮች እንደአግባቡ መልስ ተሰቷል።
432 views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 14:00:47
"ከታች ከቀረበው በመንግሥት እና በህወሓት በኩል ከተፈረመው የሠላም ስምምነት ውጪ የተሰራጩ መረጃዎች ያልተሟሉና ሊያሳስቱ የሚችሉ ናቸው" አምባሳደር ሬድዋን

ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በመንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረሰውን ትክክለኛ ስምምነት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አጋርተዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ስምምነቱ የተፈረመው ከበርካታ እልህ አስጨራሽ የቡድን ክርክሮች እና ንግግሮች በኋላ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም ከሁለቱ ተወያይ ወገኖች የቀረቡ በርካታ ረቂቆች የነበሩ ቢሆንም ስምምነት ላይ የተደረሰበት እና ተቀባይነት አግኝቶ የተፈራረምንበት ሠነድ ግን ከዚህ በታች የተቀመጠው ነው ሲሉም አስታውቀዋል።

አምባሳደር ሬድዋን እየተሰራጩ ያሉት መረጃዎች ቀደም ብለው የተዘጋጁ መረጃዎች ሊሆኑ እንደሚችሉም ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
1.3K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 19:14:11
928 views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 19:14:07 የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህወሓት ግጭት ለማቆም መስማማታቸውን ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አስታወቁ

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ግጭት ለማቆም መስማማታቸውን የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ተናገሩ። ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ወደ ስምምነት ማምራቱን ኦባሳንጆ የገለጹት፤ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አመቻችነት ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ለሁለት ዓመታት ገደማ ውጊያ ውስጥ የቆዩት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና የህወሓት ተደራዳሪዎች በይፋ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የተገናኙበት ነው። በሰላም ንግግሩ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የቀድሞዋ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ፑምዚ ለምላምቦ “በደጋፊነት” ተካፍለውበታል።

ከአንድ ሳምንት በላይ የተካሔደው የሰላም ንግግር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ)፣ የአሜሪካ መንግስት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ተወካዮች “በታዛቢነት ተሳትፈውበታል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
939 views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 18:58:05
840 views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 18:57:58 አሸባሪውና ወራሪ የሕወሓት ታጣቂ ቡድን ከ40 በላይ በሚኾኑ የምዕራብ ጠለምት የአማራ ተወላጆች አሰቃቂና ዘግናኝ ግፍ ፈጸመ።
=================
በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ ጠለምት፣ በማይጠብሪ፣ በአዳርቃይ አካባቢና በአዳርቃይ ከተማ ከሐምሌ 05/2013 ዓ.ም ጀምሮ ከ14 ወራት በላይ ወራሪ ቡድኑ በቆየባቸው አካባቢዎች ዘግናኝ የኾነ ሰብአዊና ቁሳዊ የንብረት ውድመት አድርሷል።

በወራሪው የሕወሓት ታጣቂ ቡድን ዘግናኝ ግፍ ከተፈጸመባቸው መካከል አንዱ ወጣት አብርሃ ዓለሙ በማይጠብሪ አካባቢ ነዋሪ ትውልዳቸው አማራ ሲኾን ወገኖቻችን አንዋጋም በማለት ተሸሽገን ነበር ይላል። ነገር ግን በጎረቤታቸው አካባቢ መረጃ አስቀምጠው አፍነው እንደያዙት ነው የተናገረው። የአማራ ብልጽግና ናችሁ በማለት በገመድ አስረው አንድ ቀን ሙሉ ፀሐይ ላይ እንደጣሉትና መሣሪያ አምጣ እያሉ ልብሱን አውልቀው እጅና እግሩ አስረው እንደደበደቡት ገልጿል። በደረሰበት ሰቆቃ ሁለት እጁን ተደብድቦ መመገብና ሥራ መሥራት እንዳይችል ሽባ ተደርጓል።

ሌላኛው ግፍ የደረሰበት የምዕራብ ጠለምት ወረዳ የሰራኮ ቀበሌ የ10ኛ ክፍል ተማሪ ወጣት አስፋው ዓለሙ በወቅታዊ ችግር ትምህርቱን አቋርጦ አርሶአደር አባቱን እያገዘ ባለበት ሰዓት ለምን አትታገልም፣ አንተ ባንዳ የሕወሓትን ንብረት ወስድሃል በማለት እጅና እግሩን አስረው በቢላዋ ጎኑን እየወጉ በሰደፍ እየቀጠቀጡ ፀሐይ ላይ እንደጣሉት አስረድቷል። የጭካኔያቸው ጥግ ከአንድ የሰው ፍጡር ለሕዝብ ነፃነት እታገላለሁ የሚል ታጋይ የሚፈጸም አይደለም ብሏል።

ሌላኛው ችግር የደረሰበት ወጣት ደስታ ታከለ ለምን አትታገልም እያሉ ሲያሮጡት እንደነበር ገልጸው የአማራ ክልል መታወቂያ ይዘሃል፣ በማለት በጠቋሚ ይዘው በመቀጥቀጥ ዘግናኝ ግፍ ተፈጽሞበታል። ባንዳ ሽፍታ መረጃ ነህ በማለት ተራ በተራ መደብደባቸውን አሳይቷል።

ልጆቻቸው ጉዳት የደረሰባቸው የምዕራብ ጠለምት ወረዳ የማይጠብሪ ዙሪያ ነዋሪ አቶ ዓለሙ አበባው ሁለት ልጆቻቸውን ጨምሮ ከ40 በላይ የሚኾኑ የምዕራብ ጠለምት ነዋሪ የአማራ ተወላጆች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል። ልጆቻችሁን ለጦርነት አምጡ በማለት ከ40ሺ ብር በላይ እንደዘረፉአቸው ተናግረዋል።

በደረሰባቸው የአካል ጉዳት የሕክምና ድጋፍ መንግሥት እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል። በዚህ ዘግናኝና ሰቆቃ ሰዓት የኢትዮጵያ ጥምር ጦር ደርሶ ነጻ መውጣታቸውን አድንቀዋል። በመጨረሻም ይህ ነፍሰ በላ አሸባሪ ቡድን ዳግም ከተከዜ እንዳይሻገር ከመንግሥት ጎን ኾነው እንደሚታገሉም ጠቅሰዋል።

ዘገባው፦ የሰሜን ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን ነው።
832 views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 18:51:24 አሸባሪው ሕወሀት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አባላት ላይ ጥቅምት 24-2013 ዓ.ም ያደረሰውን ክሕደት እና ጥቃት/ጭፍጨፋ/ መታሰቢያ አስመልከቶ ከአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር  የተሰጠ መግለጫ

ዕለተ ሰኞ ጥቅምት 23-2013 ዓ.ም ለጥቅምት 24 አጥቢያ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ አባላት ሽበርተኛው ሕወሀት በክህደት ጥቃት መፈጸሙ ሁሌ የሚታወስና ፈፅሞ የማይዘነጋ እለት ነው።

እለቱን ስናስብ ለአመታት ቤት ንብረታቸውን ትተው የአገርን ዳር ድንበር እና ሉአላዊነት ለማስከበር ሐሩር እና ቁሩ ሳይበግራቸው በቀበሮ ጉድጓድ የቆዩት እና የትግራይ ሕዝብ ችግር ችግሬ ብለው ካላቸው እያካፈሉ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮቹን ከማንም ቀድመው ሲጋፈጡ የኖሩ የሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ጭካኔ በአሸባሪው ህዋሃት  ባልጠበቁት እና ባላሰቡት ሰዓት የተካዱና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸውን  ጀግኖች ሰማዕቶቻችንን በልባችን ታትመዋልና መቼም አንረሳቸውም! ትውልድም ሲዘክራቸው ይኖራል።

ዘንድር ለሁለተኛ ጊዜ እለቱን "ጥቅምት 24ን መቼም አንረሳውም" በሚል መሪ ቃል ስንዘክር ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን የተዘረጋለትን የሰላም እጅ ገፍቶ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተላላኪ ሕወሀትን ወረራ በመቀልበስና የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት እኒያ ክህደት የተፈጸመባቸውን ሰማዕታት አደራ በጀግንነት በወጣት ላይ በመሆኑ የኢትዮጵያ ከፍ ብላለች!

ዛሬም በሀገር ወዳድ ልጆችዋ ሉዓላዊነትዋ መከበሩን ሰንደቅዋ ከፍ ብሎ መውለብለቡን ቀጥሏል! ጀግኖቻችንን እያመሰገንን እነሱ በደማቸው ያጸኗትን ሀገር ሌት ተቀን ሰርተን ድህነትን ተፋለመን በማሸነፍ የሀገራችንን ነጻትና ሉዓላዊነት እናጸናለን!

ውድ የከተማችን ነዋሪ በውጪ ጠላቶቻችን አዝማችነት ሀገር ለመበተን ጥቃት የፈጸሙብንን ህወሀትንና ጀሌዎቹን  በጀግንነት በመመከት  የሀገራችንን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ  ወደር የለሽ መስዋእትነት እየከፈለ ካለው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመሰለፍ አንደ ሁልጊዜው ከሰራዊታችን ጎን በመቆም ደጀንነቱን እንዲያረጋግጥ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ዕለቱን ሁሉም የመንግስት፣መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ነዋሪው ሕዝብ በተመሳሳይ ሁኔታ በሚከተለው መልኩ የሚዘከር ይሆናል።

ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ለ አንድ ደቂቃ ክላክስ ያሰማሉ።

ከጠዋቱ 4:30 በተመሳሳይ ሰዓት ሁሉም በከተማችን የሚገኙ  የመንግስት ና የግል ተቋማት አመራሮች ፣ ሰራተኞች እና መላው ነዋሪ በተሰማራበት እና ባለበት ቦታ  በመቆም የቀኝ እጁን በግራ ደረቱ ላይ በማድረግ ድምፁን ከፍ አድርጎ "ስለኢትዮጵያ የከፈላችሁትን አንረሳም" በማለት ለሰማዕታቱ ያለውን ክብር የሚገልፅ ይሆናል።

"ጥቅምት 24ን መቼም አንረሳውም"!!!
924 views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 18:16:15 ላሊበላ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል አገኘች!

ለረጅም ጊዜ ኤሌክትሪክ የተቋረጠባቸው ላሊበላ፣ ላስታ ወረዳ እና ሙጃ ከተማ ዛሬ የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ፡፡የኤሌክትሪክ ኃይሉን በድጋሚ ያገኙት በሽብር ቡድኑ ህወሓት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የአላማጣ - ላሊበላ የ66 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና መጠናቀቁን ተከትሎ ነው፡፡

የወልዲያ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ሽመልስ ወልደሰማያት የጥገና ሥራውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅና አካባቢዎቹን በድጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የዲስትሪክቱ ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል ብለዋል፡፡በሰቆጣና አካባቢዋ የሚገኙ ከተሞች የተቋረጠባቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል እዲያገኙ ይሠራልማለታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ አመላክቷል፡፡
1.0K views15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 18:27:44
1.1K views15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 18:26:34 የህወሓትና የፌደራል መንግስቱ የሰላም ንግግር እስከ ዕሮብ ተራዘመ!

በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያን ጦርነት በሰላም ይፈታል ተብሎ የታመነበት የሰላም ንግግር እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. መራዘሙ ተሰማ።

ቢቢሲ ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው በድርድሩ ስለተነሱ ሃሳቦች ምንም ፍንጭ ማግኘት አልተቻልም ያለ ሲሆን እሮብ ሲጠናቀቅ የጋራ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስነብቧል።

ከአንድ ሳምንት በፊት ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በፌደራል መንግስት እና ህወሓት መካከል የሰላም ንግግር መጀመሩ ይታወሳል።
1.1K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ