Get Mystery Box with random crypto!

ላሊበላ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል አገኘች! ለረጅም ጊዜ ኤሌክትሪክ የተቋረጠባቸው ላሊበላ፣ ላስታ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

ላሊበላ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል አገኘች!

ለረጅም ጊዜ ኤሌክትሪክ የተቋረጠባቸው ላሊበላ፣ ላስታ ወረዳ እና ሙጃ ከተማ ዛሬ የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ፡፡የኤሌክትሪክ ኃይሉን በድጋሚ ያገኙት በሽብር ቡድኑ ህወሓት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የአላማጣ - ላሊበላ የ66 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና መጠናቀቁን ተከትሎ ነው፡፡

የወልዲያ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ሽመልስ ወልደሰማያት የጥገና ሥራውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅና አካባቢዎቹን በድጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የዲስትሪክቱ ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል ብለዋል፡፡በሰቆጣና አካባቢዋ የሚገኙ ከተሞች የተቋረጠባቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል እዲያገኙ ይሠራልማለታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ አመላክቷል፡፡