Get Mystery Box with random crypto!

'ከታች ከቀረበው በመንግሥት እና በህወሓት በኩል ከተፈረመው የሠላም ስምምነት ውጪ የተሰራጩ መረጃዎ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

"ከታች ከቀረበው በመንግሥት እና በህወሓት በኩል ከተፈረመው የሠላም ስምምነት ውጪ የተሰራጩ መረጃዎች ያልተሟሉና ሊያሳስቱ የሚችሉ ናቸው" አምባሳደር ሬድዋን

ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በመንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረሰውን ትክክለኛ ስምምነት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አጋርተዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ስምምነቱ የተፈረመው ከበርካታ እልህ አስጨራሽ የቡድን ክርክሮች እና ንግግሮች በኋላ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም ከሁለቱ ተወያይ ወገኖች የቀረቡ በርካታ ረቂቆች የነበሩ ቢሆንም ስምምነት ላይ የተደረሰበት እና ተቀባይነት አግኝቶ የተፈራረምንበት ሠነድ ግን ከዚህ በታች የተቀመጠው ነው ሲሉም አስታውቀዋል።

አምባሳደር ሬድዋን እየተሰራጩ ያሉት መረጃዎች ቀደም ብለው የተዘጋጁ መረጃዎች ሊሆኑ እንደሚችሉም ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J