Get Mystery Box with random crypto!

ሁለት ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች ተብላ የተከሰሰችው የቤት ሰራተኛ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

ሁለት ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች ተብላ የተከሰሰችው የቤት ሰራተኛ ላይ ምስክር ተሰማ

ተከሳሽ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም  በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የህጻን ግዮናዊት መላኩ አፏን በማፈን  በቢላ በማረድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን እና ህጻን ክርስቲና መላኩን ደግሞ አፍፏን በማፈን በማነቅ  በአጠቃላይ ህፃናቶቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ  አድርጋለች ሲል በግድያ ወንጀል እና በወቅቱ የሟች ቤተሰቦችን የሰነድ ማስረጃዎች ቀዳዳ በመጣል በአጠቃላይ በተደራራቢ ክስ  ዓቃቢህግ በጥቅምት 15 ቀን ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

ተከሳሿ በጥቅምት 22 ቀን በነበረ ቀጠሮ የግድያ ወንጀሉን አልፈጸምኩም  ስትል የዕምነት  ክህደት ቃሏን መስጠቷን ተከትሎ  ወንጀል መፈጸሟን ያስረዱልኛል ያላቸውን 6 ምስክሮችን አቅርቦ ከሳሽ ዓቃቢህግ  ዛሬ አሰምቷል።አንድ ምስክር ተመሳሳይ ጭብጥ ያለው በመሆኑ እንዲታለው ተደርጓል።ችሎቱ የሟች ግዮናዊት እና ክርስቲና  መላኩ ወላጆችን ጨምሮ ስድስት ምስክሮች በእውነት ለመመስከር ቃለ መኃላ እንዲፈጽሙ አድርጓል።

በቀዳሚነት ዓቃቢህግ የሚሰሙለት ምስክሮቹን የምስክርነት ጭብጥ ለችሎቱ  አስመዝግቧል።በዚህም ባስመዘገበው የምስክር ጭብጥ መሰረት  የቤት ሰራተኛዋ መቼ እንደተቀጠረችና  ወላጆቻቸው ከቤት ሲወጡ የልጆቹ የነበሩበት የጤና ሁኔታ ÷ ተከሳሿ ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ እንዴት እጇን እደሰጠች እና ለሟች ህጻናቶች አባት መላኩ ታረቀኝ እንዴት ስልክ እንደደወለችና  በስልክ የተናገረኘ መልክት በሚመለከት እንዲሁም ፖሊስ ጣቢያ ከደረሰች በኋላ የሰጠችውን የዕምነት ቃል የሚመለከትና በቤት ውስጥ ተቀዳዶ ስለተገኘ የሰነድ ማስረጃን የሚመለከት ÷በቤት ሰራተኝነት ህጻናትን በመንከባከብ በምትሰራበት ቤት ውስጥ ሁለቱን የህጻናቶቹ ላይ እንዴት  ግድያን ወንጀል ፈጸመች በሚለው ነጥብ ÷ ወንጀሉ በተፈጸሙበት ወቅት ደግሞ የሟች ወላጆችን ማስረጃ   ተቀዳዶ  እንዲጠፋ የተደረገበትን ነጥብ አስመልክቶ ምስክሮቹ ምስክርነታቸው እንደሚሰማለት ጭብጥ አስመዝግቧል።

ጭብጥ ከተመዘገበ በኋላ በቀዳሚነት የሟች ህጻናቶች ወላጅ አባት መላኩ ታረቀኝ ልጆቹ እንዴት ተገለው እንደተገኙ እንደተመለከተ እና ትልቋ ህጻን ጊዮናዊች መስማት እና መናገር የማትችል እንደነበረች እና በወቅቱ የትምህርት ማስረጃው እንዴት ተቀዳዶ እንደተገኘ ገልጾ ምስክርነቱ አሰምቷል።በዚህ ምስክርነቱ ወቅት ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት እያለቀሰ ምስክርነቱን የሰጠ ሲሆን የችሎት ታዳሚውም በተመሳሳይ በለቅሶ ምስክርነቱን ሲሰሙ  ተስተውሏል።

የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ የሟች ህጻናቶች ወላጅ  አባት ተረጋግቶ ቃሉን መስጠት እንዲችል አረጋግተውታል።በማስከተል የሟች ህጻናቶች ወላጅ እናት መሰረት የሻነውም አጠቃላይ የህጻናቶቹን ሞት አስመልክቶ እንዲሁም በቤት ውስጥ ተቀዶ ስለተገኘ የስራ ልምድና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን በሚመለከት ምስክርነቷን ሰታለች።

እንዲሁም በፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ፈጽሜ ነው የመጣሁ በማለት ዕጇን መስጠቷን በሚመለከት በዕለቱ ፖሊስ ጣቢያ ተረኛ የነበሩ  አባላት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።ሌሎች ምስክሮችም የተመለከቱትን የህጻናት አሟሟትን በሚመለከት የምስክርነት ቃላቸውን አሰምተዋል።በተከሳሽ ተከላካይ ጠበቃ በኩል ለምስክሮቹ የመስቀለኛ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን በፍርድ ቤቱ የተለያዩ የማጣሪያ ጥያቄ ቀርቦ በምስክሮች እንደአግባቡ መልስ ተሰቷል።