Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለስሙም ሆነ ለክብሩ የማይመጥን እና ከእውነት የራቀ ለፖለቲካ ፍጆታ የሚውል | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለስሙም ሆነ ለክብሩ የማይመጥን እና ከእውነት የራቀ ለፖለቲካ ፍጆታ የሚውል ረብ-የለሽ መግለጫ ማውጣቱ በርካቶችን አስቆጥቷል

ንሥር ብሮድካስት
ህዳር 3/2015

አገልግሎት መስጠት ላይ የተሰማራ ማንኛውም ለትርፍ የተቋቋመ የንግድ ድርጅት በሚሰራበት አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰብን ስነ ልቦና እና እሴት ማክበር ግዴታው ነው።

በዋናነት ለንግድና ለማኀበረሰብ አገልግሎት የተቋቋመ በይበልጥ ደግሞ መንግሥታዊ የሆነ  ተቋም የሚሰራበትን አካባቢ ማህበረሰብ የወል ፍላጎቶች ማክበር፣ እሴትና ባህሉን መጠበቅ ትንሹ ተቋማዊ ኃላፊነት ነው።

ይህን አለማድረግ የንግድ ተቋሙ በአካባቢው ህዝብ ዘንድ በጥርጣሬ እንዲታይ ብሎም ከገበያ ውድድር መውጣትን ያስከትላል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአገሪቱ የፋይናንስ ተቋም ትልቁ ተቋም መሆኑ ይታወቃል።

ይህ አንጋፋ ባንክ ለስሙ ክብር የማይመጥን እና ከእውነት የራቀ ለፖለቲካ ፍጆታ የሚውል ረብ-የለሽ መግለጫ በዛሬው ዕለት አውጥቷል።

ባንኩ በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ላለፉት ሁለት ዓመት ከአከባቢው አስተዳደርና ህዝብ ተቀራርቦ ያለምንም የፀጥታ እንከን ሲሰጥ የነበረውን አገልገሎት በጎንደር ዲስትሪክት በኩል ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል።

ዛሬ፣ ባንኩ አሰራሩን ህቡዕ በሆነ አካሄድ በመቀየር ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት በ"ሽሬ ዲስትሪክት" በኩል በማድረግ እንደሚሰራ አስታውቋል።

በዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኛ ተኮር ( customer based) የንግድ አሰራርን ሳይሆን ፖለቲካዊ አቋምና ፍላጎት የሚያራምድ ከዝንባሌም ከፍ ያለ ሚና ለማሳየት ቃጥቷል። ይህ ኢትዮጵያችን ከምትኮራበት ግዙፍ የንግድ ተቋም የማይጠበቅ፣ ለተቋሙ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቱ ለሚኮራው ሕዝባችን ጭምር አሳፋሪ ክስተት ነው። ተቋሙ በዚህ ሁነቱ፣ ለወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብም ያለውን ንቀትም በጉልህ ገልጿል።

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ለዘመናት በዘረኛ የትግሬ ልሂቃን የደረሰበትን ዘግናኝ ግፍ የሚያስታውሰው አይፈልግም ብቻ ሳይሆን አምርሮ ይጠላል፤ ይታገላል። ከባርነት ወደ ነፃነት የተሸጋገረበትን ታሪካዊ ምዕራፍ ሊያደናቅፈበት የሚፈልግን የትኛውም ኃይል አይታገስም።

ለነፃነቱ ቀናኢ እና ሟች የሆነው የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ የባንኩን መግለጫ በፅኑ ያወግዛል።

ባንኩ የትልቋ ኢትዮጵያን መጠሪያ የያዘ እንደመሆኑ መጠን፣ ስሙን የሚመጥን ግብር (መገለጫ) ሊኖረው ይገባል ብለን እናምናለን። በእስካሁኑ ቆይታውም ከዘር፣ ኃይማኖትና ሌሎች ቡድናዊ ወገንተኝነቶች በራቀ መንገድ ኢትዮጵያዊ ቀለምና ገፅታ ተላብሶ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበረ እንረዳለን።

ከዚህ መልካም ገፅታውና ከፍታው ሊያወርደው በሚችል መልኩ በዛሬው ዕለት ያወጣውን መግለጫ እንደሚያስተካክለው እምነት አለን። ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ባንኩ እንደተቋም ፀረ-ወልቃይት ጠገዴ አማራቱን በግላጭ እንዳሳየ ይቆጠራል። እንደአስፈላጊነቱም መላው የአማራ ህዝብ እና ፍትህ ወዳድ የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች በባንኩ ያልተገባ ሁነት ላይ ቁጣቸውን እንዲያሰሙ ንቅናቄ ወደ መፍጠር ለመሻገር እንደምንገደድ እናስታውቃለን።

ወልቃይት ጠገዴ አማራ ነው !
ስንኖር በምክንያት ስንሞትም ለምክንያት!!
***
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን

ሕዳር 03/2015 ዓ.ም
ሁመራ-ኢትዮጵያ

=====================