Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህወሓት ግጭት ለማቆም መስማማታቸውን ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አስታወቁ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህወሓት ግጭት ለማቆም መስማማታቸውን ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አስታወቁ

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ግጭት ለማቆም መስማማታቸውን የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ተናገሩ። ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ወደ ስምምነት ማምራቱን ኦባሳንጆ የገለጹት፤ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አመቻችነት ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ለሁለት ዓመታት ገደማ ውጊያ ውስጥ የቆዩት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና የህወሓት ተደራዳሪዎች በይፋ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የተገናኙበት ነው። በሰላም ንግግሩ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የቀድሞዋ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ፑምዚ ለምላምቦ “በደጋፊነት” ተካፍለውበታል።

ከአንድ ሳምንት በላይ የተካሔደው የሰላም ንግግር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ)፣ የአሜሪካ መንግስት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ተወካዮች “በታዛቢነት ተሳትፈውበታል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)