Get Mystery Box with random crypto!

💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomerejaa
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

24 Hour News

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-10-31 18:23:33 የፋኖወች ግድያ መበራከት ለምን???

ሻምበል መማር ጌትነት; ፋኖ ቅዱስ; ፍኖ ባበይ; ፋኖ መሀመድ; ወጣት ደሳለኝ አያል
:- በአማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
*****

ሻምበል መማር ጌትነት በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ልዩ ስሙ ወርቅ ዋሻ በተባለ አካባቢ በግፍ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ አስከሬኑ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ታውቋል። በሰኔ 15/2011ዱ የባለስልጣናት ግድያ እድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት ሻምበል መማር ጌትነት
ጥቅምት 18/2015 ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ በአሰቃቂ መልኩ በጥይት እና በስለት ጭምር ግድያ የተፈጸመበት ይህ ወንድም አስከሬኑ በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ወርቅ ዋሻ በተባለ አካባቢ አስፓልት ላይ ተጥሎ መገኘቱን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።
መቄት ወረዳ በወቅቱ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ባለማግኘቱ በትክክል ያልታወቀ ይበለው እንጅ አስከሬኑ የሻምበል መማር ጌትነት መሆኑ ታውቋል።
አሁን ላይ አስከሬኑም ከወርቅ ዋሻ ወደ ወደ ሸድሆ መቄት ሆስፒታል ተወስዶ የሚረከብ ቤተሰብ እየተጠበቀ መሆኑን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ካነጋገረው የመቄት ፖሊስ ለማወቅ ችሏል።
በሰኔ 15/2011ዱ የባለስልጣናት ግድያ ከተከሰሱት እና በሌሉበት በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እድሜ ልክ ከተፈረደባቸው መካከል አንዱ የሆነው ሻምበል መማር ጌትነት በግፍ ተገድሎ አስከሬኑ ወድቆ የተገኘው በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ወርቅ ዋሻ፣ ከደቡብ ጎንደር ዞን ጨጨሆ መድሃኒያለም አዋሳኝ አካባቢ መሆኑ በፖሊስ ተመላክቷል።
"ሻምበል መማር ጌትነት በታህሳስ 13/2012 በድሬድዋ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል" በሚል በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ተዘግቦ እንደነበር በማስታዎስ ግድያው ከእስር ቤት በማስወጣት ተፈጽሞ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ሲያጋሩ ለማስተዋል ተችሏል።
በመቄት ወረዳ የፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጌታቸው አለሜ እንደገለጹት በወረዳው ደብረዘቢጥ ቀበሌ፣ በላይ ጋይንት ወረዳና መቄት ወረዳ አዋሳኝ ልዩ ስሙ ወርቅ ዋሻ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ መንስኤውና ገዳዩ ባልታወቀ ሁኔታ ጥቅምት 18/2015 ዓ.ም በህዝብ ጥቆማ ከአስፓልት መንገድ ዳር ከውሃ ተፍሰስ ቱቦ ላይ ከረፋዱ አራት ስዓት ላይ አስከሬኑ ወድቆ መገኘቱን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አጋርተዋል።
ወረዳው ለበለጠ መረጃም በስልክ ቁጥር ፦
09 14 06 48 32፣ 09 87 77 84 59 እና
0921 52 39 37 በመደወል መረጃ ለማግኘት እንደሚቻል አስታውቋል።
በተያያዘ ነዋሪነቱ በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ መና መቀጥዋ የሆነው የሻለቃ አስቻለው ደሴ ጀግና የትግል አጋር እንደነበር የተነገረለት ፋኖ ቅዱስ ደሴ ጥቅምት 12/2015 መንገድ ላይ ጠብቀው በመቆዬት ተኩስ በከፈቱበት የጉና በጌምድር ፖሊሶች አምጃዬ በተባለ ቦታ መገደሉን እና በተኩስ ልውውጡም ከፖሊሶች የተገደለ እና የቆሰሉ ስለመኖራቸው አሚማ ከአካባቢው ነዋሪዎች አረጋግጧል።
ፋኖ ቅዱስ ባለፈው ዓመት በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ከተማ ላይ በተፈጠረ እለታዊ የግል ግጭት ምክንያት ባበይ በተባለ ፋኖ ላይ ግድያ መፈጸሙን እና እርቅ ሰላም ሳይፈጸም መቆየቱን ምንጮች ተናግረዋል።
በተያያዘ በፋኖ ቅዱስ ደሴ መገደል በእጅጉ ያዘኑ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ወዳጆቹ ጥቅምት 20/2015 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በሻማ ማብራት ስነ ስርዓት በማስታወስ ነፍስ ይማር ብለዋል።
ከወራት በፊት በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ከደቡብ ወሎ ፋኖ መሀመድ የተባለ አባሉ ሀርቡ ላይ ከታሰረ በኋላ በፖሊስ በተፈጸመበት ከፍተኛ ድብደባ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
በተመሳሳይ በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ እንዲሁ ደሳለኝ አያል የተባለ ወጣት ጥቅምት 8/2015 በእስር ላይ እያለ በፖሊስ በተፈጸመበት ድብደባ ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል። ዘገባው የአሚማ ነው::
=====================
1.1K views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 18:32:11 መግለጫ!!

"የትግራይ ሕዝብ ሕወሐት ከጫነበት ቀንበር ነጻ እንዲሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መሥዋዕትነት እየከፈለ ነው

የመከላከያ ሰራዊቱ መሥዋዕትነት የታሰበውን ግብ እንዲያሳካ የትግራይ ሕዝብ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የመከላከያ ሠራዊቱን በመንከባከብ፣ ስንቅ በማቀበል፣ ስለተደበቁ ጀሌዎችና የጦር መሣሪያዎች መረጃ በመስጠት፣ መንገድ በመምራት እና አካባቢውን በመጠበቅ የትግራይ ሕዝብ ከሠራዊቱ ጋር ተሰልፏል። ለዚህም መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባል።

የትግራይ ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ያለው ቅንጅት ሕወሐትን አስደንግጦታል። በዚህም የተነሣ "ምስለኔዎች ሊያስተዳድሩህ እየመጡ ነው" የሚል ውዥንብር እየነዛ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሕወሓት ጋር የታገለው የምስለኔ አስተዳደር እንዲቀር ነው። የምስለኔ አስተዳደርን በክልሎች ላይ እንደገና የዘረጋው ሕወሐት በመሆኑ።

የትግራይ ሕዝብ በራሱ ልጆች እንጂ በማንም ሊተዳደር አይገባም።

ፌዴራላዊ ሥርዓቱም ይሄንን አይፈቅድም። ሕወሐትም ይሄንን ያውቃል። ይደብቃል እንጂ። በመሆኑም የትግራይ ሕዝብ የሕወሐትን የምስለኔ ቴአትር፣ በምስለኔነት ለኖረው ለሕወሐት ትቶ፣ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር የጀመረውን ትብብር እንዲያጠናክር መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል።"

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
2.0K views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 23:04:20 አላማጣ መሀል ከተማ ላይ ከህወሓት የሽብር ቡድኑ በተተኮሰ መድፍ በርካቶች መሞታቸውን አረጋግጠናል ።
4.8K views20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 22:58:15 “ማረጋገጫ ከተሰጠን ጦርነቱን አቁመን ሀገር ለቀን ለመውጣት ዝግጁ ነው” የህወሃት አመራሮች

ጦርነቱ ወደ መገባደዱ መድረሱን ተከትሎ የህወሃት ቁንጮዎች አነጋጋሪ ውሳኔ ላይ እንደ ደረሱ ከውስጥ አዋቂ የሚመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከቀን ወደ ቀን፣ ከሰዓት ወደ ሰዓት የከበባው ቀለበት በሁሉም አቅጣጫ እየጠበበ መምጣቱን የተረዱት የህወሃት ሰዎች አለም አቀፉ ማህበረሰብና የአፍሪካ ህብረት መውጫ ካመቻቸልን ጦርነቱን ወዲያው አቁመን ከሀገር ለመውጣት ተዘጋጅተናል የሚል አቋም ላይ እንደደረሱና ይሄንንም አቋማቸውን በቴድሮስ አድሃኖም አማካኝነት ለአሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ተደራሽ እንዳደረጉ ታውቋል። ዛሬ የአፍሪካ ህብረት ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ የህወሃት ሚዲያዎች በሙሉ ተኩስ አቁሙን እንደተቀበሉ ተደርጎ እንዲሰራጭ ከማዕከል ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ዛሬ ቴድሮስ አድሃኖም በርሊን ላይ ይህንኑ የህወሃት አመራሮችን ማስመለጫ መንገድ በተመለከተ ከተለያዩ ሰዎች ጋር እንደተነጋገረና በቀጣይ ቀናትም ወደ ብራሰልስ እንደሚጓዝ ይጠበቃል። ዛሬ በርሊን ላይ ካነጋገራቸው አካላት መካከል የአሜሪካ ሰዎችም እንደሚገኙበት ነው ጀርመን ካሉ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች የተረዳነው።

ጦርነቱ መቀልበስ የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ጠላትም ወዳጅም ተረድቷል። አሁን መፍትሄው፣ ውሳኔውም ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያ እጅ ነው። መከላከያ ሰራዊት ግዳጁን በሚገርም ኦፕሬሽን አፈፃፀም እየተወጣ ነው። ህወሃት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መወገዱ የማይቀር ብቻ ሳይሆን በጣም በፍጥነት የሚሆን ነገር መሆኑ ተረጋግጧል። ከአሁን በኋላ ከህወሃት በኋላ የሚኖረው የትግራይ ክልል አስተዳደርና የሰሜኑን የሀገራችን ክፍልን መልሶ ማቋቋም ላይ ትኩረት መደረግ አለበት!

    ( ሱሌማን አብዴላ )
4.5K views19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 22:53:39

4.5K views19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 21:59:45 ማይጠምሪ በጥምር ጦሩ ጠንካራ ክንድ ነፃ ወጥታለች። በማይጠምሪ ግንባር በኩል ወልቃይትን እይዛለሁ እያለ እየጨፈረ የከረመው የትህነግ ታጣቂ ሙትና ቁስል ሆኖ ቀሪው በዲማ በኩል ወደ ትግራይ ፈርጥጧል።

አማራን አሳድደህ በለው እያለ ሲዘፍን የከረመ የትህነግ ታጣቂ በአማራ ልዩ ኃይል ክፉኛ ተመትቶ እውነታውን አይቷል። ማን እያሳደደ እንደሚያቀምስ የተማረ ይመስላል። የጥምር ጦሩን የዘንድሮ ጀብዱ ጠላት ራሱ ቢመሰክረው ይሻላል።
4.3K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 16:54:33

2.0K views13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 21:28:41 ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር-ቤት የተላለፈ ማሻሻያ መልዕክት

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ የፀጥታ ስጋትን አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔ አስተላልፏል።

1ኛ. በከተማ አስተዳደሩ በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚኖር ተፈናቃይ ጠዋት ከ11ሰአት በፊት መውጣት ማታ ከ1:00 ሰዓት በኋላ ወደ መጠለያ ጣቢያውም ሆነ ወደ ከተማው መግባት ክልክል ነው።
2ኛ. በከተማው የሚገኙ ሁሉም አይነት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ እንዲሁም ከለሊቱ 11 ሰአት በፊት እንቅስቃሴ ሲያደርግ የተገኘ ማንኛውም ተሽከርካሪ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል።

3ኛ. በከተማው የሚገኙ መጠጥ ቤቶች ምግብ ቤቶች ምሽት ጭፈራ ቤት እስከ ምሸት 4:00 ሰአት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ወስኗል።

4ኛ. በከተማው በሚገኙ የንግድ ቤቶች የምርት የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

5ኛ. ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ሀይሎች ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው ይዞ የተገኘ ይወረሳል።
6ኛ. ከመንግስት ዕውቅና ውጭ የሚደረጉ ማናቸውም አይነት ውይይቶችና ስብሰባ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

7ኛ. የጠላትን ሀሳብና እንቅስቃሴ በመደገፍ አሉባልታና ወሬን ማሰራጨት በህብረተሰቡ ላይ ሽብር መንዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
8ኛ. አዳር የሚሰሩ በከተማችን ያሉ ፍብሪካዎችና ድርጂቶች ድርጁቱ በሚሰጣቸው ህጋዊ መረጃ ና በፀጥታ መዋቅሩ የተረጋገጠ የይለፍ ከያዘ ብቻ መንቀሳቀስ ይችላል፡፡
9ኛ. መላው የከተማው ማህበረሰብ በአደረጃጀት አካባቢውን ቀንና ሌሊት ከሰርጎ ገቦች በንቃት መጠበቅ አለበት።
10ኛ. በከተማ አስተዳደሩ ፀጉረ ልውጥ ሲያጋጥም በፍጥንት ለህግ አካል ጥቆማ በመስጠት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረግ ከማህበረሰቡ ይጠበቃል።
11ኛ. የከተማው ባለሆቴሎች እና አልጋ አከራዮች ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ግለሰብ በድርጅታችሁ ሲያጋጥማችሁ ለህግ አካላት ጥቆማ እንድትሰጡ።

12ኛ. በከተማ አስተዳደሩ ያላችሁ የቤት አከራይዎች የምታከራዩትን ግለሰብ ማንነትት መታወቂያ በመጠየቅ ለይታችሁ እንድታከራዩ የተከራዩንም መረጃ በፎርም በመሙላት ለከተማው ሰላምና ፀጥታ መምሪያ እንድታሳውቁ መልዕክት አስተላልፏል።
13ኛ. ማንኛውም ሰው የመከላከያ የልዩ ሀይል ወዘተ የደንብ ልብስ ለብሶ መገኘት በህግ ያስቀጣል ።
ይህ የውሳኔ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ከላይ በዝርዝር የተቀመጡትን የውሳኔ ሀሳቦች የሚጥስ ማንኛውም አካል ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድበትም የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር
መስከረም 3/1/2015 ዓ.ም

@Esat_tv1
@Esat_tv1
4.6K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 01:44:41
3.2K views22:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 01:44:35 #ክርስቲያን #የሆነ ሁሉ #ሼር #ያድርገው


ባህርዳር አወርስ ካፌ የሆነው እጅግ በጣም አሳዛኝ ነገሬ ነው።ከኦርቶዶክሳውያን ገንዘብ እየለቀሙ፣ በኦርቶዶክሳውያን ሠራተኞች ላይ እንዲህ ያለ ግፍና ነውር መፈጸም ምን ማለት ነው? ለዚህ ካፌ ከ90 ፐርሰንት በላይ ተጠቃሚው
ኦሮቶዶክሳዊያን ነው። ትርፉም የሚገኘው ከእነዚህ ነው። ነገርግን አማኞችን እየተጸየፉ ገንዘባቸውን ብቻ መፈለግና ከዚህም ብሶ ታማ ለወደቀች ሴት ከቤቱ ለምን ፀሎት አደረጋችሁ ብሎ የፀሎት መጽሐፍ ቀዳዶ ቅርጫት ውስጥ መጣል ትልቅ ድፍረትና ነውር ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው ባህርዳር ከተማ OURS የሚባል ካፌ አለ። የዚህ ካፌ ባለቤት ፕሮቴስታንት ነው። ሰውየው የሃይማኖት ሰላይና ከሌሎች ጋርም እጅና ጓንት ሆኖ ይሰራል ነው የሚባለው። ካፌው 4 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ ድርጊቱ የተከሰበት ካፌ ፓፒረስ ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኘው ፒያሳ ህንጻ ወይንም የሺ ቡና ጎን ይገኛል። ከዚህ ካፌ የምትሰራ አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ሴት ብዙ ግዜ ሰለሚያማት የፀሎት መጽሐፍ ትይዛለች። ትናንት ልጂቷ በሥራ ላይ እንዳለች አዙሮ ይጥላታል። በዚህን ጊዜ ጓደኞቿ የፀሎት መጽሐፉን እየደገሙ ውሐ ሲረጯት ልጂቷ መንቃት ትጀምራለች። ይህን የሰማው የካፌው ሥራ አስኪያጅ ይመጣና የፀሎት መጽሐፉን ከልጆች ቀምቶ፣ ከሁለት ቀዶ እዛው ካፌ ውስጥ ቆሻሻ ሶፍትና ሌላም ከሚጣልበት ቅርጫት ላይ ይጥለዋል። በተጨማሪም የቅድስት እመቤታችን ድንግል ማርያምን ስዕለ አድኅኖ ቀዶታል። ሥራአስኪያጁ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ እንደሆነ ታውቋል።


በወቅቱ ከካፌው የነበሩ ወጣቶች ስሜታቸውን ውጠው ቢያንስ ይቅርታ እንዲጠይቅ ሲጠይቁት በትዕቢት ተነፍቶ እምቢ ይላል። የከተማው ወጣት ይህን በዝምታ ማለፍ አልፈልግም ዛሬ የህግ አካል ይዘው ልጁን በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርገውታል። በአሁኑ ሰዓት ጊዮርጊስ አካባቢ ካለው አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል። የ'OURS ሁለቱም ካፌዎች ተዘግተዋል። አንደኛው ድርጊቱ የተፈጸመበት ፒያሳ ህንጻ ያለው፣ ሁለተኛው ጊዮርጊስ አካባቢ ከዊን ሆቴል ጎን ያለው።

ወጣቶች ስሜታቸውን ተቆጣጥረው ነገሩን ወደ ህግ መውሰዳቸው የሚያስመሰግናቸው ነው። ነገርግን ልጁ የፈፀመው ከባድ ወንጀል እና የሰዎችን እምነት መጋፋትና ማንቋሸሽ ብሎም ፀብ-አጫሪነት በመሆኑ በዝምታ መታለፍ የለበትም።  የዚህን ጉዳይ የመጨረሻ ሁሉም ሊከታተለው ይገባል። ሃይማኖትህን የምታስከብረው አንተው እራስህ ነህ። ባለቤቱን ካልናቁ አጥር አይነቀንቁ!
5.6K views22:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ