Get Mystery Box with random crypto!

ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር-ቤት የተላለፈ ማሻሻያ መልዕክት የደብረ ብርሃን ከ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር-ቤት የተላለፈ ማሻሻያ መልዕክት

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ የፀጥታ ስጋትን አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔ አስተላልፏል።

1ኛ. በከተማ አስተዳደሩ በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚኖር ተፈናቃይ ጠዋት ከ11ሰአት በፊት መውጣት ማታ ከ1:00 ሰዓት በኋላ ወደ መጠለያ ጣቢያውም ሆነ ወደ ከተማው መግባት ክልክል ነው።
2ኛ. በከተማው የሚገኙ ሁሉም አይነት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ እንዲሁም ከለሊቱ 11 ሰአት በፊት እንቅስቃሴ ሲያደርግ የተገኘ ማንኛውም ተሽከርካሪ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል።

3ኛ. በከተማው የሚገኙ መጠጥ ቤቶች ምግብ ቤቶች ምሽት ጭፈራ ቤት እስከ ምሸት 4:00 ሰአት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ወስኗል።

4ኛ. በከተማው በሚገኙ የንግድ ቤቶች የምርት የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

5ኛ. ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ሀይሎች ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው ይዞ የተገኘ ይወረሳል።
6ኛ. ከመንግስት ዕውቅና ውጭ የሚደረጉ ማናቸውም አይነት ውይይቶችና ስብሰባ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

7ኛ. የጠላትን ሀሳብና እንቅስቃሴ በመደገፍ አሉባልታና ወሬን ማሰራጨት በህብረተሰቡ ላይ ሽብር መንዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
8ኛ. አዳር የሚሰሩ በከተማችን ያሉ ፍብሪካዎችና ድርጂቶች ድርጁቱ በሚሰጣቸው ህጋዊ መረጃ ና በፀጥታ መዋቅሩ የተረጋገጠ የይለፍ ከያዘ ብቻ መንቀሳቀስ ይችላል፡፡
9ኛ. መላው የከተማው ማህበረሰብ በአደረጃጀት አካባቢውን ቀንና ሌሊት ከሰርጎ ገቦች በንቃት መጠበቅ አለበት።
10ኛ. በከተማ አስተዳደሩ ፀጉረ ልውጥ ሲያጋጥም በፍጥንት ለህግ አካል ጥቆማ በመስጠት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረግ ከማህበረሰቡ ይጠበቃል።
11ኛ. የከተማው ባለሆቴሎች እና አልጋ አከራዮች ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ግለሰብ በድርጅታችሁ ሲያጋጥማችሁ ለህግ አካላት ጥቆማ እንድትሰጡ።

12ኛ. በከተማ አስተዳደሩ ያላችሁ የቤት አከራይዎች የምታከራዩትን ግለሰብ ማንነትት መታወቂያ በመጠየቅ ለይታችሁ እንድታከራዩ የተከራዩንም መረጃ በፎርም በመሙላት ለከተማው ሰላምና ፀጥታ መምሪያ እንድታሳውቁ መልዕክት አስተላልፏል።
13ኛ. ማንኛውም ሰው የመከላከያ የልዩ ሀይል ወዘተ የደንብ ልብስ ለብሶ መገኘት በህግ ያስቀጣል ።
ይህ የውሳኔ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ከላይ በዝርዝር የተቀመጡትን የውሳኔ ሀሳቦች የሚጥስ ማንኛውም አካል ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድበትም የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር
መስከረም 3/1/2015 ዓ.ም

@Esat_tv1
@Esat_tv1