Get Mystery Box with random crypto!

#ክርስቲያን #የሆነ ሁሉ #ሼር #ያድርገው ባህርዳር አወርስ ካፌ የሆነው እጅግ በጣም አሳ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

#ክርስቲያን #የሆነ ሁሉ #ሼር #ያድርገው


ባህርዳር አወርስ ካፌ የሆነው እጅግ በጣም አሳዛኝ ነገሬ ነው።ከኦርቶዶክሳውያን ገንዘብ እየለቀሙ፣ በኦርቶዶክሳውያን ሠራተኞች ላይ እንዲህ ያለ ግፍና ነውር መፈጸም ምን ማለት ነው? ለዚህ ካፌ ከ90 ፐርሰንት በላይ ተጠቃሚው
ኦሮቶዶክሳዊያን ነው። ትርፉም የሚገኘው ከእነዚህ ነው። ነገርግን አማኞችን እየተጸየፉ ገንዘባቸውን ብቻ መፈለግና ከዚህም ብሶ ታማ ለወደቀች ሴት ከቤቱ ለምን ፀሎት አደረጋችሁ ብሎ የፀሎት መጽሐፍ ቀዳዶ ቅርጫት ውስጥ መጣል ትልቅ ድፍረትና ነውር ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው ባህርዳር ከተማ OURS የሚባል ካፌ አለ። የዚህ ካፌ ባለቤት ፕሮቴስታንት ነው። ሰውየው የሃይማኖት ሰላይና ከሌሎች ጋርም እጅና ጓንት ሆኖ ይሰራል ነው የሚባለው። ካፌው 4 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ ድርጊቱ የተከሰበት ካፌ ፓፒረስ ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኘው ፒያሳ ህንጻ ወይንም የሺ ቡና ጎን ይገኛል። ከዚህ ካፌ የምትሰራ አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ሴት ብዙ ግዜ ሰለሚያማት የፀሎት መጽሐፍ ትይዛለች። ትናንት ልጂቷ በሥራ ላይ እንዳለች አዙሮ ይጥላታል። በዚህን ጊዜ ጓደኞቿ የፀሎት መጽሐፉን እየደገሙ ውሐ ሲረጯት ልጂቷ መንቃት ትጀምራለች። ይህን የሰማው የካፌው ሥራ አስኪያጅ ይመጣና የፀሎት መጽሐፉን ከልጆች ቀምቶ፣ ከሁለት ቀዶ እዛው ካፌ ውስጥ ቆሻሻ ሶፍትና ሌላም ከሚጣልበት ቅርጫት ላይ ይጥለዋል። በተጨማሪም የቅድስት እመቤታችን ድንግል ማርያምን ስዕለ አድኅኖ ቀዶታል። ሥራአስኪያጁ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ እንደሆነ ታውቋል።


በወቅቱ ከካፌው የነበሩ ወጣቶች ስሜታቸውን ውጠው ቢያንስ ይቅርታ እንዲጠይቅ ሲጠይቁት በትዕቢት ተነፍቶ እምቢ ይላል። የከተማው ወጣት ይህን በዝምታ ማለፍ አልፈልግም ዛሬ የህግ አካል ይዘው ልጁን በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርገውታል። በአሁኑ ሰዓት ጊዮርጊስ አካባቢ ካለው አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል። የ'OURS ሁለቱም ካፌዎች ተዘግተዋል። አንደኛው ድርጊቱ የተፈጸመበት ፒያሳ ህንጻ ያለው፣ ሁለተኛው ጊዮርጊስ አካባቢ ከዊን ሆቴል ጎን ያለው።

ወጣቶች ስሜታቸውን ተቆጣጥረው ነገሩን ወደ ህግ መውሰዳቸው የሚያስመሰግናቸው ነው። ነገርግን ልጁ የፈፀመው ከባድ ወንጀል እና የሰዎችን እምነት መጋፋትና ማንቋሸሽ ብሎም ፀብ-አጫሪነት በመሆኑ በዝምታ መታለፍ የለበትም።  የዚህን ጉዳይ የመጨረሻ ሁሉም ሊከታተለው ይገባል። ሃይማኖትህን የምታስከብረው አንተው እራስህ ነህ። ባለቤቱን ካልናቁ አጥር አይነቀንቁ!