Get Mystery Box with random crypto!

💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomerejaa
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

24 Hour News

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-09 20:19:35
504 views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 20:19:31 ደራ
በደራ ወረዳ ከፍተኛ ስጋት መስፈኑ ተገረ!!

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሰው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በወረዳው ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን የአካባቢው ነዋሪዎች መግለፃቸውን አዲስ ማለዳ ዘግባለች፡፡

በወረዳው ውስጥ በምትገኘው ባቡ ድሬ ቀበሌ በርካታ የሆኑ የሸኔ ታጣቂዎች ከተለያየ ቦታ እየመጡ መሰባሰባቸውን የተናገሩት የአዲስ ማለዳ ምንጮች፣ ከዚህ ቀበሌ ባሻገር ሰው በማይኖርባቸው በረሃዎች  በርካታ ታጣቂዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

የሸኔ ታጣቂዎች አጎራባች ከሆኑ የሰሜን ሸዋ ወረዳዎች ወደ ደራ ወረዳ እየገቡ እንደሆነ የተናገሩት ምንጮች፣ የታጣቂዎቹ ብዛት ከዚህ በፊት ከታዩት የበለጠ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ይህም በነዋሪዎች ላይ ስጋት ፈጥሯል ያሉት ምንጮች፣ የሸኔ ታጣቂዎች ከዚህ በፊት በወረዳዋ ነዋሪዎች ላይ ከሚያደርሱት ጥቃት አንጻር ስጋቱ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለሸኔ ታጣቂዎች ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል እጃቸወን ለፖሊስ ከሰጡ ታጣቂዎች መካከልም የተሀድሶ ስልጠና ሳይሰጣቸው ከኅብረሰተቡ ጋር መቀላቀላቸውን የተናገሩት ምንጮች፣ በጉዳዩ ዙሪያ በመንግስት አካላት ጥንቃቄ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡ 

ከቀናት በፊት የወረዳው ነዋሪዎች በሸኔ ታጣቂዎች እየታፈኑ መሆኑን መዘገቧን ያስታወሰችው አዲስ ማለዳ የታፈኑት ሰዎች እስከ 300 ሺሕ ብር የሚደርስ የማስለቀቂያ ክፍያ እየተከፈለላቸው መለቀቃቸው ተሰምቷል ብላለች፡፡ (አዲስ ማለዳ)
592 views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 07:01:54
1.1K views04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 07:01:20 "አራት ፖሊሶች እጆቼን ይዘው በምላጭ ያንገቴን ማህተም በጠሱት"

በሕይወቴ ጥቁር ጠባሳ የጣለብኝ እስር !!

ከታሰርኩባቸው እስሮች ትንሹ የሚባለው ይሄኛው እስር ቢሆንም ከፍተኛ ግፍና ማስጠንቀቂያ ያዘለ እስር ነው ፤ ዝርዝሩን በሰፊው እመለስበታለሁ ። ከመጀመሪያ ጀምሮ ማህተቤን እንድበጥስ ግፊት ቢደረግብኝም ያንን ማደረግ እንደማልችል እና ለእኔ ሞት እንደሆነ ነግሬ አልበጥስም አልኩ !! ከአንድ ቀን ጭቅጭቅ በኋላ አራት ፖሊሶች ብቻዬን በማስጠራት ሳላስበው እጆቼን ከያዙ በኋላ
በምላጭ ያንገቴን ማህተብ በጠሱት እቅም የማጣት ስሜት ተሰማኝ ፤ እንዲደበድብኝ ተሳደብኩ እነሱ ከዱላ በላይ የሆነ ነገር እንዳደረሱብኝ ስለገባቸው ዝም አሉኝ ።

መብላት መጠጣት አቃተኝ በአይኤስ አይኤስ በሰው ሀገር ማህተባችንን አልበጥስም ብለው የተሰው ወንድሞቼ አይነት አቅም እንደሌለኝ ሲሰማኝ ልቤ ክፉኛ ተሰበረ ፤ኡፍፍ ይህ ክፉ ቀን መቼም አረሳወም !!

ይህ እንዲህ እንዳለ ፤ሁሌም ከግፉዓን ጎን የሚቆመው ወንድማችን ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ በዚህ ፈተና ወቅት ሙያዊ ግዴታው እንዳለ ሆኖ! እንደወትሮ አሁንም ፤ስለ ፍትህ ፤ስለ እውነት በማለት ከእኔ በደለኛ ጎን በመቆም ወንድሜ ቤተ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ ፤ አመሰግናለሁ ።

ሁሌም ቢሆን የግፉአን ዓይንና ጆሮ በመሆን የበደለኞችን ድምጽ የምታሰሙ ፤ጋዜጠኞች ፤አክቲቪስቶች ክብር ለእናንተ ይሁን !!

ብቻ ፈተውኛል ለሁላቹም እግዚአብሔር ይስጥልኝ !!
1.1K views04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 23:57:32 መንግሥት የሰዎች የመዘዋወር መብት ላይ የሚፈጸሙ ገደቦችን በአስቸኳይ እንዲያስቆም ኢሰመጉ ጠየቀ

ሐሙስ የካቲት 9 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) መንግሥት ከሕግ አግባብ ውጪ በሰዎች የመዘዋወር መብት ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ገደቦችን በአስቸኳይ እንዲያስቆም እና በዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እና በአገር አቀፍ ሕጎች ላይ የተጣሉበትን ኃላፊነቶች እንዲወጣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ጠየቀ።

ኢሰመጉ የሰዎችን የመዘዋወር፣ የአካል ነጻነትና መሰረታዊ ፍላጎቶችን የማግኘት መብት መንግሥት ያስከብር በሚል ርዕስ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ የመዘዋወር ነጻነትን አስመልክቶ በተደጋጋሚ ጊዜ መግለጫዎችን በማውጣት በእዚህ መብት ላይ የሚጣሉ ተገቢ ያልሆኑ ገደቦች እንዲቆሙ ሲወተውት መቆየቱን አስታውሷል።

በመግለጫው በኢትዮጵያ ተገቢ ያልሆኑ ገደቦች ከሚጣልባቸው መብቶች አንዱ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብት መሆኑን በማስታወስ፤ ምንም እንኳን ይህ መብት በዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እንዲሁም አገር አቀፍ ህጎች ላይ እውቅና ያለው ነገር ግን ፍጹም ያልሆነ የመብት አይነት ቢሆንም፤ በተለያዩ ምክንያቶች ተገቢ ያልሆኑ ገደቦች እየተጣሉበት እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ኢሰመጉ የካቲት 3/2015 ባወጣው መግለጫ ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ ሰዎች ከመንገድ እየተመለሱ መሆኑን እና በእዚህም ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው መንገደኞች እየተንገላቱ መሆኑን በመግለጽ ይህ ድርጊት እንዲታረም ጥሪዎችን ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ምንም አይነት የእርምት እርምጃዎች ሳይወሰዱ ይልቁንም ጉዳዩ ዳራውን በማስፋት ከደብረብርሀን፣ ከባህርዳር፣ ከደብረዘይትና ሌሎችም አካባቢዎች ጭምር ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ መንገደኞች ያለምንም በቂ ምክንያት እየተመለሱ መሆኑን እና በእዚህም ምክንያት ለተለያዩ ጉዳዮች ሕክምናንም ጨምሮ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተጓጎሉ መሆኑን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን ገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት፤ በሰዎች የመዘዋወር መብት ላይ የሚደረገው ገደብ ምንም አይነት ሕጋዊ መሰረት የሌለው፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ እንዲሁም አስፈላጊነቱ ጥያቄ ውስጥ የሚወድቅ በመሆኑ ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙ በተለየዩ ኬላዎች ላይ የሚገኙ የመንግስት የጸጥታ አካላት ከእዚህ ሕገ-ወጥ ድርጊት እንዲቆጠቡ፣ ይህንንም ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን መንግስት በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርግ አሳስቧል።

በተጨማሪ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ በሚገኙ አንዳንድ ክፍሎች ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች እየታሰሩ ይገኛሉ፡፡“ ያለው ኢሰመጉ፤ በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ በብዛት የሚፈጸሙ ተገቢውን የሕግ ሥነ ስርዓት ያልተከተሉ እስሮች እየተፈጸሙ እንደሚገኙ ገልጿል፡፡ ይህ ድርጊት አሁንም ምንም አይነት ዘላቂ መፍትሄ ባለማግኘቱ ድርጊቱ እየተበራከተ እንደሚገኝ ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን አስታውቋል፡፡

የፌደራል እንዲሁም የሚመለከታቸው የክልል መንግስታት ከሕግ አግባብ ውጪ በብዛት የሚፈጸሙ ሕገወጥ እስሮችን በአስቸኳይ እንዲያስቆሙም ኢሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

በሌላ በኩል፤ ትናንት የካቲት 8/2015 በወልቂጤ ከተማ ከመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ጋር በተያያዘ የከተማው ነዋሪዎች “ችግሩ እንዲፈታልን” በማለት ቅሬታቸውን ለመግለጽ ጀሪካን ይዘው አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች ላይ፤ የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል በወሰደው እርምጃ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን እና መቁሰላቸውን ኢሰመጉ ገልጿል፡፡

የደቡብ ክልል መንግስት በወልቂጤ ከተማ የተከሰተውን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር በአስቸኳይ በመፍታት ማሕበረሰቡ ንጹህ የመጠጥ ውሃ የማግኘት መብቱን እንዲያከብር፤ እንዲሁም ይህ እንዲሟላላቸው በጠየቁ ዜጎች ላይ የሞት እና ሌሎች አደጋዎችን ያደረሱ የፀጥታ አካላት በሕግ ፊት ተጠያቂ እንዲደረጉ ኢሰመጉ በመግለጫው አሳስቧል፡፡
140 views20:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 22:43:17 እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀናት እጾማለሁ ያለው ፓስተር ህይወቱ አለፈ

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
በሞዛምቢክ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀናት እጾማለሁ ያለው ፓስተር ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል።

ፍራንሲስኮ ባራጃህ የተባለው ፓስተር ከባዱን ነገር ተጋፍጦ ምዕመኑን ለማስደመም ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት በዛሬው እለት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል።

ማኒካ በተባለችው ግዛት ነዋሪ የሆነው ፍራንሲስኮ፥ ለ25 ቀናት ከጾመ በኋላ ከሰውነት ተራ ወጥቶ ህይወቱ ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

ፓስተሩ ቀናት እየገፉ ሲሄዱ መራመድም ሆነ መቆም ተስኖት እንደነበር የተናገሩት ቤተሰቦቹ፥ ቤይራ በተሰኘችው ከተማ ወደሚገኝ ሆስፒታል ወስደውት ህክምና ሲደረግለት ቆይቷል።

የህክምና ክትትሉ ግን የፍራንሲስኮ ባራጃህ “በድንቅ መዝገብ ስሙን የማስፈር ሙከራ” ሊያሳካው አልቻለም።

ቤተሰቦቹም ሆነ የሚያገለግለው ቤተእምነት ምዕመናን እንደማይተርፍ የገባቸው አስቀድሞ መሆኑን የጠቀሰው የቢቢሲ ዘገባ፥ በህልፈቱ ብዙም አለመደናገጣቸውን አመላክቷል።

በደቡብ አፍሪካም ተመሳሳይ ሙከራ የ44 አመቱን ፓስተር ህይወት መቀማቱ የሚታወስ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
356 views19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 06:52:44 እምነቶች ለእኛ አማኞች የመጨረሻ ምሽጎቻችን ናቸው። ብርታት ጽናት ተስፋ ... ይሰጣሉ፡፡ ለጠፋው ሕይወት ሃዘኔን ገልጫለሁ።

ከዚህ በፊት እንዳልኩት ዘርና ሃይማኖትን ለፓለቲካ ጥቅም ማዋል ... ቀይ መስመርን መተላለፍ ነው። የሰው ልጅ በሕይወቱ፣ በሥራው፣ በማህበራዊ ኑሮው ድንበር ከሌለው እራሱ የእደጋ ምን ነው።

የት ይደርሳሉ ብለን ችላ ያልናቸው ሁኔታዎች ናቸው ማጣፍያውን የሚያሳጥሩት፡፡

የሃይማኖት ጉዳይ የቤተ እምነቶቹ አባቶችና ምዕመናን ጉዳይ ነው።

ኢትዮጵያ ባሏት ዘመናትን ያስቆጠሩ በህሎቿ ሃይማኖቶቿ ታሪኳ ... እንኮራለን። እንጠብቃቸው፣ ከጥቃት እንከላከላቸው።

ጥንቃቄ፣ ብልሃት፣ ጥበብ፣ የሰከነ አእምሮ፣ እርጋታ፣ አርቆ አስተዋይነት ... የችግሮች መፍቻ ዘዴዎች ናቸው፡፡

የተደረጉትም ሆነ መደረግ ሲገባቸው ያልተደረጉት ሲታዩ የአገር ጽኑ መሠረት የሆኑትና ለድርድር የማይቀርቡ የዜጎች መሠረታዊ መብቶች፣ የሕግ የበላይነት፣ ለሕግ ተገዢነት፣ ተጠያቂነት፣ የሃሳብ ነጻነት፣ መረጃ የማግኘት መብት... የመሳሰሉት ለአደጋ እንዳይጋለጡ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

ከነበርንበት መከራ ወጥተን ሳናበቃ፣ በአገር በሕዝብ ላይ የደረሱ በርካታ ስብራቶችን ሳንጠግን፣ ሕይወት የሚቀጥፉ ግጭቶችን ሳናስወግድ፣ በርካታ ዜጎቻችን በተፈናቀሉበት፣ በሚሊዮኖች የሰብዓዊ ዕርዳታ በሚሹበት ተመካክረን ተግባብተን ከመሥራት ሌላ አማራጭ አይታየኝም።

አገሪቱ የሁላችንም ነች። ሁላችንንም ያገባናል። ፈጣሪ ይጠብቀን።

የ.ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ
723 views03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 13:27:04
706 views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 13:27:03 የሲኖዶሳችን መግለጫ
702 views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 18:43:03
1.1K views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ