Get Mystery Box with random crypto!

እምነቶች ለእኛ አማኞች የመጨረሻ ምሽጎቻችን ናቸው። ብርታት ጽናት ተስፋ ... ይሰጣሉ፡፡ ለጠፋው | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

እምነቶች ለእኛ አማኞች የመጨረሻ ምሽጎቻችን ናቸው። ብርታት ጽናት ተስፋ ... ይሰጣሉ፡፡ ለጠፋው ሕይወት ሃዘኔን ገልጫለሁ።

ከዚህ በፊት እንዳልኩት ዘርና ሃይማኖትን ለፓለቲካ ጥቅም ማዋል ... ቀይ መስመርን መተላለፍ ነው። የሰው ልጅ በሕይወቱ፣ በሥራው፣ በማህበራዊ ኑሮው ድንበር ከሌለው እራሱ የእደጋ ምን ነው።

የት ይደርሳሉ ብለን ችላ ያልናቸው ሁኔታዎች ናቸው ማጣፍያውን የሚያሳጥሩት፡፡

የሃይማኖት ጉዳይ የቤተ እምነቶቹ አባቶችና ምዕመናን ጉዳይ ነው።

ኢትዮጵያ ባሏት ዘመናትን ያስቆጠሩ በህሎቿ ሃይማኖቶቿ ታሪኳ ... እንኮራለን። እንጠብቃቸው፣ ከጥቃት እንከላከላቸው።

ጥንቃቄ፣ ብልሃት፣ ጥበብ፣ የሰከነ አእምሮ፣ እርጋታ፣ አርቆ አስተዋይነት ... የችግሮች መፍቻ ዘዴዎች ናቸው፡፡

የተደረጉትም ሆነ መደረግ ሲገባቸው ያልተደረጉት ሲታዩ የአገር ጽኑ መሠረት የሆኑትና ለድርድር የማይቀርቡ የዜጎች መሠረታዊ መብቶች፣ የሕግ የበላይነት፣ ለሕግ ተገዢነት፣ ተጠያቂነት፣ የሃሳብ ነጻነት፣ መረጃ የማግኘት መብት... የመሳሰሉት ለአደጋ እንዳይጋለጡ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

ከነበርንበት መከራ ወጥተን ሳናበቃ፣ በአገር በሕዝብ ላይ የደረሱ በርካታ ስብራቶችን ሳንጠግን፣ ሕይወት የሚቀጥፉ ግጭቶችን ሳናስወግድ፣ በርካታ ዜጎቻችን በተፈናቀሉበት፣ በሚሊዮኖች የሰብዓዊ ዕርዳታ በሚሹበት ተመካክረን ተግባብተን ከመሥራት ሌላ አማራጭ አይታየኝም።

አገሪቱ የሁላችንም ነች። ሁላችንንም ያገባናል። ፈጣሪ ይጠብቀን።

የ.ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ