Get Mystery Box with random crypto!

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀናት እጾማለሁ ያለው ፓስተር ህይወቱ አለፈ (እለታዊ የኢትዩትዩብ መ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀናት እጾማለሁ ያለው ፓስተር ህይወቱ አለፈ

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
በሞዛምቢክ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀናት እጾማለሁ ያለው ፓስተር ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል።

ፍራንሲስኮ ባራጃህ የተባለው ፓስተር ከባዱን ነገር ተጋፍጦ ምዕመኑን ለማስደመም ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት በዛሬው እለት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል።

ማኒካ በተባለችው ግዛት ነዋሪ የሆነው ፍራንሲስኮ፥ ለ25 ቀናት ከጾመ በኋላ ከሰውነት ተራ ወጥቶ ህይወቱ ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

ፓስተሩ ቀናት እየገፉ ሲሄዱ መራመድም ሆነ መቆም ተስኖት እንደነበር የተናገሩት ቤተሰቦቹ፥ ቤይራ በተሰኘችው ከተማ ወደሚገኝ ሆስፒታል ወስደውት ህክምና ሲደረግለት ቆይቷል።

የህክምና ክትትሉ ግን የፍራንሲስኮ ባራጃህ “በድንቅ መዝገብ ስሙን የማስፈር ሙከራ” ሊያሳካው አልቻለም።

ቤተሰቦቹም ሆነ የሚያገለግለው ቤተእምነት ምዕመናን እንደማይተርፍ የገባቸው አስቀድሞ መሆኑን የጠቀሰው የቢቢሲ ዘገባ፥ በህልፈቱ ብዙም አለመደናገጣቸውን አመላክቷል።

በደቡብ አፍሪካም ተመሳሳይ ሙከራ የ44 አመቱን ፓስተር ህይወት መቀማቱ የሚታወስ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ