Get Mystery Box with random crypto!

ደራ በደራ ወረዳ ከፍተኛ ስጋት መስፈኑ ተነገረ!! በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ተ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

ደራ
በደራ ወረዳ ከፍተኛ ስጋት መስፈኑ ተገረ!!

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሰው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በወረዳው ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን የአካባቢው ነዋሪዎች መግለፃቸውን አዲስ ማለዳ ዘግባለች፡፡

በወረዳው ውስጥ በምትገኘው ባቡ ድሬ ቀበሌ በርካታ የሆኑ የሸኔ ታጣቂዎች ከተለያየ ቦታ እየመጡ መሰባሰባቸውን የተናገሩት የአዲስ ማለዳ ምንጮች፣ ከዚህ ቀበሌ ባሻገር ሰው በማይኖርባቸው በረሃዎች  በርካታ ታጣቂዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

የሸኔ ታጣቂዎች አጎራባች ከሆኑ የሰሜን ሸዋ ወረዳዎች ወደ ደራ ወረዳ እየገቡ እንደሆነ የተናገሩት ምንጮች፣ የታጣቂዎቹ ብዛት ከዚህ በፊት ከታዩት የበለጠ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ይህም በነዋሪዎች ላይ ስጋት ፈጥሯል ያሉት ምንጮች፣ የሸኔ ታጣቂዎች ከዚህ በፊት በወረዳዋ ነዋሪዎች ላይ ከሚያደርሱት ጥቃት አንጻር ስጋቱ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለሸኔ ታጣቂዎች ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል እጃቸወን ለፖሊስ ከሰጡ ታጣቂዎች መካከልም የተሀድሶ ስልጠና ሳይሰጣቸው ከኅብረሰተቡ ጋር መቀላቀላቸውን የተናገሩት ምንጮች፣ በጉዳዩ ዙሪያ በመንግስት አካላት ጥንቃቄ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡ 

ከቀናት በፊት የወረዳው ነዋሪዎች በሸኔ ታጣቂዎች እየታፈኑ መሆኑን መዘገቧን ያስታወሰችው አዲስ ማለዳ የታፈኑት ሰዎች እስከ 300 ሺሕ ብር የሚደርስ የማስለቀቂያ ክፍያ እየተከፈለላቸው መለቀቃቸው ተሰምቷል ብላለች፡፡ (አዲስ ማለዳ)