Get Mystery Box with random crypto!

💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomerejaa
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

24 Hour News

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-04 19:46:49 በአንዋር መስጊድ የነበረዉን "ተቃውሞ አቀናጅታችኋል" የተባሉ ወጣቶች ከየቤቱ ታድነው እየታሰሩ ነዉ ተባለ

እስከአሁን የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል


ባሳለፍነው አርብ በአዲስ አበባ ከተማ፣ መርካቶ በሚገኘው አንዋር መስጊድ አካባቢ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በአማኙ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት፤ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ስምንት ሰዎች ሲሞቱ፤ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁት ደግሞ ከፍተኛ እና መካከለኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዘመድኩን ብሩ፤ "በዕለቱ ከጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል" ሲሉ ለአዲስ ማለዳ የገለጹ ሲሆን፤ ከሟቾች መካከልም አንድ ግለሠብ መታወቂያ ባለመያዙ ምክንያት እስከአሁን ማንነቱ ሊታወቅ አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም፤ "ሰልፍ አቀናጅታችኋል" የተባሉ ወጣቶች ከየቤቱ ታድነው እየታሰሩ መሆኑን በመግለጽ፤ "ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል" ሲሉ ተናግረዋል።

ሟቾችን ለመቅበር የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ መዋቀሩን የተናገሩት ኃላፊው፣ ትናንት ቅዳሜ ግንቦት 26/2015 ኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መካነ መቃብር የአራት ምዕመናን ሥርዓተ ቀብር መፈጸሙን ገልጸዋል፡፡ የቀሩትንም ወደ ትውልድ ሥፍራቸው በአስቸኳይ ለመሸኘትና ማንነቱ ያልታወቀውን ምዕመን ማንነት ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

"በተለያዩ ሚዲያዎች ሕዘበ ሙስሊሙ ምንም ዓይነት የተቃውሞ ድምጽ ሳያሰማ በሰላም ሰግዶ ሲወጣ ከጸጥታ ኃይሎች ተኩስ እንደተከፈተበት የሚወራው እውነት ነው ወይ?" የሚል ጥያቄ ከአዲስ ማለዳ ቀርቦላቸውም፤ "እሱን ገና በማጣራት ላይ ነን" ሲሉ መልሰዋል፡፡

በተያያዘ በዕለቱ፤ በጅማ ከተማ በተለያዩ መስጅዶች ተመሳሳይ ችግሮች ተፈጥረው እንደነበር በሥፍራው የነበሩ የአዲስ ማለዳ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ለአብነትም መንቲና ወይም ሰቃ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ሙኒር መስጂድ፣ አጂፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ፈቲ መስጂድ እንዲሁም ሀሰን ጋራዥ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ራሕማ መስጂድ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ነግረውናል፡፡

በሥፍራው ከጠዋት ጀምሮ የጸጥታ ኃይሎች በብዛት ይታዩ እንደነበር የነገሩን የመረጃ ምንጫችን፣ የእምነቱ ተከታዮች ሰግደው ሲወጡ ከሰሞኑ እየፈረሱ ስላሉት መስጂዶች ድምጻቸው ማሰማታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህ ሰዓት በአካባቢው የነበሩት የጸጥታ አካላት የተኩስ ድምጽ ማሰማታቸውን የነገሩን ሲሆን፤ በዚህ የተደናገጡት የእምነቱ ተከታዮች ለመሸሽ በሚያደረጉት ጥረት በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡

በሐረር፣ ሻሸመኔ እና ዶዶላ ከተሞችም መሰል ችግሮች ተከስተው እንደነበር በሥፍራው የሚገኙ የአዲስ ማለዳ ቤተሰቦች ጠቁመዋል፡፡ 
1.6K views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 18:46:09 ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በመንግሥት ግፍ የተፈፀመባቸውን እስረኞች መጠየቅ እንደማይችሉ ተነገራቸው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር  ዶክተር ዳንኤል በቀለ ከፍተኛ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈፀመባቸውን 28 የአማራ ተወላጆችን ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሄደው ተጎጂዎችን ለማየት እና የተፈፀመባቸውን ሰብዓዊ ጥሰት ለማጣራት ቢሞክሩም ፖሊስ ጥቃት የደረሰባቸውን እስረኞች አላሳይም በማለት መመለሳቸውን ገልፀዋል።

ጥቃት የደረሰባቸው የአማራ ተወላጆች ግን ጥቃት የተፈፀመባቸውን አካላቸውን እና ዝርዝር ሁኔታውን  ፍርድ ቤት በቀረቡ ጊዜ ማስረዳታቸው ይታወቃል።

መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሞክራችኋል በሚል ለ28 ቀናት በኦሮሚያ ክልል ገላን ከተማ በሚገኘው የልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሲፈፀምባቸው መቆየቱን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል።

ከ28 ታሣሪዎቹ መካከል የእግር እና የእጃቸው ጥፍር በፒንሳ የተነቀለ፣ ጀርባቸውን በኤሌክትሪክ የተገረፉ በዱላ እና በክላሽ ሰደፍ የተደበደቡ እንዳሉ ይታወቃል።
2.1K views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 17:35:06 አርበኛ ዘመነ ካሴ ነጻ መባሉ ተሰማ

                      ንሥር ብሮድካስት
                      ግንቦት 25/2015

መስከረም ወር 2015 በቁጥጥር ሥር የዋለው ዘመነ ካሴ፤ ዛሬ ግንቦት 25 /2015 በባህርዳር ከተማ እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት “ነፃ ነህ” መባሉ ተገልጿል።

ዘመነ ካሴ በመስከረም ወር በቁጥጥር ሥር ውሎ መስከረም 23/ 2015 በባህርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ የ7 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቶት እንደነበር የሚታወስ ነው።

ምርመራውን የያዘው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን "በተሰጠኝ 10 ቀናት ውስጥ ምርመራዬን ማጠናቀቅ አልቻልኩም" በማለት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል።

የዘመነ ካሴ ጠበቆችም ወንጀል የተባለውን ጉዳይ ለማጣራት በሚል ፖሊስ ላለፉት አራት ወራት ያጣራ በመሆኑ እና ፍርድ ቤቱ ባለፈው ችሎት ውሎ የፈቀደው 10 ቀናት በቂ መሆኑን እና ሌሎችን መከራከሪያዎች አቅርበዋል፡፡ ስለዚህም ”የጊዜ ቀጠሮ መስጠት አያስፈልግም“ በማለት ተከራክረው ዘመነ ካሴ በዋስ እንዲለቀቅ ለፍርድ ቤቱ ጠይቀዋል።

የምርመራ ቡድኑ ያቀረበው ምክንያት በቂ አይደለም ያለው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ መርማሪ ቡድኑ ከጠየቀው 14 ቀናት ውስጥ የ7 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ በመስጠት ፖሊስ እስከ ጥቅምት 01/2015 ድረስ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ ትዕዛዝ ተሰጥቶት፤ ዘመነ ካሴም ወደ ባህርዳር ማረሚያ ቤት መመለሱ  ይታወሳል።

"በከባድ የሰው መግደል ወንጀል" ተከሶ የነበረው የዘመነ ካሴ ጠበቆች የክስ መቃወሚያ ማቅረባቸውን ተከትሎ፤ ዐቃቤ ሕግ መልስ ለመስጠት የክስ ችሎት ለማሰማት ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱም አይዘነጋም።

ፍርድ ቤቱም ዐቃቤ ሕግ በጠየቀው መሠረት ለኅዳር 12/2015 ቀን ዘጠኝ ሰዓት በድጋሜ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ፤ ዘመነ ካሴ ለፍርድ ቤቱ የቃልና የጽሑፍ አቤቱታን እንዲያቀርብ ተደርጓል። 

በመጨረሻም ዛሬ ግንቦት 25 /2015 ቀን ሰባት ሰዓት በዋለው ችሎት፤ ዘመነ ካሴ ከወንጀል ነፃ ነህ መባሉን የአዲስ ማለዳ ምንጮች ገልጸዋል። አዲስ ማለዳ ይህን ዘገባ እስካጠናቀረችበት ጊዜ ድረስ ዘመነ ከማረሚያ ቤት እንዳልወጣ ማወቅ ተችሏል ሲል አዲስ ማለዳ ዘግቧል።
2.0K views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 17:34:03 <<ከጁሙዓ በኋላ በንፁሃን ሰጋጆች ላይ በተወሰደው የኃይል እርምጃ በርካታ ሙስሊሞች ላይ ጉዳት ደርሷል። አሁንም ድረስ የህክምና እርዳታ ማግኘት ያልቻሉ ብዙ ናቸው። ይህንን ቀውስ ለመፍታት በአስቸኳይ አምቡላንስ መግባት አለበት።

የፀጥታ ኃይሎች ቀውሱን ከሚያባብሱ እርምጃዎች በመቆጠብ ወደቦታው የመጅሊስ አመራሮች እና የሙስሊሙ የማህበረሰብ መሪዎች እንዲገቡና መረጋጋት እንዲፈጥሩ ሊፈቅዱ ይገባል።

በጥይት ተመትተው ደማቸው እየፈሰሱ ያሉ ሙስሊሞች እርዳታ ሊያገኙ ይገባል።>>
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
1.8K views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 14:40:28
1.9K views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 14:40:18 ፀጋ በላቸው ከእገታ ነጻ ወጣች

ከሰሞኑ እጅግ መነጋገሪያ የነበረችውና ለ10 ቀናት ያክል በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ታግታ የቆየችው ፀጋ በላቸው፤ ከአጋቿ ቁጥጥር ነጻ በመውጣት ወደ ሐዋሳ መመለሷን አዲስ ማለዳ ዘግባለች።

በጉዳዩ ላይ በአሁኑ ሰዓት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ እና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሸን መግለጫ እየሰጡ ሲሆን፣ አዲስ ማለዳ በቦታው ካሉ ምንጯቿ ያገኘችው መረጃ እንደሚያመላክተው፤ ጸጋ ነጻ ብትወጣም እገታውን የፈጸመው የፖሊስ አባል አለመያዙ ታውቋል፡፡

ግንቦት 15/2015 የግል ተበዳይ ፀጋ በላቸው፤ ከሥራ ወጥታ ወደ ግል ጉዳይ በምታመራበት ወቅት በተለምዶው አሮጌው መነሃሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጠለፋው እንደተፈፀመባት በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የመነሐሪያ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለአዲስ ማለዳ መግለጹ ይታወሳል።ጸጋ መታገቷ ከተሰማ በኋላ ፖሊስ ከፍተኛ ክትትል ሲዲርግ መቆየቱን የገለጸ ሲሆን፤ እሳካሁን ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የጠጠረጠሩ ስምንት ሰውች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡
2.0K views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 13:16:18 የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በከንቲባዋ ንግግር ዙሪያ የሰጡት አስተያየት

ሐሙስ መጋቢት 7 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ ባሳለፍነው ማክሰኞ መጋቢት 5/2015 ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት "ከአንዳንድ ክልሎች የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት መንግስትን በመጣል በኃይል ስልጣን ለመቆጣጠር ያለመ ነው" ማለታቸውን ተከትሎ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዚህ ላይ ሀሳብ ሰንዝረዋል፡፡

እናት ፓርቲ የከንቲባዋን ንግግር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እና ግጭት ሊያነሳሳ የሚችል ነው ብሎታል፡፡

“የሚያጠፋ አካል ካለ ኹሌም በሕግ መጠየቅ አለበት።” ያለው ፓርቲው፣ ከዚህ ባለፈ ግን ሰበብ እየፈለጉ የዜጎችን የመንቀሳቀስ ተፈጥሯዊ መብት መጣስ አይገባም ሲል ገልጿል፡፡

እንዲህ አይነት ስህተት የሚፈጽሙ አመራሮች ይስተካከላሉ የሚል ተስፋ ነበር ነገር ግን፣ ስህተቶች እየተደጋገሙ በአዲስ አበባ ዙሪያም በርካታ ቤቶች እየፈረሱ ብዙዎች ተፈናቅለዋል፣ ይህም ቆይቶ ለከተማዋና ለአገር ከፍተኛ አደጋ ያመጣል ነው ያለው፡፡

የእናት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ያየህ አስማረ፣ “መንግሥት ያለው አራት ኪሎ ብቻ አይደለም።” ሲሉ ገልጸው፣ የመንግሥት መዋቅር እስከ ቀበሌ ድረስ ከጫፍ እስከ ጫፍ የተዘረጋ በመሆኑ መንግሥትን በኃይል የመጣል ፍላጎት ያለው አካል አዲስ አበባ አይመጣም ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

አክለውም፣ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት የሚያሳየው በክልሎች ያለውን አለመረጋጋት እና የሥራ እድል አለመኖር ነው ብለዋል፡፡

ስለሆነም ዛሬ አንድን አካል ለማጥቃት የተደረገ እንቅስቃሴ ነገ ኹሉንም ዜጋ የሚያጠቃ በመሆኑ ማንኛውም አካል ሊታገለው የሚገባ ሀሳብ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡

የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር ተክሌ ቦረና፣ “ከንቲባዋ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያሉ ግለሰብ ስለሆኑ ንግግራቸው እንደ ተራ የሚታይ አይደለም፣ “ወደ አዲስ አበባ መንግሥትን ለመጣል የሚገባ አካል አለ” ከተባለ እንዴትና በምን መልኩ የሚለው በግልጽ ለሕዝብ ይፋ መደረግ አለበት።” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ይህ እስካልሆነ ድረስ ግን የከንቲባዋ ንግግር በእውነት ላይ ያልተመሰረተ ተራ ሀሜት ነው በማለት አክለዋል፡፡

የአገሪቱ ሕዝብ ወደ አዲስ አበባ በብዛት እንዲጓዝ የሚያስገድዱት በርካታ ምክንያቶች መኖራቸውን ጠቅሰው፣ ሌሎች ክልሎች የመዲናዋን ያህል መልማት አለመቻላቸው ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር ያለቪዛ ነጻ የሰዎች እንቅስቃሴ እንዲኖር ጥረት እያደረገች ባለችበት ወቅት ከንቲባዋ ይህን መናገራቸው፣ ዜጎች በአገራቸው ያላቸውን የመንቀሳቀስ መብት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን ያሳያል ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡

የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የከንቲባዋ ንግግር ከአንድ ትልቅ ኃላፊነት ላይ ከተቀመጠ የመንግሥት አመራር የማይጠበቅ፣ ጥሩ እና ሚዛናዊ ያልሆነ፣ በእውነት ላይ ያልተመሰረተ ነው ሲል ለአዲስ ማለዳ ገልጿል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ ከንቲባዋ ለምክር ቤቱ ያደረጉት ይህ ንግግር አደገኛ ከፋፋይ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ መሆኑን ገልጾ፣ አገረ መንግሥቱን አደጋ ላይ የሚጥል እና በማናቸውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ዓለም አቀፍ የወንጀል ጥሪ ነው ብሎታል፡፡

ፓርቲው አክሎም “ዓለም አቀፍ ከተማን በከንቲባነት እመራለሁ ከሚል የመንግሥት ባለስልጣን እንዲህ ዓይነት አደገኛ ቅስቀሳ የማይጠበቅ ነው።” ካለ በኋላ፣ መንግሥት ይኼንን አደገኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ ያደረጉትን ግለሰብ ከስልጣን እንዲያነሳና ለፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪ አቅርቧል፡፡

አዲስ ማለዳ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) እና የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ  በከንቲባዋ ንግግር ላይ ሀሳብ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ብትጠይቅም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

በሳሙኤል ታዴ
----------------------------
750 views10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 09:18:34
450 views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 09:18:29 ከአራት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ አየርመንገድ አውሮፕላን አደጋ በደረሰበት ቦታ ላይ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

የዛሬ አራት ዓመት መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ጉዞ እንደ ጀመረ በምሥራቅ ሸዋ ጊንብቹ ወረዳ ልዩ ስሟ ሐማ ቁንጡሽሌ በተባለ ቦታ ላይ በደረሰበት አደጋ የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ጨምሮ 157 የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። በዚሁ ዕለት ሕይወታቸውን ያጡት 17 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የእነዚሁ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች በየዓመቱ አደጋው በተፈፀመበትና አስከሬናቸው ባረፈበት ቦታ  መታሰቢያ እያደረጉ ቆይተዋል፡፡

እነዚሁ የአደጋው ሰለባ የሆኑ ቤተሰቦች በቦታው ላይ ለመታሰቢያ የሚሆን ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት 7ሺህ ካሬ ሜትር በላይ ቦታ ገዝተው ባቀረቡት ጥያቄ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ መልካም ፈቃድ ትናንት የ 4ኛ ዓመት መታሰቢያቸው በተከበረባት ቀን መጋቤ ጥበብ ቀሲስ ጌቱ ሞቲ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ልዩ ፀሐፊ ፣ መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ገብረ ጻድቅ መኮንን የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ፣ ሊቀ ትጉኃን መንክር አቤ፣ መልአከ ኃይል ቀሲስ ኃይለ መስቀል የጊንቢቹ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ፣ መምህራን ፣ዘማሪያን እንዲሁም ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የማጽናኛ ዝማሬና ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል  መባሉን ዳጉ ጆርናል ከቤተክርስቲያኗ የዜና ምንጭ ካገኘዉ መረጃ ተመልክቷል፡፡

በመቀጠልም መጋቤ ጥበብ ቀሲስ ጌቱ ሞቲ ይህን ቅዱስ ዓላማ ወገኖቻቸውን ለማሰብ ቤተክርስቲያንን ለማነጽ መነሳሳታቸው እጅግ የሚበረታታ መሆኑና ዘመን የማይሽረው ታሪክን በወገኖቻቸው ስም እያስቀመጡ መሆኑን ገልጸው የብፁዕነታቸውን አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል ሲል ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ዘግቧል።
455 views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 17:13:49
344 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ